የምግብ በሆድ ውስጥ ያለመፈጨት ችግር (ኢንዳይጄስሺን)
ይሄ ምግብ አልተስማማኝም ወይም ይሄ ምግብ ስብላ አይመቸኝም የሚሉ አባባሎችን ከአንዳንድ ሰዎች መስማት የተለመደ ነው፡፡ ለመሆኑ የተመገቡት ምግብ ያልተስማማዎት መሆኑን እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ?
የተመገቡት ምግብ ምንም ምቾት ከነሳዎት ችግሩ የምግብ በሆድ ውስጥ ያለመፈጨት ችግር (ኢንዳይጄስሺን) በመሆኑ እነዚህን መልክቶች ልብ ይበሉ
1. የላይኛው ሆድ ሕመም ይሰማዎታል
2. ግሳት (ጋዝ ወይም አየር በአፎ ይወጣል)
3. ሆዶት በጋዝ ወይም በአየር ይነፋል
4. የደረት ሕመም
5. ማለሽለሽና አልፎ አልፎ ትውኪያ ሊኖር ይችላል
6. ጥቂት እንደተመገቡ የመጥገብ ስሜት መኖር
7. አንዳንድ ጊዜ ሊያስቀምጦት ይችላል
8. የራስ ሕመም ሊኖሮት ይችላል
9. የመፍዘዝ ስሜት ሊታይብዎት ይችላል
ምግብ በሆድ ውስጥ እንዳይፈጭ የሚያደርጉ ምክንያቶች
1. ብዙ መብላት
2. በደንብ ሊፈጭ የማይችል ምግብ መብላት
3. ያለ ጊዜ መብላት
4. ቶሎቶሎ መጉረስና በፍጥነት ፈሳሽ ነገር መውሰድ
5. በደንብ አኝኮ አለመዋጥ
6. የሚስማማን ምግብ በሚገባና በተወሰነ ጊዜ በመጠኑ ያለመብላት
7. አንዳንድ ሰዎች ሌሎች የማያስቸግራቸውን ምግብ እነሱ ስለበሉ ሊያስቸግራቸው ይችላል፡፡
መፍትሔውስ
1. የሕይወት ዘይቤ ለውጥ፡- ዝግ ብሎ መብላትና በትንሽ መጠን መብላት
2. አልኮልና ካፊን ያለባቸውን መጠጦች ቡናና ሻይን የመሰሉትን ከመውሰድ ማስወገድ
3. ሲጋራ ማጨስ ማቆም
4. አባባሽ የሆኑ ምግቦችን በተለይ ቅመም የበዛባቸውና በቀላሉ የማይፈጩ ምግቦችን ያስወግዱ
5. በሳምንት አንድ ቀን ፍራፍሬ መመገብ
6. በየቀኑ ከተቻለ ሦስት ብርጭቆ አሬራ(ወተት) መጠጣት
7. ጸረ-አሲድና አሲድ ገዳቢ መድኃኒቶች
8. አንድ የሾርባ ማንኪያ ሙሉ የማግኔዚያ ወተትና አንድ የሻይ ማንኪያ ግማሽ ሱዲዬም ባይ ካርቦኔት በአንድ ብርጭቆ ለብ ባለ ውሃ ውስጥ በጥብጦ በግማሽ በግማሽ ሰዓት የተበጠበጠውን መድኃኒት እሩብ መጠጣት ነው፡፡(በአንድ ብርጭቆ የተበጠበጠው መድኃኒት ለአራት ጊዜ ይሆናል ማለት ነው) መድኃኒቱ በትውኪያ የወጣ እንደሆነ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ጨምሮ መጠጣት ነው፡፡ መድኃኒቱ ካለቀ በኃላ አንድ ሰዓት ቆይቶ አንድ የሾርባ ማንኪያ ሙሉ የማግኔዚያ ወተት መጠጣትና በሁለት ሰዓት ውስጥ ጨምሮ መጠጣት ነው፡፡ከዚያ በኃላ ለሃያ አራት ሰዓት ያህል ተፈልቶ ከቀዘቀዝ ወይም ከታሸገ የፕላስቲክ ውሃ በስተቀር ሌላ ነገር አለመውሰድ ይመከራል፡፡
9. የሕመሙን ለማስታገስ እርጥበት ባለው ጨርቅ ወይም መቀነት ሆድን ማታ ማታ አስሮ መተኛት
መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ!
እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!
ምስጋናችን ከልብ ነው!
@EthioBini @EthioBini