ጠንካራ ተቋማትን የመፍጠር ሕልም እና ጉዞ
ኢትዮጵያ የታሪክ ሐብታም ከሆኑ ሀገራት መካከል ስሟ ቀድሞ ይጠቀሳል፡፡ ሀገሪቱ ካሏት ግዙፍ ታሪኮች መካከል ደግሞ የረጅም ዘመን የመንግስትነት ሥርዓት አንዱ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ያላት የሥርዓተ መንግሥት ታሪክ ግን በዕድሜው ልክ ጠንካራ እና ወጥነት ያለው ሳይሆን በመንግስታት መለዋወጥ ውስጥ ውጣውረድ የበዛበት ሆኖ ቆይቷል፡፡
ለዚህ ደግሞ አንዱ ምክንያት እየደመሰሱ የመቅዳት አባዜ ሲሆን ኢትዮጵያን ካስተዳደሩ መንግስታት መካከል ጥሎ ያልወደቀን ማግኝቱ ከባድ ነውና ከውጣውረዶቹ አንዱ ሆኖ ይነሳል፡፡
እንዲህ ያለው ውጣውረድ ደግሞ ኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ የተቋማት ግንባታ እንዳይኖራት ያደረገ ክስተት ሆኗል፡፡
እነዚህ ተቋማት ነጻ እና ገለልተኛ ሆነው የመንግስታት ለውጥ የማያውካቸው ይልቁንም ለመንግስት አቅም የሚሆኑ እንዲሆኑ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ይህን የማረጋገጥ ስራ በብዙ መልኩ ፈተና የበዛበት እንደሆነ ቆይቷል፡፡
የነበረውን የማፍረስ ችግር ጎልቶ የሚታየው አንዱ ሥርዓት ሄዶ ሌላው ሥርዓት ሲተካ መሆኑ ተቋማት በመንግስታት ለውጥ ውስጥ እየተጠናከሩ እንዳይሄዱ ትልቅ ምክንያት ሆኗል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ከተመሰረተችበት የረጅም ዘመን ጉዞ አብላጫው የጦርነት መሆኑ በተቋማት ግንባታ ውስጥ የሁልጊዜ እንቅፋት እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ኢትዮጵያ ምንም እንኳ ጥንታዊ የመንግስት ሥርዓት ባለቤት ብትሆንም የነበረውን የማፍረስ ችግር ፖለቲካዊ ኋላቀር ሆኖ እንዲቀጥል አድርጎታል፡፡
መንግሥታዊ ተቋማት መሠረታቸው ጠንካራ ካልሆኑ የግለሰቦች ተክለ ስብዕና ብቻ ገዝፎ ለዘላቂ የሀገረ መንግስት ግንባታ የሚሰጠው ትኩረትም ሆነ ቁርጠኝነት እዚህ ግባ የማይባል ይሆናል፡፡
በኢትዮጵያም ይህ ችግር በመኖሩ የሀገር ግንባታ ሒደቱ ላይ ስምምነቶች እንዳይኖር አድርጎት ቆይቷል።
የሰዎች በነፃነት መንቀሳቀስ እና መኖር የሚረጋገጠው ሕግ አስከባሪ ተቋማት በጠንካራ መሰረት ላይ ሲገነቡ ነው፡፡ ዜጎች መብታቸው የሆነውን አገልግሎትን በሥርዓት ማግኘት የሚችሉትም ተቋማቱ ሕግ አክብረው የሚሠሩበት ተቋማዊ ልዕልና ሲኖራቸው ነው፡፡