•ወዱእ ያለው መስሎት ያለ ውዱእ የሰገደ ሰው ሶላቱን እንደገና መስገድ አለበት። ያለ ውዱእ ሶላት የለምና። ያስታወሰው ወቅት ካለፈ ቢሆን እንኳ ሶላቱን መመለስ አለበት።
ኢማሙ ረስቶ ያለ ውዱእ ካሰገደስ? የተከታዮቹ ሶላት ይበላሻል?
* ሶላቱ ሳይጠናቅቅ ካስታወሰ መቀጠል የለበትም። ይልቁንም ሌላ ሰው ተክቶ ይወጣል። የተተካው ሰው ከመጀመሪያ መጀመር ሳይጠበቅበት የቀረውን ያሰግዳል።
* ኢማሙ ውዱእ እንዳልነበረው ያስታወሰው ሶላቱን ካጠናቀቀ በኋላ ከሆነ ግን የተከታዮቹ ሶላት ትክክል ስለሆነ መመለስ (ዳግም መስገድ) አይጠበቅባቸውም። ይህንን የኢብኑ ዑሠይሚን ፈትዋ ማየት ትችላላችሁ። https://binothaimeen.net/content/7883
•ኹፍ ወይም ካልሲ በጦሀራ የለበሰ መስሎት አብሶ የሰገደ ሰው ኋላ ላይ በጦሀራ ሆኖ እንዳልለበሰው ካስታወሰ ውዱኡንም ሶላቱንም መመለስ አለበት። ማለትም እንደገና ውዱእ አድርጎ መስገድ ይኖርበታል።