ከቁርኣን አሻራ
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
๏| ነሲሓ መጽሔት ቅጽ Vol1 ቁጥር 1 |๏
መደብ | ነሲሓ የዕውቀት ማዕድ
http://nesiha.com/blog
ምስጋና ለአለማት ጌታ ለሆነው አላህ ተገባው። የአላህ ሰላትና ሰላም በተወዳጁ ነብያችን፡ በቤተሰባቸው፡ በባልደረቦቻቸው፡ እንዲሁም የእነርሱን ፈለግ በመልካም በተከተሉ ሁሉ ላይ ይሁን።
ይህ ቁርአን ለየትኛውም መፅሃፍ ተስጥቶ ያልታየና ያልተሰማ ክብርና ተአምራትን የያዘ ብቸኛውና ብርቅዬው መፅሃፍ ነው። የሰው ልጆች ከጨለማ ወደ ብርሃን ሊወጡበትና የህይወታቸው መመሪያ ያደርጉት ዘንድ ከአላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) የወረደ የተከበረ የእርሱ ንግግር ነው። ስለዚህ ባጠቃላይ የሰው ልጆች። ለየት ባለ መልኩ ደግሞ ሙስሊሞች። ህይወታቸውን በእምነትም ይሁን በስነምግባር፤ በፓለቲካም ይሁን በኢኮኖሚ ባጠቃላይ በሁሉም የህይወት ዘርፋቸው አንድና ቀጥተኛ መንገድን ከፈለጉ ይህንን ታላቅ መፅሃፍ ማጥናትና መመርመር ግድ ይላቸዋል። የወረደበትም ብቸኛው አላማም ይህ ነው። አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ይህን ሲናገር እንዲህ ብሏል፦
كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ [٣٨:٢٩] “
ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መፅሃፍ ነው። አንቀፆቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮ ባለቤቶችም እንዲገሰፁበት (አወረድነው) “ (ሷድ 29)
የሚገርመው ግን ብዙ ሙስሊሞች ከዚህ ታላቅ መመሪያቸው ርቀውና ችላ ብለው ይገኛሉ፡፡ሻል ያሉት ደግሞ ፊደሎቹን ከመሸምደድና አቀራሩን (አነባበቡን) ለማሳመር ከመጨነቅ የዘለለ ግብ የሌላቸው ሆነው ነው ሚስተዋሉት። በእርግጥ ይህ ሲባል ቁርአንን በማንበብ (በመቅራት) አሊያ በመሸምደድ ብቻ ከፍተኛን ምንዳ እንደሚያስገኝ ማስተባበል አይደለም! በፍፁም! እንደውም ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ይህን ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል ፦
"من قرأ حرفا من كتاب الله فله به حسنة والحسنة بعشر امثالها لا أقول "الم" حرف ولكن:ألف حرف ولام حرف وميم حرف"
“ ከአላህ መፅሃፍ አንድን ፊደል ያነበበ አንድ የመልካም ምንዳ (ሃሰና) አለው። እያንዳንዱ ምንዳም በአስር (ይባዛል)” አሊፍ ላም ሚም” አንድ ፊደል ነው አልልም። ይልቁንም “አሊፍ” አንድ ፊደል ነው። “ላም” አንድ ፊደል ነው። “ሚም” አንድ ፊደል ነው።” ቲርሚዚ ዘግበውታል።
እንግዲህ ቁርአንን ቃሉን በማንበብ ብቻ ይህን ያህል ምንዳ ቢያስገኝም ግና ከዋናው አላማ ማለትም ህይወትን ሁሉ በእርሱ የህይወት ቀመር ማስጓዝ ከሚለው አላማ ግን ሊያዘናጋን ፈፅሞ አይገባም። ታዲያ ጊዜ ሳይሄድብን ህይወትን ሳናጣ ይህንን እንቁ መፅሃፍ መሪ ብርሃን ለማድረግ ሌት ከቀን ሳንል መጣርና መልፋት ይጠበቅብናል። ይህንን ለማድረግ ደግሞ ቅድሚያ እርሱን እያዩ በሚገባ ከማንበብ በመጀመር ፍቺውን በመረዳት ሊጠና ይገባል። አንዳንድ ሰው አይገባኝም በማለት አይቀራም። አንዳንዱ ደግሞ እድሜዬ ሄዷል እንዴት ችዬ እቀራዋለው በማለት እራሱን ከቁርአን ያገላል።
በፍፁም ይህ ሁሉ ስህተት ነው። ኧረ እንዲያውም የአላህን (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ቃል ማስተባበል እንዳይሆንብንም ያሰጋል። ምክንያቱም እርሱ ነጭ ጥቁር ሴት ወንድ ልጅ አዋቂ ብሎ ሳይለይና ሳይገድብ ይህንን ታላቅ ቁርአን ለመቅራት፤ የህይወቱ መመሪያ ለማድረግ ለፈለገ ሁሉ ገርና ቀላል እዳደረገው እንዲህ ሲል ተናግሯል።
وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ [٥٤:١٧]
“ ቁርአንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው።ተገንዛቢ አለን?” ( ቀመር 17)
እንግዲህ ከዚህ የፈጣሪ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ብስራት በውሃላ ለማንኛውም ሰው በራሱና በቁርአን መካከል ግርዶ ሊያደርግ አይቻለውም። ይልቁንስ አላህ ዕርሱን ለቁርአኑ እንዲያገራው እየለመነ ጥረት ሊያደርግ ግድ ይላል።
አንጠራጠር ተራራን ሊንድና ሊያንኮታኩት የደረሰ ተአምር የኛን ልብ የማያርድበት ምክንያት ፈፅሞ አይኖርም።እንከንና ወለምታው የኛ ሆኖ ነው እንጂ ። አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ይህንን ሲናገር እንዲህ ብሏል።
لَوْ أَنزَلْنَا هَٰذَا الْقُرْآنَ عَلَىٰ جَبَلٍ لَّرَأَيْتَهُ خَاشِعًا مُّتَصَدِّعًا مِّنْ خَشْيَةِ اللَّهِ ۚ وَتِلْكَ الْأَمْثَالُ نَضْرِبُهَا لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ [٥٩:٢١] “
ይህንን ቁርአን በተራራ ላይ ብናወርደው ኖሮ ከአላህ ፍራቻ (የተነሳ ) ተዋራጅና ተሰንጣቂ ሆኖ ባየኅው ነበር። ይህችንም ምሳሌ ያስተነትኑ ዘንድ ለሰዎች እንገልፃታለን።” (አል ሃሽር 21)
እንግዲህ ይህ ከሆነ እውነታውና ተጨባጩ ሙስሊሞችን፡ በተለየ መልኩ ደግሞ ከእነርሱ ውስጥ ከቁርአን የራቁና አሊያ የሚቀሩት ሆነው ግና ለፊደሎቹና ለድምፁ በመጨነቅ ላይ ብቻ ተወጥረው በርሱ መስራትን፡ በርሱ መኖርን ግን አይኑን ላፈር ላሉ፤ እንዲሁም ሙስሊም ላልሆኑና የሰላምን ፍኖት በህይወታቸው ለሚያቀነቅኑ ሁሉ ወደዚህ ታላቅና እንከን የለሽ ቅዱስ መፅሃፍ እንዲመጡ፤ የያዘውን የሚስጥር ካዝና እንዲመረምሩ ልባዊ ጥሪያችንን እናቀርብላቸዋለን።
እንዴታ በርሱ የተናገረ እውነተኛ ነው። በርሱ የፈረደ ፍትሃዊ ነው። በርሱ የኖረ ነፃ ነው። በእርግጥም አንብበው መርምረው የህይወት መመሪያ ሊያደርጉት የሚገባው ብቸኛው መፅሃፍ ቁርአን ነው።
ኡሙ ዐብዲላህ ነፊሳ ሙሐመድ
∞∞∞∞≅≅≅≅∞∞∞∞
https://telegram.me/nesihablog