ካልቨሪ ቻሪቲ: Calvary Charity AGAPE KINDERGARTEN ✟ ✞ ✟
እንደምን ሰነበታችሁ የካልቨሪ ቤተሰቦች በያላችሁበት የእግዚአብሔር አብ ሰላም የክርስቶስ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አብርሆት ይሁንላችሁ።
ካልቨሪ የወንጌል አገልግሎት ለብዙዎች የምስራቹን ቃል በጎዳና፣ እንዲሁም በsocial median አና በተለያዩ መንገዶች የሚያደረስ ከመሆኑም ባለፈ ሁለንተናዊ አገልግሎትን ባቀፈ መልኩ የተለያዩ የእርዳታ ሥራዎችን በመስራት ላይ ቆይቷል። አቅመ ደካማ ከሆኑት ቤተሰቦች ከ80 በላይ ህፃናት ልጆች የመዋዕለ ህፃናት(KG) ትምህርት እድል ባሉበት ስፍራ (መንደር) እንዲያገኙ ባሰባሰብናቸው አስፈላጊ የትምህርት ቁሳቁስ
(ደብተር ፤ እርሳስ... ወዘተ) ጋር ሁለተኛውን ሴሚስተር ማስጀመራችንን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።
ስለሆነም ለዚህ መልካም ስራ የተባበራችሁ ሁላችሁም ስለመልካም ልባችሁ በወረዳውና በአከባቢው ነዋሪ እንዲሁም በካልቨሪ ሚኒስትሪ ስም ምስጋና እያቀረብን ይህ መልካምነት ሳይቋረጥ ቀጥሎም ለሚያስፈልጉት ሰፊ ሥራዎች የበኩላችሁን እድታደርጉ እናሳስባለን።
----------------------------------
ለበለጠ መረጃ 👇👇
-Addis AbabaBiruk
+251910058808
-Hawassa
Amanuel
+251989929052 ----------------------------------
(መጽሐፈ ምሳሌ 19:17)
ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።
CALVARY HOLISTIC MINISTRIES@calvarygospelministry