#ብርሃን_ባንክ
“የሥነ-ምግባር አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት …”
በሚል ርዕስ ለብርሃን ባንክ አ/ማ አመራሮች በፌደራል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አሰልጣኝ ዶር/ በረከት ሰለሞን ስልጠና ተሰጠ፡፡
***********************
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የባንኩ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን አሰፋ ሲሆኑ በንግግራቸውም ወቅት ‘’ኮሚሽኑ ከተጣለበት ከፍተኛ የመንግስትና የህዝብ አደራ መነሻነት በሃገራችን ጉልህ የሚባል ለውጥ ለማምጣት ተገቢውን እንቅስቃሴ የሚያደርግ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው ባንኩም ለዚህ አላማ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተሰጠ ሲሆን ፤ ስለሙስና ምንነት እና አይነቶች እንዲሁም ባንኮች እና ተመሳሳይ ተቋማት ለሙስና ያላቸው ተጋላጭነት ፣ እና እንዴት ሙስናን መከላከል እንደሚቻል ሰፊ ገለፃ ተደርጓል፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ የባንኩ ቺፍ እስቴት ማኔጅመንትና ማርኬቲንግ ኦፊሰር አቶ ቢኒያም መስፍን ንግግር ያደረጉ ሲሆን በመጀመሪያ ኮሚሽኑ ከተሰጠው ሃገራዊ ተልዕኮ አንጻር ይህንን መሰል ሥልጠናዎችን ማዘጋጀቱ በጣም ተገቢና ወቅታዊ እንደሆነ ገልጸው፤ ብርሃን ባንክ አ/ማ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የሚጋብዙ አሰራሮችን በመፈተሽ ጊዜው በሚፈቅደው የቴክኖሎጂ ግብዓቶች በመጠቀም ስራዎችን አጠንክሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!
#Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia