ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመናፍቃንና ለአህዛብ መልስ አላት!


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


እዚህ ቻናል ውስጥ አህዛብ እና መናፍቃን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች በክርስቶስ አምላካችን ፣ በቅዱሳኑ ትሩፍት እና በስርዓተ ቤተ ክርስትያን ላይ ስለ ሚነሱ የስህተት ና የቅሰጣ ትምህርቶች ሙሉ መልስ የሚሰጥበት ቻናል ነው። በተመሳሳይ፦
* የቤተ ክርስትያን ቀኖና፣ዶግማ፣ትውፊት፣ታሪክ
* ነገረ ቅዱሳን
ይዳስሳሉ ይነገራሉ።
ለማንኛውም አስተያየት በዚህ ታገኙናላችሁ
@Selamawitttttttt

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri




እስኪ ኦርቶዶክሳዊያን በትህትና በጥሞና አንብቧት
ክፍል አንድ

✥✥✥ በዐለ ደብረዘይት ✥✥✥

ትርጉሙ፦ ደበረ ዘይት ትርጉሙ የወራ መብቀያ፣ በወይራ ደን የተሸፈነ ተራራ ማለት ነው። ወይም «ደብር» ማለት «ተራራ» ማለት ሲሆን «ዘይት» ማለት ደግሞ «ወይራ» ማለት ነው። በተገናኝ «ደብረ ዘይት» ማለት የወይራ ዛፍ የሞላበት፣ የበዛበት፣ የወይራ ተራራ ማለት ይሆናል።

- ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ ቦታ የሚገኝ ተራራ ሲሆን በመካከል የቄድሮን ሸለቆ ብቻ ነው ያለው። ከግርጌው ጌቴ ሴማኒ የተባለው የአትክልት ስፍራ ይገኛል። የጸሎተ ሐሙስ ማታ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተያዘበትና በኋላም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋዋ ያረፈበት ወይም የድንግል መካነ መቃብር በዚህ ተራራ ግርጌ ይገኛል። ቤተ ፋጌ እና ቢታንያ በኮረብታው ጫፍ እና በምስራቅ ዳገታ ላይ ይገኛሉ።

- ይህ ተራራ በመፅሐፍ ቅዱስ የሚገኙ ብዙ ድርጊቶች የተደረጉበት ቦታ ነው። ጌታችን ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስ፣ ስለ ዓለም ፍጻሜና ስለ ዳግም ምጽአት በዚህ ተራራ ላይ በትንቢት መልክ ተናገረ (ማቴ.24፥3)። በዚሁ ተራራ ላይ ወደ ሰማይ ዐረገ (ሉቃ.24፥50)። በዚሁ ተራራ ላይ ቀን በከታማና በገጠር ሲያስተምር ውሎ ሌሊት የሚያድርበት የኤሌዎን ዋሻ ይገኛል።በኋለኛው ምጽአቱ በዚሁ ቦታ እንደሚገለጥ ትንቢትተነግሯል።(ዘካ. 14፥3-5)።

- ስያሜው፦ የዓቢይ ጾም እኩሌታ ላይ ያለው ሰንበት በዚህ ተራራ ተጠርቷል። ይህንን ዕለት የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የዳግም ምጽአት አድርጎ መዝሙሩን ጽፏል። በዚህ ተራራ ላይ «እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት» (ማቴ.24፥3)። ተብሎ እንደተጻፈው ለደቀ መዛሙርቱ የዳግም ምጻቱን፣ የዓለምን ፈጻሜ፣ የትንሣኤ ሙታንን፣ ትምህርት በሰፊው ስላስተማረ በዓሉ በተራራው ስም ተሰይሟል።

➕ አመጣጡስ እንዴት ነው?

- ጌታ ይህንን ዓለም ለማሳለፍ ለሁሉም እንደ ሥራው ለመክፈል በግርማ መለኮቱ በክበበ ትስብዕቱ(ከድንግል ማርያም በነሳው ቅዱስ ሥጋው) ይመጣል፡፡ ጊዜው ዘመነ ዮሐንስ ወርኃ መጋቢት ዕለተ እሑድ መንፈቀ ሌሊት እንሆነ ሊቃውንት ተናግረዋል፡፡ምነው ‹‹ የሚያውቀው የለም ይል የለምን ቢሉ እውነት ነው የሚያውቀው የለም ብዙ የዮሐንስ ዘመን ብዙ የመጋቢት ወር ብዙ የእሑድ ዕለት የበዙ ሌሊቶች አሉና ለይቶ የሚያውቅ የለም ለማለት ነው፡፡

-> ሞት ለማንም አይቀርምና ሁሉም ይሞታል፡፡ ዘፍ 3፡19 በዕለተ ምጽኣትም ቅዱስ ገብርኤል ስምንቱን ነፋሳተ መዓት ከየመዛግብታቸው ያወጣቸዋል፡፡ ዛፍን ነቅለው ድንጊያውን ፈንቅለው ምድርን እንደብራና ይዳምጧታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ነጋሪቱን ይመታል ፩ኛመቃብ ፱፥፰ ነጋሪት የተባለው በቁሙ ነጋሪት የሚመታ ሆኖ ሳይሆን አዋጁን የምትክ ንቃ የሚል አዋጅ የሚናገር ይታወጃልና ነጋሪት ይመታል አለ

. ስለዚህ ቅዱስ እግዚኣብሔር ቅዱስ ዘያነቅሖሙ ለሙታን ሲል በዱር በገደል በባህር በየብስ በመቃብር ውስጥ ያሉት በአውሬ ሆድ ውስጥ ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡
. በሁለተኛው ነጋሪት ሲመታ አጥንትና ሥጋ አንድ ሆነው ፍጹም እንደ ዕለት በድን ይሆናሉ፡፡
. ሦስተኛው ነጋሪቱን መትቶ /ቅዱስ እግዚኣብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት / ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም ባለ ጊዜ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ደጉ ደግነቱን ክፉውም ክፋቱን ይዞ ይነሳል፡፡

- ወንዱ የ30 ዓመት ሴቲቱ የ15 ዓመት ሆነው ጻድቃን ብርሃን ለብሰው ብርሃን ተጎናጽፈው ከፀሐይ 7 እጅ አብርተው ማቴ 13፡43 ኃጥአን ጨለማ ለብሰው ፍጹም ዲያብሎስን መስለው ይነሳሉ፡፡ ጻድቃን ስለሠሩት መልካም ሥራ ኑ የአባቴ ብሩካን ብሎ መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸዋል፡፡ ኃጥአንን ስለክፋ ሥራቸው /ከእኔ ሂዱ/ ብሎ ገሃነም ይሰዳቸዋል፡፡
ጻድቃን ደስ ይላቸዋል ኃጥአን ግን ያዝናሉ ዋይ ዋይ እያሉ ደረት ይደቃሉ እንባቸውን ያፈሳሉ፡፡ የማይጠቅም ልቅሶ ይሆናል የማይረባ ኃዘን ነው ሰቅለው የገደሉትም አይሁድ ክብሩን 0ይተው ላይጠቀሙ ይጸጸታሉ፡፡

- በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ከቅዱሳኑና ከሰማዕታቱ ጋር ለመቆም ያብቃን፡፡🤲

-> መዝሙር ዘደብረ ዘይት እንዘ ይነብር እግዚእነ ወስተ ደብረ ዘይት ይባላል

-> ምንባብ ዘቅዳሴ
- 1ተሰሎ 4÷13-ፍም::
- 2ጴጥ 3÷7-15::
- ግሐዋ 24÷1-22

-> ምስባክ
" እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመፅእ፣ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ" መዝ 49÷2

-> ወንጌል፦ ማቴ፡ 24÷1-36

-> ቅዳሴው ቅዳሴ አትናቴዎስ




"…በገዳሙ የሚኖር ማንኛውም መነኩሴ ከሊቅ እስከ ደቂቅ 150 መዝሙረ ዳዊት በቀን እንዲደግም። ከደገመ በኋላም መጸሐፉን መሬት ላይ ደፍቶ ያስቀምጥ። መቁጠሪያውንና መቋሚያውን ጸሎት ከጨረሰ በኋላ መሬት ላይ ይጣል። ምግብን በተመለከተ በቋርፍ ቤትም ሆነ ብእህል ቤቶችና  በአትክልት ቦታዎች ጨው፣ በርበሬ፣ ያለበት ምግብ ከሰኞ ጀምሮ ለ3 ቀን እንዳይመገብ። በማንኛውም ቦታ የገዳማችን መነኮሳት ባእት እሳት እንዳይነድ። ከቤተ እግዚእብሔር የሚሰጠውን ብቻ እንዲመገብ። የተመገበበትን ፋጋ ከጨረሰ በኋላ ባፉደፍቶ እንዲያሳድር። ከምሽቱ 12 ሰዓት ውጭ የመቁንን ደውል እንዳይደውል። ውኃ ከአንድ ብርጭቆ በላይ እንዳይጠጣ። ሻይ እንዳይፈላ። ጭልቃ እንዳይጨለቅ ወስኗል። 

"…ይህ ትእዛዝ በሁሉም የቋርፍ ቤት፣ የአትክልት ቦታ፣ የሞፈር ቤቶች፣ በየዋሻው እና በየፍርኩታው ላሉ ባህታውያን አባቶች መልክቱ ይተላለፍ። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና በሀገራችን የመጣው አደጋ ቀላል አይደለም በሚል ተወስኗል። ይህ ውሳኔ ከትናንት ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል።

"…በአባቶች በኩል ነገሩ በጥብቅ ተይዟል። ነገሩን ያከበዱት ይመስለኛል።


የዋልድባ አባቶች መልእክት

"…የዋልድባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ዘቤተ ሚናስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና  በቅዱስ ሲኖዶስ የወጣውን መመሪያና ትእዛዝ ተከትሎ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ/ም ማኅበረ መነኮሳቱ በአብረንታንት ቤተ እግዚአብሔር ተስብስበው የቅዱስ ስኖዶስ ውሳኔ በገዳማችን እንዲተገብር በማለት ማኅበረ መነኮሳቱ ወስነዋል።

"…በተጨማሪም ማኅበረ መነኮሳቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለቅዱስ አባታችንም፣ እንዲሁም ልህዝበ ክርስቲያኑ የማጽናኛና የማበረታቻ አይዟችህ የሚል ገዳሙ ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤም እንዲጻፍ ሲሉ ማህበረ መነኮሶቱ ወስነዋል። በተጨማሪም በቋርፍ ቤትና በሞፈር ቤቶች ከቀድሞው (ዘወትር ከምናደርገው) በተለዬ መልኩ ጸሎተ ምህላው ተጠናክሮ ይቀጥል።




ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡


➡ ከላይ ያሉትን ሊንኮች እየከፈታችሁ መመልከት ትችላላችሁ❗


በቀጥታ ለአቶ እንዳልክ ዘነበ

ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ በላይ የአማልክትን አምላክ ኢየሱስን ማን አከበረ ?
=============================================================

‹‹ ‹ቅል እንኳን ማንጠልጠያ አለው› የሚል የገረጀፈ ጸረ-ኢየሱስ የሆነ የመንደር ትርክት የምትነግሩኝ የዚህ መንደር የእሁድ ክርስትያች›› በማለት ዲያቆን ነበርኩ የሚል፣ምናልባትም ዲያቆን ሆኖ ‹‹እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ›› የሚለውን ብሎ የማያወቅ ሰው ነው ይሄን ያለን፡፡አሁን አሁን ፕሮቴስታንትነት ስለበዛ በእነሱ መንገድ የተሳብን እንጂ ስሙን እንዲህ ነበር የምንጠራው ‹‹ጌታችን አምላክችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ››፡፡ይሄን አጠራር ነው እንዳልክ የተባለው ሰው መንጠልጠያ እያለ አክብሩት የሚለንን የእየሱስን ስም አጠራር የሚያጣጥለው፡፡‹‹ ማንጣልጠያ የሚፈልገው ብቻውን ሙሉ ሆኖ መቆም ለማይችል ስም ነው›› ይለናል፡፡ ጨምሮም ‹‹ኢየሱስ የሚለው ስም ውስጥ መድሃኒት፣ጌትነት፣ስልጣን አለቅነት ገዢነትና ሀይል አለ›› በማለት የብራራል፡፡ በሌላ ጽሁፉ ደግሞ ‹‹በቀን ውስጥ ሳልጠራው የማልውለው ስም ኢየሱስ›› ይላል፡፡ እንዲሁም ፕሮቴስታንቶች በሚያዘዋውሩት አንድ ቪዲዮ ላይ ‹‹ከማንም የሀይማት ተቋም ውስጥ መወሸቅ እልፈልግም ›› ይለናል፡፡ እንግዲያው እኛ ኦርቶዶክስ ውስጥ ያለነው እውነት ስሆነ እንጂ ለመወሸቅ ፈልገን አይለም፡፡፣መጽሃፍ ቅዱስ ይዳኘን፡፡

የእንዳልክን መንጠልጠያ ስላቅ እንፈትሽ፡፡ በቲቶ 2፡13 ላይ ‹‹የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ›› ይላል፣ 2ኛ ቆሮ 1፡2 ላይ ‹‹ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ››፣ ፊልሞና1፡25 ላይ ‹‹ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ›› ይላል፡፡እንዳልክ ግን እየሱስ ብቻ በሉ ይለናል፡፡ማንጠልጣያ ተጨማሪ አያስፈልገውም ይለናል፡፡ማንን እንከተል እንዳልክን ወይስ መጽሃፍ ቅዱስን? ምርጫው የእናንተ ነው፣ኦርቶዶክስ ግን መጽሃፍ ቅዱስን ነው የምትከተለው፡፡የእንዳልክ አይነቱ ለስሙ ዲያቆን ነበርኩ የሚል ማንጣልጣያውን ተው እያለ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መድሃኒትንት ጌትንት በሥም አጠራሩ እንዳንመሰከር ይቃወመናል፡፡እኛ ግን መጽሃፍ ቅዱስን ሃዋሪያትን እንከተላለን፡፡የተወሸቅነው መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን አምላካችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጉያ ውስጥ ነው፡፡ተቃዋሚዎቹ ጌታ አምላክ ክርስቶስን በዚህ መልኩ ስላከበርነው ይከፋቸዋል፡፡

በእርግጥ በፖለቲካ ላይ በሚያነሳው ትችቶች በመንግስት አይን ውስጥ የገባው እንዳልክ፣ከኦርቶዶክስ ጠሉ መንግስት እና ስርዓት ጋር ለመታረቅ ኦርቶዶክስን ማብጠልጠሉ አይገርምም፡፡ ግናስ ለጥቂት ቀናት ሲታሰር ባር ባር ያለው እንዳልክ በኢየሱስ ስም ሞት እንኳን ቢመጣ ማለቱ ቀድሞውኑ ኦርቶዶክስን የሚዘልፍ መች ሞት ይመጣበትና በሚል ስርዓቱ ኦርቶዶክስ ጠል ስለሆነ ተማማኖ ነው፡፡አይገርመንም፡፡ብዙ አባቶቻችን ስለ ክርስቶስ ብለው መስዋዕት ተቀብለዋል፣በኦርተዶክስ ለክርስቶስ ብሎ መከራን መቀበል አዲስ አይደለም፡፡

እንዳልክ ‹‹ኢየሱስ ጌታ ነው ስትባሉ በቀጥታ አሜን ማለት ሲገባችሁ›› እያለ ኦርቶዶክሳዊያንን ይዘልፋል፡፡የትኛውን ኢየሱስ እንደሚያመልኩ አትጠይቁ ዝም ብለችሁ አሜን በሉ ይለናል፡፡መጽሃፍ ቅዱስ 1ኛ ዮሐ 4፡1 ላይ ግን እንዲህ የለናል ‹‹ ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።›› ይለናል፡፡ እንዳልክ ግን መንፈስን ሁሉ እመኑ ይለናል፡፡ማቴ 24፡24 ላይ ሀሰተኛ ክርስቶሶች እንደሚነሱ ይነግረናል፡፡ሰዎች በአዕምሯቸው ሀሰተኛ ክርስቶስ ቢያስነሱ እንኳን አሜን በሉ ይለናል ዲያቆን ነኝ የሚለው እንደልክ፡፡2ኛ ቆሮ 11፡13-14 ላይ ‹‹እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና።ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።›› ሀሳዊያን የክርስቶስን ሃዋሪያ የሚመስሉት እነዚህ ሰዎች የሚሰብኩትም ክርስቶስ ሀሳዊ ነው፣ባይሆንማ ሀሳዊያን አይባሉም፡፡የእነሱን ሀሳዊ ክርስቶስ ስም ሲነሳ እንኳን አሜን በሉ ሳትጠይቁ ይለናል እንዳልካቸው ዘነበ፡፡

እየሱስ ጌታ ነው እያልኩ እኖራለሁ ይላል እንዳልክ፣መጽሃፍ ቅዱስ ደግሞ ‹‹ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።›› ይላል ትዕዛዛቱን የሚፈጽም እና ህይወቱን ከሚኖር ውጪ፡፡

[https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/887366125580438](https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/887366125580438)

[https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/870399150610469](https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/870399150610469)

[https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/478538026463252](https://www.facebook.com/endalkachew.zenebe.71/posts/478538026463252)

[https://www.facebook.com/photo/?fbid=5121802881258024&set=a.104410396330656](https://www.facebook.com/photo/?fbid=5121802881258024&set=a.104410396330656)

[https://www.facebook.com/watch/?v=2979223162222134](https://www.facebook.com/watch/?v=2979223162222134)


ለ500 ዓመታት ፕሮቴስታንት ቤት የስብከት ርዕስ ያልሆኑ ጥቅሶች
***

የአዳራሽ ውስጥ ነብያት፣ በሐሰት ላይ የተሾሙ ፓስተሮች መጽሐፍ ቅዱስ ሲገልጡ መመልከት የማይፈልጉት ጥቅሶች አሉ።

እነኝን ጥቅሶች ርእስ አድርገው ቢሰብኩ ቤታቸውን ከሥሩ የሚንዱ ቃላትን መጽሐፍ ቅዱስ ይዟልና።

እስኪ ጥቂት ቆንጥረን እንመልከት
***




ጌታን እንደ ግል አዳኟ አድርጋ የተቀበለችው የኖርዌ ቤተክርስቲያን በግብረ ሰዶማዊነት ላይ ላሳየችው ለዘብተኛ አቋም ይቅርታ ጭምር በመጠየቅ ግብረሰዶማዊነት ኃጢያት እንዳልሆነ ካወጀች ዓመታት አስቆጥራለች

ፀሎት ተደግሞላቸው፣ወንጌል ተሰብኮላቸው ፣ቅልጥ ካለ መዝሙር ጋር የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻነትን ይህቺ ቤተክርስቲያን ታስፈጽማለች።

እንደ Oslo pride የመሳሰሉ የግብረ ሰዶማዊነትን ዓለም አቀፍ ፌስቲቫሎችን የሚደረጉት በእዚህች ጌታን እንደ ግል አዳኝ አድርገው በተቀበለችው ሀገር ውስጥ ነው።

ባሻዬ... እኛን ቅድስት ቤተክርስቲያን ከስርዓት ጥምቀት በኃላ ስመ ክርስትና(ወልደ ገብርሔል፣ሐና ማርያም) እንደምትሰጠን ሁሉ የኖርዌ ቸርች ፆታቸው ለሚቀይሩ አባሏ መንፈስቅዱስ አቀብሎኛል ብላ በስርዓተ ጸሎት ስም ትሰጣለች።

የእዚህች ሀገር ዜጋዋ ከሚሞትበት 4 ገዳይ በሽታዎች መሃከል አንዱ የአእምሮ መታወክ(Mental illness ) እንደሆነ ብነግርህስ..

መጠጥን ላይ ያለውን የእዚህች ሀገርን አቋም ጠይቀኛ።
በዓለም 3ኛ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ሴት አልኮል ጠጪ ዜጎችን የያዘችው ይህቺው ሀገር ናት ብልህስ?

በነገርህ ላይ የእዚህች ሀገር እና የእዚህች ቤተክርስትያን የእጅ ሥራ የሆነው (Norewagian Church Aid ) የተባለ ድርጅት አፍሪካ ውስጥ ያለውን የፕሮቴ*ት የወንጌል አገልግሎት ይደግፋል።

ወደ ኢትዮጽያችን ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ ተቸንክሮ ኖሯል።

መጽሐፍ ቅዱስ

"“ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።ማቴ 7፥20" አይደል ያለን ።እንግዲህ ፍሬያቸው ይህን ይመስላል ።

ሐሳዊውን ወንጌል ዘርተህ አማናዊ የሆኑ የክርስቶስ ደቀመዝሙራትን ማፍራት አይቻልም። ኩርንችት በለስን ታፈራ ዘንድ አይቻላትም።


"ጌታን እንደ ግል አዳኟ" የተቀበለችው ኖርዌ ለምን ረከሰች?
*****

ወደ 5.5 ሚሊዬን ህዝብ የያዘችው በሰሜን አውሮፓ የምትገኝ ከኖርዲክ ሀገራት መሃከል አንዷ የሆነችውን ኖርዌን ታውቃታለህ?ካወክ እሰዬው

በ18ኛ መቶ ክፍለዘመን ላይ አጅሬዎቹ እንደሚሉት በኖርዌ ውስጥ > አሉ....አሉ ነው

ልክ እንደ አሁናዊ የእኛ ሀገር ሁኔታ በየመንገዱ፣በየገበያው ጌታን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ የሚቀበል ነፍስ ፍለጋ



እያሉ የሚኳትኑ ሰዎች ይርመሰመሱባት ነበር።

ቀስ በቀስ የእኝ ቡድኖች ዘመቻቸው ተሳካ። የኖርዌ ሉትርያን ቸርች በ1960 ዓ.ም ኖርዌን ተቆጣጠረች። የኖርዌ 96℅ ህዝቧ ጌታን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ መቀበል ቻለ።

ከእዛች ዘመን በኃላ ይህቺ ሀገር ከእግዚአብሔር ጋር ያላት መስተጋብር ገደል መግባት ጀመረ።

በ60 ዓመታት ውስጥ በእዚህች ሀገር ውስጥ ሃይማኖት የለሽ ትውልድ እየተበራከተ መጣ።

ጌታን የተቀበለውም ህዝብ ከ96 ወደ 68℅ በፍጥነት አሽቆለቆለ።

በኖርዌ ሉተርያን ቸርች በማህበረሰቡ ላይ ተጨባጭ ለውጥ አላመጣችም ያለው የኖርዌ መንግስት 632 አብያተክርስቲታናትን በሀራጅ ሸጦ ለደኃ እንዳከፋፈል በእዚህች ሀገር ታሪክ ውስጥ ውሳኔ ሲያስተላልፍ የቤተክርስቲያኒቷ ተከታዮች ሳይቀሩ ውሳኔውን አሜን ብለው ደግፈውት ነበር።

አሁን ላይ ከ68% ጌታን ከተቀበለው ህዝቧ መሃል 52.9%



በሚል እምነት ውስጥ ያለ በድን ስጋውን ብቻ አዳራሽ ውስጥ አስቀምጦ ይንቀሳቀሳል።

ከአጠቃላይ ህዝቧ 22℅ ብቻ በእግዚአብሔር የሚያምን ሲሆን ቀሪው አንድ ኃይል አለ በሚል አስተሳሰብ ውስጥ የተዘፈቀ ነው።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


✝✞✝ እንኩዋን አደረሰን ✝✞✝

"" ነገሠ : ቅዱስ ሚካኤል ነገሠ::
የጠላትን ምክር ፈጥኖ አፈረሠ:: ""

✝✞✝ አንተኑ ሚካኤል ለእስራኤል መና ዘአውረድከ:: ✝✞✝

☞እስራኤልን በበርሃ . . .
❀በደመና የመራህ::
✿መና ያወረድህ::
❀ክንፍህን የጋረድህ::
✿ውሃን ያፈለቅህ::
❀የብርሃን ምሰሶን ያቆምህ . . . ርሕሩሑ መልአክ ሚካኤል አንተ ነህን?!

☞ለኢትዮዽያም እንጂ ረዳት ነህ::

ዛሬም ረድኤትህ ፈጥኖ ይደረግልን




ሃሌ ሉያ (በ፭) ጸገየ ወይን ወፈርየ ሮማን ፥
ወፈርዪ ኲሉ ዕፀወ ገዳም ፥ ቀንሞስ ዕቊረ ማየ ልብን ፥
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ጸገዩ ጽጌያት ጸገዩ ደንጎላት ፥
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር። ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ፥ ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት፤
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር።
እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት ፥
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር፤
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍት ወለመድኃኒት።

✥ አመላለስ ዘመዝሙር፦

ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ /2/
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍት ወለመድኃኒት። /2/

፠ ማኅሌተ ጽጌ ተፈፀመ !፠

ይህን የተወደደ ማኅሌተ ጽጌ አስጀምሮ ላስፈፀመን ለእርሱ ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው። ሀገራችንን እና ሕዝቧን ይጠብቅልን።
አሜን!

#ጼጥሮስ


"ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር
የሰማይና የምድር ንግሥት ድንግል ማርያም የተወደደ ማኅሌተ ጽጌ ተፈፀመ ‼

🌺🌻🌼 ማኅሌተ ጽጌ ፮ኛ እና የመጨረሻ ሣምንት 🌺🌻🌼

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ፡ ሃሌ ሉያ ፡ ሃሌ ሉያ ፣
ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ ፡ ሃሌ ሉያ ፡ ሃሌ ሉያ ፣
ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡፡
በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ ፡ ሃሌ ሉያ (2)
አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ፡ ሃሌ ሉያ (2)
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡፡
ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡
ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡
ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኩሎ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡

ማንሻ፦

ስቡህ ወውዱስ ዘሣረረ ኩሎ ዓለመ በአሐቲ ቃል... /ጸንጽል/

ነግሥ

ሰላም ለአብ ገባሬ ኲሉ ዓለም፤
ለወልድ ሰላም ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤
ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም
ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም ፤
ለሰማእታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም፡፡

ዚቅ

ዛቲ ይእቲ ትንቢቶሙ ለነቢያት ፣
ስብከቶሙ ለሐዋርያት ፣
እሞሙ ለሰማዕት ፣
ወእኅቶሙ ለመላእክት፡፡

ማኅሌተ ጽጌ

ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃልቀ። ዘኢየኃልቅ ስብሐተ (ስብሐተኪ)እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ።
ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ።
ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ።
ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ።
(በእጅጉ የማያልቀውን ምስጋናሽን እያመሰገንኩሽ የጽጌረዳ ወራት ባለቀ ጊዜ በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም። ማርያም ተአምርሽ እንዳስረዳ ስምሽን መጥራት የወደቀውን ያነሣል፤ ኃጥኡን ጻድቅ ያደርጋል)

ወረብ

ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ/፪/
ዘኢየኃልቅ "ስብሐተ"/፪/ እንዘ እሴብሐኪ/፪/
(በእጅጉ የማያልቀውን ምስጋናሽን እያመሰገንኩሽ የጽጌረዳ ወራት ባለቀ ጊዜ በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም)

ዚቅ

እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤
ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤
ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ፤
ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤
ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል፤
መርዓተ አብ ወእመ በግዑ።
(የተቀመጣችሁ ተነሡ፤ ዝም ያላችሁ ተናገሩ፤ ማርያምን በምስጋና ቃል ጥሩ፤ የድንግልን ተአምር ትሰሙ ዘንድ ቆማችሁ አድምጡ በበጉ እናት በአብ ሙሽራ በቅድስት ድንግል ሥዕል ፊት ጸልዩ)

ወረብ ዘዚቅ

እለ ትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ
ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ/፪/
ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል
መርዓተ አብ ወእመ በግዑ/፪/

ማኅሌተ ጽጌ

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።
(በንጽሕናና በተአምር ዕለት ነጭም ቀይም አበባ የተባለ ልጅሽን ታቅፈሽው ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ርግቤ ከለቅሶ ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ፤ መልካማዬ ከደስተኛው ከገብርኤልና እንዳንቺ ርህሩህ ከኾነው ከሚካኤል ጋር ነዪ)

ወረብ

እንዘ ተሐቅፊዮ "ለሕፃንኪ"/፪/
ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/

ዚቅ

ይዌድስዋ ትጉሃን ፤ ይቄድስዋ ቅዱሳን ፤
ሰሎሞን ይቤላ ርግብየ ሠናይት፤
ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ፍጽምት፤
ዳዊትኒ ይቤላ ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ፡፡
(ትጉኃን ያመሰግኗታል፤ ቅዱሳን ይቀድሷታል፤ ሰሎሞን መልካሟ ርግቤ ይላታል፤ ጳውሎስም ፍጽምት ድንኳን ይላታል፤ ዳዊትም ልጄ ሆይ ስሚ በጆሮሽ አድምጪ ይላታል)

ማኅሌተ ጽጌ

ሶበ ዴገነኪ አርዌ በሊዓ ሕጻንኪ ዘኀለየ ፤
በዘትሠርሪ ገዳመ ወታፈጥኒ ጐይየ፤
አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ ጸገየ፤
ብእሲተ ሰማይ ማርያም ዘትለብሲ ፀሐየ፤
ተአምረኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ፡፡
(ልጅሽን መብላት ያሰበ አውሬ በተከተለሽ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ በምትበሪበት፤ መሸሽን በምታፈጥኚበት ገንዘብ ዮሐኒ ክንፍን እንዳበበ ክንፎችን ያበብሽ ፀሐይን የለበስሽ የሰማይ ብላቴና ማርያም ተአምርሽን ያየ ዮሐንስ ጻፈ)

ወረብ

አመ አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ/፪/
ተአምረኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ ዘርእየ ተአምረኪ/፪/

ዚቅ

በሊአ ህጻናት ሶበ ሀለየ ሄሮድስ አርዌ ሰማይ
ዘምስለ ዮሴፍ አረጋዊ ነገደት ቁስቋመ ናዛዚተ ኀዘን ወብካይ።

ማኅሌተ ጽጌ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ዚቅ

አክሊሎሙ ለሰማዕት
ተስፋ መነኮሳት፤
ሠያሚሆሙ ለካህናት፤
ነያ ጽዮን መድኃኒት።

ዐዲ ዚቅ

ከርካዕ ዘተተክለት በቤተ መቅደስ፤
መራኁቱ ለጴጥሮስ፤
አንቲ ውእቱ ደብተራ ስምዕ ዘጳውሎስ፤
አማን አክሊሉ ለጊዮርጊስ።

ማኅሌተ ጽጌ

ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ፤
አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር ፤
ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤
ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡

ወረብ

ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ፤
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት፡፡

ዚቅ

ሃሌ ሃሌ ሉያ
ሃሌ ሉያ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ
ይግበሩ ለኪ ኰሰኰሰ ወርቅ ፡፡

ሰቆቃወ ድንግል

ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤
ወኢትጐንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤
በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤
ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤
በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡

ወረብ

ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ፤
ወኢትጐንድዪ በግብጽ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፡፡

ዚቅ

ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት ፨
ወንርአይ ብኩ ሰላመ ፨
ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት ፨
እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር ፨
ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ፡፡

ወረብ

ሃሌ ሉያ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት፤
ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ፡፡

መዝሙር ዘሰንበት

ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበት፤
ወጸገወነ ዕረፍተ ከመ ንትፈሣሕ ኅቡረ፤
አዕጻዳተ ወይን ጸገዩ፤ ቀንሞስ ፈረየ፤
ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ ከመ ፩ እምእሉ።

ዓራራይ

በሰንበት እውራነ መርሐ፤
በሰንበት አጋንንተ አውጽአ፤
እለ ለምጽ አንጽሐ፤
ቃለ ማዕነቅ ተሰምዓ በምድርነ፤
ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት።

ዕዝል

መንክር ግብሩ ለ፩ እግዚአብሔር አብ ዘላዕለ ኲሉ፤
መንክር ግብሩ ለዘሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት፤
መንክር ግብሩ ለዘአሠርገዋ ለምድር በጽጌያት፤
መንክር ግብሩ ለዘገብረ ብርሃናተ ዓበይተ ባሕቲቱ።

ሰላም

ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ፤
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤ እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤
እንተ በሥሉስ ትትገመድ፤
ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት ሐረገ ወይን፤
ሲሳዮሙ ለቅዱሳን ሐረገ ወይን፤
ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፤
ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ።

✥ የዕለቱ የሰንበት መዝሙር፦





20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

1 834

obunachilar
Kanal statistikasi