የኢስላም ውበት
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
๏| ነሲሓ መጽሔት ቅጽ Vol1 ቁጥር 1 |๏
https://telegram.me/nesihablog
ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ነው:: የአላህ ሰላም እና እዝነት የመልዕክተኞች ሁሉ መደምደሚያ በሆኑት ነብይ በሙሀመድ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን::
ኢስላም ማለት ከአላህ በቀር በሀቅ የሚመለክ አምላክ የለም ሙሀመድ ﷺ የአላህ መልዕክተኛ ናቸው:: ብሎ በልቦና ማመን፣ በአንደበት መመስከር እና በተግባርም ማረጋገጥ ሲሆን፤ በስድስቱ የእምነት መሰረቶች ማመን እና አምስቱን የኢስላም መሰረቶች መተግበር፣ እንዲሁም ይሄንኑ ተግባር ባማረ መልኩ ማከናወን (ኢህሳንን) ያጠቃልላል::
ኢስላም፤ አላህ የነብያትንና የመልዕክተኞች (ሩስሎች) መደምደሚያ በሆኑት ሙሀመድ ኢብን ዐብደላህ ላይ ያወረደው የመልዕክቶቹ ሁሉ መቋጫ ነው:: አላህ ዘንድም ከኢስላም በቀር ተቀባይነት ያለው ሀይማኖት የለም:: ይህንን እውነተኛ ሀይማኖት አላህ ገር እና ቀላል፣ አዳጋችም ሆነ አስቸጋሪ ነገር የሌለበት አድርጎታል:: አማኞችን ከአቅም በላይ የሆነ ትዕዛዝ አላዘዛቸውም፣ የማይችሉትንም ግዴታ አላደረገባቸውም::
ኢስላም፤ መሰረቱ የአላህ አንድነት (ተውሒድ)፣ መነሻው ሀቅና እዝነት፣ መለያው እውነተኝነት፣ መሽከርከሪያ ዛቢያው ፍትህ ነው:: ኢስላም ሰዎችን ለመንፈሳዊ ህይወታቸውም ሆነ ለዓለማዊ ኑሮቸው ጠቃሚ ወደ ሆነ ነገር ሁሉ የሚመራ፣ በአንጻሩም ጎጂ ከሆነ ነገር ሁሉ የሚያስጠነቅቅ ሀይማኖት ነው::
ኢስላም፤ አላህ የሰው ልጆችን እምነት እና ባህሪ ያስተካከለበት፣ የዱንያን እና የአኼራ ህይወት ያሳመረበት፣ የተራራቁ አመለካከቶችን እና የተለያዩ ዝንባሌዎችን አንድ በማድረግ ከንቱ ከሆነ ጽልመት አጥርቶ ወደ እውነት የመራበት ሀይማኖት ነው:: አጠቃላይ ህግጋቱም ሆነ መልዕክቶቹ ፍጹም በሆነ መልኩ ተብራርተዋል::
ኢስላም ሀቅን እንጂ አልተናገረም ! በእውነት እና በፍትህ እንጂ አልፈረደም ! ትክክለኛ እምነትን እና ቀና የሆኑ ተግባራትን አስተምሮል፣ በእውነት ኢስላምን የሚኖር ሰው ግሩም ባህሪን እና የላቀ ስርዓትን ይላበሳል::
የኢስላም መልዕክት የሚከተሉትን አላማዎች ያካትታል፦
1_ የመጀመሪያ ዓላማው የሰው ልጆችን ከፈጣሪያቸው ጋር ማስተዋወቅ ሲሆን፤ ያማሩ ስሞቹ ወደር እንደሌላቸው፣ መልካም ባህርያቱ ምሳሌ እንደሌላቸው፣ በጥበብ የተሞሉ ስራዎቹንም ማንም እንደማይጋራው፣ እንዲሁም በፍፁም ቢጤ እንደሌለው አምልኮም ለእርሱ ብቻ እንደሚገባ ያስተምራል::
2_ የሰው ልጆች አላህ የደነገጋቸውን እና በዱንያም ሆነ በአኼራ ስኬታማ የሚያደርጋቸውን ትዕዛዛቱን በመፈፀም፣ ከከለከላቸውም ነገሮች በመቆጠብ፣ አጋር የሌለውን አላህን ብቻ እንዲያመልኩ ይጣራል::
3_ የሰው ልጆች ከሞት በኌላ የሚኖራቸውን ዕጣ ፈንታ፣ ከሞት በኌላ እስከ ሚቀሰቀሱ እና በትንሳኤ ቀን የሚያጋጥማቸውን ክስተት ያስተምራል:: አላህም ባሮቹን በመጪው አለም እንደሚተሳሰባቸው ይናገራል:: የመልካም ስራ ዋጋ መልካም፣ የክፉ ስራ ምንዳም ክፉ በመሆኑ እንደየስራቸው መጨረሻቸው ጀነት ወይም እሳት እንደሚሆን ያስገነዝባቸዋል::
እንደሚታወቀው ኢስላም የግለሰቦችንም ሆነ የኢስላማዊ ማህበረሰቦችን ሕይወት በዱኒያም ሆነ በአኺራ ለስኬት በሚያበቃቸው መልኩ ስርዓት አስይዟል:: ለምሳሌ፦ ትዳርን ፈቀደ አበረታታም! በአንፃሩም ዝሙትንና ግብረ-ሰዶማዊነትን እንዲሁም መሰል ፀያፍ ተግባራትን ከለከለ:: ዝምድናን መቀጠልን፣ለፍጡራን ማዘንን፣ ድሆችንና ችግረኞችን መንከባከብን ግዴታ አደረገ:: መልካም ፀባይን ሁሉ አስተማረ::
ከመጥፎ ፀባይም ሁሉ አስጠነቀቀ:: ለተከታዮቹ ከንግድ፣ ከኪራይና ከመሳሰሉት የገቢ ምንጮች የሚገኝን ሀላል ትርፍ ፈቀደ:: አራጣን እና ሊሎችን ማጭበርበር ያለባቸውን የንግድ እንቅስቃሴዎች በሙሉ እርም አደረገ:: ጠርዘኝነትን ከልክሎ ማዕከላዊ አመለካከትን ያሰፍናል፡፡
ሰዎች ለህግጋቱ ከመገዛትና የሌሎችን መብት ከመጠበቅ አኳያ ስለሚለያዩ ዝሙት፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣትና በመሳሰሉት የአላህን ሕግ በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ ቅጣትን ደንግጎል:: እንዲሁም በሰዎች ደም፣ ንብረትና ክብር ላይ በሚፈፀሙ እንደ ግድያ፣ ስርቆት፣ ስም ማጥፋት፣ የሰዎችን ንብረት ያለአግባብ መውሰድ የመሳሰሉት ወንጀሎችም ላይ ገሳጭ ቅጣቶችን ደንግጓል:: ቅጣቶቹ በደል የሌለባቸው ፍጹም ፍትሀዊ ናቸው::
ኢስላም በገዢና በተገዢ መካከል ያለውን ግንኙነት በመወሰን አስተዳደርን ስርዓት አስይዟል:: በኢስላማዊ ስርዓት ማህበረሰቡ ወንጀልነክ ባልሆኑ ነገሮች ሁሉ ለገዢው መደብ ታዛዥ እንዲሆን ግዴታ አድርጎል:: በግለሰቦችና ባጠቃላይ ማህበረሰቡ ላይ በሚያስከትለው መዘዝ ሳቢያ በመሪዎች ላይ የሚደረግ አመጽን ከልክሏል::
በመጨረሻም ይህችን አጠር ያለች መልዕክት በዚህ ማጠቃለያ ሀሳብ እንቌጫለን::
ኢስላም መልካም ባህሪንና ጥሩ ማህበራዊ ግንኙነትን ለተከታዮቹ አስተምሮል:: በሰው ልጆችና በጌታቸው፣ በግለሰቦችና በሚኖሩበት ማህበረሰብ መካከል በሁሉም መስክ ትክክለኛና መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ያስችላል:: በአንጻሩም መጥፎ ከሆኑ ባህሪያትና ለመልካም ግንኙነት መሻከር ምክንያት ከሚሆኑ ነገሮች ሁሉ አስጠንቅቌል:: ይህም የኢስላምን ሙሉዕነትና በሁሉም ጎኑ ለሰው ልጆች የሚበጅ እንደሆነ በጉልህ የሚያሳይ ነው::
ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ነው::
∞∞∞∞≅≅≅≅∞∞∞∞