Muktar Hussen የሱና ወዳጆች ቻናል ቡታጅራ ከተማ ከስልጤ አጠገብ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


➾ቅድሚያ ለተዉሒድ ለአላህ መብት ለሆነው/ወደዚህ ምድር ለምን እንደመጣን እንወቅ/ከሺርክ እናስጠንቅቅ ከአደንዛዥና ከሀራም ነገሮች እንረቅ ለእውቀት ቦታ እንስጥ እናንብብ እንወቅ እውቀት ከፍ ያደርጋል ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት 09253 44831 ሙክታር ሁሴን✅

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri








አደራ አደራ አደራ መልእክቴን አድርሱልኝ
==========================
ሙስሊም እህት ወንድሞቼ ለአረፋ ወደቤተሰቦቻችሁ በምትሄዱ ሰአት አንድ አላህ የሚወደውን ተግባር መፈፀም አትርሱ በትንሽ ብር ብዙ ጥቅም አግኙ።

እንደሚታወቀው በሀገራችን በተለየዩ ቦታዎች የሺርክ ተግባራት ይፈፀማል{ይሰራል} ወደ ሀገር ቤት ስትሄዱ ወይም ወደ ቤተሰቦቻችሁ በምትሄዱ ሰአት ለቤተሰብ {1,2,3 }ወይም ከዛ በላይ Memory በመግዛት ሀዲሶችን በመጫን ይዛችሁ ሂዱ ከቤተሰብ አልፎ ለአካባቢው ማህበረሰብ ይበቃል።

👉ስለ ተዉሒድ የበላይነት የሚነገር የኡስታዞችን ዳዕዋ በMemory በመጫን !!

👉የሺርክ አስከፊነትን የሚነገር የኡስታዞችን ደዕዋ በmemory በማስጨን ይዛችሁ ሂዱ አደራ አደራ አደራ!

እናንተን የሚያህል ልጅ ወልደው አባት እናታችሁ እንዴት እናንተ እያላችሁ በሺርክ እየኖሩ ሺርክ እየሰሩ ይሙቱ ??

መቸም አባት እናቱ ቤተሰቡ ጀሃነም እንዲገቡበት የሚፈልግ ልጅ የሚኖር አይመስለኝም የግል ፀብ ከሌላቸው በስተቀር ሺርክ ደግሞ ዘለአለም ጀሃነም ዉስጥ እንዲቆዩ የሚያደረግ አደገኛ ተግባር ነው ።

👉በሙዚቃ ፋንታ ሀዲስ፣ቁርአን የመሳሰሉትን ለእስልምና የሚጠቅሙ ነገሮችን ይዛችሁ በመሄድ {{አላህና መልእክተኛው ሰለላሁ አለሂ ወሰላም}}የሚወዱትን ተግባር በመፈፀም ተደሰቱ ።

👉አላህን እያስከፉ ደስታ በጭራሽ የለም የዉስጥ እርካታ የለም እባካችሁ ተዉሒድ ምን እንደሆነ ሺርክ ምን እንደሆነ ቤተሰቦቻችን ማወቅ አለባቸው እኛ ልጆቻቸው ስንመክራቸዉ የበለጠ ደስ ይላቸዋል ይገባቸዋል ቀለል ይላቸዋል።

እኛም እናንተም መልካም ስራ ሰርተው ጀነት ከሚገቡት አላህ ያድርገን ከቤተሰብ ሀቅ ይጠብቀን ተዉሒድን የበላይ ሺርክን የበታች የምናደርግ አላህ ያድርገን ።

መልእክቱን አደራ አደራ አደራ ሼር ሼር ሼር  አድርጉት

ወንድማችሁ ሙክታር ከቡታጅራ ከተማ ከስልጢ አጠገብ!
||
⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇
https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen




ዒድኩም ሙባረክ
እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፊጥር በዐል በሰላም አደረሳችሁ


📮 ሰበር ዜና ሰበር ዜና ነገ ፆም.....
📮 عاجل عاجل عاجل...

🔭 تعذر رؤية هلال شوال في تمير ، والأربعاء أول أيام عيد الفطر بالسعودية.

📮 ሱዑዲ ላይ ጨረቃ ስላልታየች አላህ ካለ ነገ 30ኛው የረመዷን ፆም ይሆናል።


ቁርአንን በሙዚቃ አድርጎ የመጨፈር ድፍረት ከየት መጣ❓

ልባችን ደርቆ በትቢት ተወጥሮ
ቁርአንና ሀዲስን ወደዚያ ወርውሮ
በትንሹ ጭንቅላት ኩራት ተጨምሮ
አቤት አወዳደቅ በተንኮል ተወጥሮ።

ከዚህ  በፊት እህት ወንድሞቻችን ከሙዚቃ የማይተናነስ ነሺዳና መንዙማ በሚሉበት ግዜ ተዉ አላህን ፍሩ ማለት ሲገባ ማሸ አላህ በርቱቱቱቱቱ!!! ሲባል ነበር !!

እሀዉ ዛሬ በተከበረው በአላህ ቃል በሆነው ቁርአን ሲከፈን፣ ሲጨንቀን፣ስንደሰት ለሁሉም ነገር መፍትሔ ሆኖ የሚያገለግለንን የህይወት መመሪያ የሆነው የጌታችንን ቃል
#በራፕፕፕፕ ተደርጎ መጣላችሁ።

👉ዉሻ በቀደደው ጅብ ይመላለሳል!!
የኛው ሙስሊሞች ናቸው የተባሉት
#በሰለዋት እየጨፈሩ አይተናል ሴቱ ወንዱ አንድላይ ሆኖ ለዛውም መስጂድ ዉስጥ ጥጋበችን እስከዚህ ደርሶአል።

አላህን ፍሪ በየት ለዛች እህትሽ
አስታዉሺ በየት ጀሃናም አለልሽ
ምንም አይጠቅምሽ በትቢት መወጠርሽ።

አላህን ፍራ በለው ያንን ወንድምህን
በቁርአንና በሀዲስ የሚቀልደዉን
ቁርአንን በሙዚቃ አድርጎ የሚጫዋተውን።

ስለዚህ ወደጆቼ፦
==========
ቁርአን የአይን ማረፊያችን እንጂ የማንም ዱርዬ ቲክቶክ Fb YouTube ማሞቂያ የጨዋታ መስሪያ አይደለም የቻላችሁት ጥራት አድርጉ።

ወላሂ ቢላሂ
||
አላህ አየያዙ  የከፋ ነው ባላሰብነው ሰአት ይዘናል!!
👉 ሀቅን መደበቅ እናቁም  ለእውነት እንኑር እስልምና ህይወታችን ነው በህይታችን ማንም እንዲጫወት መፍቀድ የለብንም  አላህን ፈርታን በአላህና በነብዩ ስም የሚቀልዱ ሰዎችን ከመታገል ወደኃላ ማለት የለብንም ።

እስልምና ዉብ ነው የዉቦች ዉበት
እስልምና ፍቅር ነው የሰላም ሰገነት
በቁርአን በሀዲስ ከመጡ  እሱን ለማንቋሸሽ
በትቢት በጥጋብ የአላህን ቃል ለማንቋሸሽ
በአላህ ይሁንብህ አትፍራ ወደኃላ አትሽሽ
ማንም አይቻልም እስልምናን ማንቋሸሽ


👉እህት ወንድሞቼ የአላህ ዲን መጫወቻ አይደለም ማንም እየተነሳ የሚጫወትበት በያላችሁበት መታገል አለባችሁ በዚህ በወጣትነታችን ለእስልምና የሚጠቅም ቢያንስ አንድ መልካም ተግባር መፈፀም አለብን ።

አደራ አደራ
========
||
እስልምናን ጠቅማን እንጂ አድክማን ወደ አኼራ መሄድ የለብንም  በአላህ ፊት ተጠያቂ መሆናች አይቀሬ ነው ።
እኛ ዝም በማለታችን ነው በሙስሊሞች ሰይቀር በቁርአን መጫወት የጀመሩት አስቡት ምን ያህል ልባችን እንደደረቀ።

ወላሂ የአላህ ትግስት ይገርማል
እንደኛ ተንኮል ትቢት ቢሆንማ እሳት ይዘንባል ብዬ አስባለሁ ትግስቱ የአላህ ይገርማል።

አላህ ትክክለኛውን መንገድ ይምራን
ተንኮለኞችን ተገቢውን ቅጠት ይስጣቸው
አላህ አንድነታችንን ጠንካራ ያድርግልን መለያየት የጥፋልን መልካም ስራ ሰርተው ጀነት ከሚገቡት ያድርገን አሚን አሚን።

ተፃፈ በወንድማችሁ
Muktarr Hussen Butijra
|||
የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen




ኢትዮጵያ የደም ምድር
≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡

ንፁሃን አለቁ ድሆች ተጨነቁ
መስጂዶች ፋረሱ ደካሞች ተጨነቁ
ህፃናት አለቀሱ አባት እናታቸው ተነጠቁ
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ክቡር የሰው ህይወት ክቡር መስጂደችን
አትንኩ በማለት አፈሰሱት በባዶ ደማችንን
ዝም አትበል ጌታችን አላህ ለንፁ ደማችን
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ለፖለቲካ ብለው ለጥንብ ዘረኝነት
ኢትዮጵያ በምትባል ሀገር ስንቱ አለቀበት
ስንቱ ሞተበት ስንቱ ደሙ ፈሰሰበት
የስንቱ አጥንት ተሰብሮ ደማ ከልብ ሆናበት
አላህ ጌታችን ዘወር ብለህ ባክህ ተመልከተት
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የህፃናት እንባ የተበዳዮች  በደል
በመንገድ ተጥለው እንደ ረገፈ ቅጠል
እንባቸው ይወርዳል ደማቸው ይፈሳል
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እባክህ ጌታዬ አንተው እርዳቸው
አንተው አዋቂህ ነህ እባክህ እርዳቸው

ለጥጋበኞች መቀጣጫ አንተው አምጣለቸዉ
መስጂዶች አለቁ ንፁሃን አለቁ ፍትህ አምጣለቸዉ
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
👆 ተፃፈ በወንድማቹ ሙክታር ሁሴን
የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ
⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇
https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen
╚══════════════════╝




ቃላቶች አጠሩኝ ምን ብዬ ልነገር
የእስልምና ጀግና መሆን አሳይተሃል በተግባር
ሀቂቃ ገብቶሃል የላ ኢላህ ኢላ አላህ ምስጥር
ሞተህም ከሆነ አላህ ያድርግህ ከነብዩ መንደር

by Muktar Hussen
|||
https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen






መስጅዴን__አትንካ
≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡

ስምህ ብልፅግና ተግባርህ ብልግና
ስምህ ብልፅግና ተግባርህ እርኩስና
መስጅድ ማፍረስ  ነው የአንተ ህልውና ::
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በል እጅህን አንሳ አትድረስ ከመስጅዴ:
የአንተ ድድብና አይተነዋል አዉቀናዋል አንዴ:
ከተማው የሚያምረው ደግሞ ከመስጅድ ነው:
የምትሰራው ስራ በጣም ቆሻሻ ነው:
መስጂድ የሌለበት ከተማ ምኑ ከተማ ነው ::
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

መስጅዴን አትንካ ህይወቴ ነው ደስታዬ:
የዚህ አለም ደስታ የሀዘን ማስረሻዬ:
ድንቋ  ዉብ መስጅድ የደስታ ጎጆዬ:
የዉሸት ለቅሶ ይዘህ አትበለኝ እዬዬ::
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ኢስላምን ለመጥፋት በጭራሽ አታስብ:
መቼም አይጠፋህም የተንኮልህ ሀሳብ :
ኢስላም እፍፍ ብለህ የሚጠፋ አይደለም :
የኢስላም ጠላት ሞክረዋል የሚሆን አይደለም::
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በል እጅህን አንሳ አትንካ መስጅዴን:
ብዙ አልነገር አልጨርሰዉ የሆዴን:
እዛው ተጨማለቅ ባለመድከዉ ቦታ:
መስጅዴን  አትንካ ቀይር የክፋትህን ቦታ:
  በነጃሰዉ እጅህ  ንፁህ መስጅድ አትንካ:
በቆሻሻዉ እጅህ  ንፁሁ  መስገጃ አትንካ።
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
👆 ተፃፈ በወንድማቹ ሙክታር ሁሴን
የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ
⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇
https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen
╚══════════════════╝






አዲስ ግጥም ሼር ሼር
ኦሮሚያ ዝም አትበይ
≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
መስጂዶችሽ እየፈረሱ ዝምታሽ ምንድነው
በራፍሽ ላይ እየሆነ የለው እባክሽ ምንድነው
በእስልምና ላይ የመጣው ክፋቱ ምንድነው ?
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

እኛ የምናቅሽ ለእስልምና ስትሆኚ ከለላ
ዘሬ ከየት መጣ  በመስጂዱ የሚወርደው ዱላ
በእርግጥ ለእኛም አላህ አለን የሚሆነን ከለላ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ተይ ዝም አትበይ ቤትሽን እየፈረሱ
ከአላህ ቤት ከመስጅድ እጃቸውን ያንሱ
መረራ የሆነው የአላህን ቅጠት እንደይቀምሱ።
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ዝምታሽ በዝቶአል በሙስሊሙ በደል
በፍትህ ላይ ቁሚ ሙስሊም እንዳይበዳል
የፍትህ ክልል ሁኚ እንዳይበዛ ወንጀል
=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ልብ በይ ኦሮሚያ ዉስጥሽን ተመልከቺ
ለሙስሊም ጠላቶች በርሽን አትክፈቺ
እባክሽ ኦሮሚያ  በፍትህ ላይ በርቺ

=========================
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ለሙስሊሙ ያልሆነ ለአንቺም አይጠቅምሽ
ለመስጂድ ያልሆነ ከቶ ምን ሊጠቅምሽ
ዝምታሽ አይብዛ  እንዳይጓደል ፍትህሽ
ሁሌም እንወድሸለን አላህ ይጠብቅሽ
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
👆 ተፃፈ በወንድማቹ ሙክታር ሁሴን
የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ
⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇⬇
https://t.me/httpMuktarhussen
https://t.me/httpMuktarhussen
╚══════════════════╝




የኢስላም ጠላቶች እረፉ
መቼም አይሳካላችሁም
https://t.me/httpMuktarhussen

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

11 085

obunachilar
Kanal statistikasi
Kanalda mashhur