ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ ለ37 ተከሳሾች ጥሪ እንዲያደርግ የታዘዘው EBC ጥሪ ስለማድረጉ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠ
ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ ለ 37 ተከሳሾች ጥሪ እንዲያደርግ ታዞ የነበው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን (EBC) ጥሪ ስለማድረጉ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ።
በደብረጽዮን ገ/ሚካኤልን የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ያልቀረቡት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልን፣ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) እና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 37 ተከሳሾች በኢትጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) ጥሪ እንዲደረግላቸው በመጋቢት 30 ቀን በነበረ የችሎት ቀጠሮ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር።
የዚህን የጥሪ ትዕዛዝ ውጤት ለመጠባበቅ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬ ተሰይሟል።
ይሁንና ትዕዛዙ የተሰጠው የኢትጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጥሪው ስለማስተላለፉ የሚገልጽ ማረጋገጫ አላቀረበም።
ሌላኛው ጥሪ እንዲያደርግ ታዞ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሲሆን፤ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሚያዚያ 23 ቀን 2014 በ133 ህትመቱ በቁጥር 81 በገጽ 12 የተከሳሾቹ ሥም በዝርዝር በመጥቀስ በጋዜጣ ጥሪ ማድረጉን የሚገልጽ ማረጋገጫ ቀርቧል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግንቦት 17 ቀን ጥሪ ስለማድረጉ የሚገልጽ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ አዟል።
ቀሪዎቹ በዚህ የክስ መዝገብ የተካተቱት ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ፣ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ፣ ዶሪ አስገዶም፣ ዶ/ር ሙለታ ይርጋን ጨምሮ 16 ተከሳሾች ችሎት የቀረቡ ሲሆን፣ በርሔ አሰፋ የተባሉ ተከሳሽ ግን በህክምና ቀጠሮ ምክንያት አለመቅረባቸው በተከሳሾቹ ተገልጿል። የተከሳሾቹ ጠበቆች ወንደሰን በቀለና ታደለ ገ/ሚካኤል በችሎት ተሰይመዋል።
በሌላ በኩል በዚሁ መዝገብ በሽብር ወንጀል የተከሰሱት ትራንስ ኢትዮጵያ፣ ሱር ኮንክትራክሽን እና መስፍን ኢንዱስትሪያል ሀ/የ/የግ/ማህበር ድርጅቶቹ የተከሰሱበት የሽብር ክስ ተነጥሎ በችሎት በንባብ ተሰምቷል።
እነዚህ ሦስቱ ድርጅቶች ለህውሃት ወታደራዊ ቡድን ምሽግ ቁፋሮ የተሽከርካሪ የነዳጅ እና የሰው ኃይል ድጋፍ በማድረግ በጥቅምት 24 ቀን 2013 በሰሜን ዕዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት እንዲደርስ በመተባበር በየደረጃው ተሳትፎ አላቸው ሲል ዓቃቢህግ ያቀረበባቸውን የሽብር ወንጀል ክስ በዝርዝር ተነቧል።
ጠበቆቹ የተነበበው ክሱ ግልጽ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ከአንድ ወር በፊት 17 ተከሳሾችን በሚመለከት ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ላይ የድርጅቶችን ጉዳይ ያካተቱ መሆናቸውን የገለጹት ጠበቆቹ፤ ነጥለው የድርጅቶቹን ለብቻ የክስ መቃወሚያ ለማቅረብ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
በፍርድ ቤቱ በኩል ጠበቆቹ የክስ መቃወሚያ ለማዘጋጀት የአንድ ሳምንት ጊዜ ቢሰጣቸው እንደማበቃቸው እና እንደማይበቃቸው ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ጠበቆቹ ሱር ኮንስትራክሽን ዋናው መስሪያ ቤቱን መቋለ ማዛወሩን በመጠቆም ከድርጅቶቹ ማስረጃዎችን አሰባስበው ለማቅረብ አንድ ሳምንት እንደማይበቃቸው በመግለጽ አንድ ወር እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱም በሦስቱ ድርጅቾች ላይ በቀረበው የሽብር ክስ ላይ ጠበቆች የክስ መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ለሰኔ 13ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በሌላ በኩል ከዚህ በፊት በነበረ ቀጠሮ በፌደራል ፖሊስ በምርመራ የተያዘባቸው ሞባይላቸው በተወካያቸው በኩል እንዲሰጣቸው ታዞላቸው የነበሩት በትግራይ ክልል በተከናወነ ህገወጥ ምርጫ ተሳትፈዋል ተብለው የተከሰሱት የአሲንባ ዲሞክራሲ ፖርቲ ሊቀመንበር የነበሩት ዶሪ አስገዶም ሥልካቸውን ፌደራል ፖሊስ ለራሳቸው እንጂ ለወካያቸው አካል አልሰጥም የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ገልጸው፤ በአጃቢ ሄጄ እንድቀበል ይታዘዝልኝ ሲሉ በድጋሚ አቤቱታ አቅርበዋል።
ሌላኛው 43ኛ ተከሳሽ ተክላይ አብርሐ፤ ከዚህ በፊት በኦሮሚያ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ በአጃቢ ሄደው መንጃ ፍቃድ ለማሳደስ የተፈቀደላቸውና የሄዱ ቢሆንም፤ ኦሮሚያ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ግን የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በቀጥታ ለኔ ካልደረሰኝ ማደስ አልችልም የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው በመግለጽ በቀጥታ ለኦሮሚያ መንገድ ትራንስፖርት ለቢሮው እንዲታዘዝላቸው አቤቱታ አቅርበዋል።
አቤቱታው የደረሰው ፍርድ ቤቱ በአቤቱታው ላይ ትዛዝ ለመስጠት እንዲያስችል አቤቱታ ያቀረቡት ተከሳሾች ግንቦት 17 ቀን ችሎት ቀርበው በቅድሚያ ማረሚያ ቤት አስተያየት እንዲሰጥበት ማዘዙን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።
በዚህ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የክስ መዝገብ ተካተው የነበሩት ስብሐት ነጋ፣ ቅዱሳን ነጋ እና ሙሉ ገ/እግዚአብሔርን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች በዕድሜ መግፋትና በህመም ምክንያት ክሳቸው መቋረጡ ይታወሳል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n