በወቅታዊው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ 7 ነጥቦች!
1) በትናንትናው ዕለት የተቋቋመው መጅሊስ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ስኬት እንጂ የተወሰኑ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ውጤት አይደለም።
ሌላ ቢቀር " ያ አላህ የሙስሊሞችን ጉዳይ አንተ አስተካክለው" ብሎ ዱአ ያደረገ ስለ መጅሊስ ምንም የማያውቅ እልም ያለ ገጠር ውስጥ ያለ ወንድም ዱአ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።
2) አሸናፊ እና ተሸናፊ የለም
ሙስሊሞች የተሻለ የመሰላቸውን መንገድ ይዘው ሊለፉ ሊደክሙ ይችላሉ [ ሸር አስቦ የሚንቀሳቀውን አላህ የውስጡን ያውቀዋል፣ የስራውንም ይሰጠዋል] ግን በመጨረሻ ላይ ድል ሲገኝ በዛንኛው መንገድ የለፋው ሰው ተሸናፊ፣ በዚህኛው መንገድ የለፋው አሸናፊ ብለን የምንሄድበት አይደለም። አላህ የተሻለውን ይመርጣል። ስለዚህ አንዱ ፎክሩ አንዱ አንገቱን የሚደፋበት አይደለም። ሁሉም አላህን ያመስግን፣ በኒዕማውም ይደሰት።
3) ደስታው ልክ ይኑረው
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለዘመናት የተመኙት ፣ የለፉለት፣ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የሚወክል ተቋም፣ የማይደሰት አይኖርም [ኸይር የተጋረደበት ሲቀር]
ይሁንና የተቋሙ መቋቋም ትልቅ ውጤት ሆኖ የመጨረሻ ግብ ግን አይደለም፣ ባለመሆኑን ደስታውን በለከቱ አድርጎ በቀጣይ ላሉ የቤት ስራዎች ሁሉም የአቅሙን ያበርክት [ለዚህም አዲሱ መጅሊስ ግብአቶችን ከሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫዎች የሚቀበልበት ፕላትፎርም ያዘጋጅ]
4) ተቋሙ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን እንጂ ኢስላምን አይወክልም
መጅሊሱ የኢስላም ተወካይ ሳይሆን፣ ሙስሊሞችን ከዚያም አልፎ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የሚወክል ተቋም በመሆኑ ኢስላም የሞላና አዲስ ጭማሩን የማይፈልግ ስለሆነ ስለ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ 24/7 ሊሰራ ይገባል። [በቢላሽ የባከኑ በርካታ ጊዜዎች በመኖራቸው በተቻለ መጠን ሊካካሱ እንደሚገባ ልብ ይሏል]
5) ተቋሙ ሙስሊሙ ለሀገሩ እድገት ይበልጥ አበርክቶ የሚሰጥበትን መንገድ ይቀይስ
6) ከቀድሞው መጅሊስ ያሉ መልካም ነገሮችን እንዳሉ መውሰድ፣ ስህተቶችን ደግሞ ዳግም ለላመሳሳት አርሞ፣ ተጫማሪ ተግባራትን በማከል መቀጠል
7) አመስጋኝ እንሁን!
ለዚህ ተቋም በእግሩ መቆም ከአላህ በታች የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ብዙ መስዋእትነት የከፈሉ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይሁንና በአዋጅ እንዲነገግ ከማድረግ አንስቶ ሂደቶችን ከመገፍ አንፃር የኢትዮጵያ መንግስትን በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን አላመመስገን ንፉግነት ነው።
ሀምሌ 12/2014
ዳጉ ሚዲያ ኔትዎርክ
አስተያየት ይስጡበት
Dagu media network
@dagumedianet