በተረጋገጡ ነብያዊ ሃዲሶች ከጀነት እንደወረዱ የተጠቀሱ አምስት ነገራትን እነሆ
http://T.me/iqraknow1 መቃሙ ኢብራሂም
መቃሙ ኢብራሂም(የኢብራሂም መቆሚያ) ነብዩሏህ ኢብራሂም ካዕባን ሲገነቡ የቆሙበድ ድንጋይ ነው።
ይህ ድንጋይና ሩክነል-የማኒ የተባለው የካዕባ ማዕዘን ከጀነት እንደመጡ ነብዩ በሚከተለው ቃላቸው ነግረውናል:-
"ሩክነል የማኒና(በየመነ አቅጣጫ ያለው የካዕባ ማዕዘን) መቃሙ ኢብራሂም ከጀነት የሆነ እንቁዎች ናቸው"
(ሃኪም 3559፤አልባኒ ሰሂህ ብለውታል)
2 የዓጅዋ ቴምር
ዐጅዋ በመዲና ከሚገኙ ልዩ የቴምር አይነቶች አንዱ ነው።ይህ ቴምር ለተለያዩ ህመሞች ፈውስነት እንደሚያገለግል ተጠቅሷል። በሃዲስም "ዐጅዋ ከጀነት ናት። በውስጧም የመርዝ መድሃኒት አላት" (ኢብኑ ማጀህ 3452)
3 ሃጀረል-አስወድ(ጥቁሩ ድንጋይ)
ሃጀረል አስወድ ከካዕባ ደቡብ ምስራቃዊ አቆጣጫ የሚገኝ ጥቁር ድንጋይ ነው። ስለዚህ ክቡር ድንጋይ አስመልከተው ነብዩ(ሰ.ዓ.ወ) የሚከተለውን ነግረውናል:-
"ሃጀረል አስወድ ከጀነት ሲወርድ ከወተት የነጣ ነበር።ነገር ግን የሰው ልጆች ወንጀል አጠቆረው።"
(አህመድ፣ቲርሚዚ፤በሰሂሁል ጃሚዕ 1145)
4 ናይል(አባይ)ና ፉራት(ኤፍራጠስ) ወንዞች
"ሰይሃን፣ጀይሃን፣ ናይልና ኤፍራጠስ ከጀነት የሆኑ ወንዞች ናቸው።" (ሙስሊም 2839)
5 አር-ረውዷቱ ሺሪፋህ(የተከበረው ጨፌ) የተከበረው ጨፌ በነብዩ(ሰ.ዓ.ወ) መስጂድ ውስጥ ከሚምበራቸው እስከ መኖሪያ ክፍላቸው ያለው ስፍራ ነው።
"ከቤቴ እስከ ሚምበሬ ያለው ስፍራ ከጀነት የሆነ ጨፌ ነው!!"
(ቡኻሪ 1196)
(በአምስተኛው ላይ የዑለሞቹ የትርጉም ልዩነት መኖሩን ልብ ይበሉ)
http://T.me/iqraknow http://T.me/iqraknow