Suleiman Ibnu Jabir(Channal) dan repost
ፎቶ ማንሳትን በተመለከተ!
=~=~=~=~=~=~=~=
*
ፎቶ ሐራም እንደሆነ በርካታ ማስረጃዎች መጥተዋል። #የብዙሃኑ_የሱንና ዑለማዎች አቋምም ይሄንኑ የሚያፀና ነው። አስገዳጅ ለሆነ ጉዳይ ሲሆን ግን ሁሉም ይፈቅዱታል። አስገዳጅ ደረጃ ባይደርስም ጥቅም ከኖረው የፈቀዱትም በተጨባጭ አሉ።
•
እንደዚህ ሲባል ደግሞ መነሳትን ሐላል አድርጎ መመልከት ከባድ ጥፋት ነው። በመሰረቱ ያለ በቂ ምክንያት ፎቶ ማንሳትም ይሁን መነሳት በጥብቅ #የተከለከለ ነው! ከከባባድ ወንጀሎችም መካከል አንዱ ነው።
ሳንገደድና ለመሰረታዊ ነገሮች በጥብቅ ሳያስፈልግ ፎቶ መነሳት ክልክል ከመሆኑ ጋር እንዲሁ ያለ ምክንያት ሚዲያዎች ላይ ለመለጠፍ መነሳት ይቻላል ማለት በዚህ ዙሪያ የተነገሩ በርካታ ነቢያዊ ሐዲሦችን ትርጉም ማሳጣት ነው የሚሆነው።
*
እጅግ አሳሳቢ የሚሆነው ደግሞ ይህ ነገር በሴቶች ሲደረግ ማየት ነው። በጣም ያሳፍራል!። ሴትን ማየት የዓይን ዝሙት በመሆኑ ሌሎችን ለወንጀል ይገፋፋል። ብዙዎች በትዳር አጋራቸው እንዳይደሰቱም ያደርጋል።
•
በተለይ ውበታቸውን ለማሳየት ብለው ተውበው ፎቶ የሚለቁ ሲኖሩ! ለዚህና ለመሰል መጥፎ አላማ ፎቶን የሚለቁ (ምድር ላይ መጥፎ ነገር እንዲስፋፋ በመውደድ ወንጀል አላህ ዘንድ ልዩ ምርመራና አሳማሚ ቃጣት እንደሚጠብቃቸው ቁርኣን ላይ ተነግሯል) ችግሩ በዚህ ብቻም አያበቃም፣ ሚዲያ ላይ ፎቶዋን የምትለጥፍ ሴት አላህን የማይፈሩ ሰዎች ፎቶዋን ከዛ ላይ አንስተው በተለያየ መልኩ አቀናብረው ክብሯ ላይም ችግር ሊያደርሱባት ይችላል።
•
ፎቶ ግራፍን ሐዲሡ አይመለከተውም የሚለው አስተያየት ተቀባይነት የሌለው ፎቶ/ምስል የተከለከለበትን ዓላማም የዘነጋ አስተያየት ነው። ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም በሐዲሳቸው እንዲህ ያሉበትን ማለቴ ነው፦
"በዱንያ ላይ ስእልን #የሳለ አኼራ ላይ አላህ (ሩህ መንፋት አቅሙ ባይኖረውም) #እንዲነፋበት ያስገድደዋል። ነገር ግን አይችልም።
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]
•
በሌላም ዘገባ ላይም እንዲሁ፦
"ሰዓሊ ሁሉ #የእሳት ነው። በሳላቸው ስእሎች ልክ ነፍስ ተደርጎባቸው ጀሐነም ውስጥ ይቀጡታል።"
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]
•
ሶሐቢዩ ኢብኑ አባስም እንዲህ ብሏል፦ "ስዕል መሳልህ ካልቀረ ዛፍ እና ነፍስ የሌላቸውን ሳል!"
*
በጣም የሚገርመው ነገር አብዛኛው ሰው የማያውቀው አንድ እውነታ መኖሩ ነው። "በፎቶ ላይ ሲህር!"። ይህን ነገር አለማወቃችን ነው እንጂ ከግንዛቤያችን እጥረት የተነሳ ከሐዲሱ ይበልጥ ሲህርን ፈርተን ፎቶ ባለቀቅን ነበር!። ለማንኛውም ይህ በግምት የምናገረው ሳይሆን በተጨባጭ ያለ ነገር ነው። ይህን አውቀን ቢያንስ እንቆጠብ ዘንድ ምክሬ ነው!
•
ፎቶግራፍን በተመለከተ ከዑለማዎች በኩል በጣም ብዙ ተብሏል። ለመታወቂያ ፣ለመንጃ ፍቃድ እና ለሌሎች አስገዳጅ ነገራቶች ካልሆነ በስተቀር ሩህ ያላቸውን አካላቶች (ሰው እና እንስሳትን) በእጅ መሳልም ሆነ #በካሜራ ማንሳትን እና ለማስታወሻነት ማስቀመጥ የተከለከለ ነው የሚለውን ሀሳብ የደገፉት አብዛኛውን ናቸው።
*
ከነዚህ ውስጥም ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን [ፈትሑ ዚል ጀላሊ ወል ኢክራም፣ ፈታዊ መናሩል ኢስላም፣ ሸርሁል ሙምቲዕ] ኩቱቦቻቸው ላይ በሰፊው ዳሰዉታል። ለምሳሌ ፈትሑ ዚል ጀላሊ ወልኢክራም: 15/329 ላይ
•
"ማንም ቢሆን ማንንም ያለ ፈቃዱ ፎቶ ሊያነሳ አይፈቅድለትም። ሌላው ቀርቶ ሰውየው ፎቶ ማንሳት ይፈቀዳል የሚል እንኳን ቢሆን ያለፈቃዱ ሊያነሳው አይፈቀድም። ፎቶ መነሳትን የሚጠላ ከሆነ ደግሞ የባሰ ነው።" የሚለው አቋማቸውን አስቀምጠዋል። ሌሎቹም ላይ እንደዚሁ አቋማቸውን በግልጽ አስፍረዋል።
||
By Abu Hanifa #al_assery
#መልዕክቱን_ያስተላልፉ!!
https://telegram.me/Daru_Sunnah