Masa Farm Journal (ማሳ)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


Masa was founded to support commercial farmers. We do this by sharing relevant agricultural information like the latest news, weather info, interesting studies, price info, subsidies etc.
https://masaeth.com/

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


የግብርና ኬሚካሎች በኢትዮጵያ 🌾

የግብርና ኬሚካሎች በዘመናዊ የግብርና ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ አላቸው። በአንድ በኩል ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳድጉ ሲሆን በሊላ መልኩ በግብአት ላይ ጥገኛነትን ሊፈጥሩ ይችላሉ።

ከ2017 እስከ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ ከውጪ ሀገራት ገቢ የተደረጉት የግብርና ኬሚካሎች እንደሚከተለው የቀረቡ ሲሆን የቀረበው መረጃ አሃዛዊ እውነታውን በኬሚካል አይነቶች እና በክብደት ያሳያል።


#ግብርና_ግንዛቤዎች #ዘላቂ_እርሻ #የኢትዮጵያ_ግብርና


ከመጋቢት ወር ጀምሮ እስከ ሰኔ ድረስ በጋምቤላ ክልል በሚገኙ እርሻዎች ላይ በእርሻ ሪፖርት የተደገፈ ጥናት ስንዳስስ ቆይተናል። ጥናታችን የሰሊጥ እርሻዎችን ምርት ለማሳደግ የሚረዳ የእርሻ መመሪያ ሆኖ የቀረበ ሲሆን ከፍተኛ ምርታማነትን ለማረጋገጥ የአየር ሁኔታን፣ የተባይ ስጋትን እና የእርሻ አስተዳደር እርምጃዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነበር።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጥናታችን ለጥሩ ምርታማነት ጊዜውን ጠብቆ ዘር መዝራት፣ በሽታ እና ተባይ የሚቋቋሙ ምርጥ ዘሮች መጠቀም እንዲሁም በየጊዜው እርሻችን ላይ ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን እርምጃ በተገቢው ጊዜ መውሰድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳላቸው ማሳየት ችሏል።


#sesame #sesame_production #ethiopia #farm_management #phenology


"The session gave a wider view of how agricultural investors can access loans."

Ato Dereje was one of the participants in the first "agricultural-financing" training session. Much like Ato Dereje, most of the session participants found the session insightful.

The second session is going to be held on October 6, 2023. Make sure to register and reserve your spot!

For more details follow the link
http://bit.ly/3ZFyk7e

#agriculture #investment #finance #training #Ethiopia


ቀጣዩ የሁለተኛ ዙር ስልጠና በሚመጣው ቅዳሜ መስከረም 12 ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት የሚዘጋጅ ሲሆን አሁኑኑ በመመዝገብ ቦታዎን ያስይዙ !

Make sure not to miss the next session to be held this coming Saturday on September 23, 2023.

📅 ቀን: መስከረም 12 2016

🕒 ጊዜ፡ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ረፋዱ 6 ሰዓት

📍 ቦታ፡ 22 ጫካ ቡና ፊት ለፊት


#agri_financing #የግብርና_ፋይናንስ #DBE #ኔትወርክ #network


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የመጀመሪያውን የግብርና ፋይናንሲንግ ዙር ስልጠና የግብርና ኢንቨስትመንት ባላቸው እና የግብርና ኢንቨስትመንት መጀመር የሚፈልጉ ባለሃብቶች ታድመውን ነበር።

በስልጠናውም ከኢትዮጵያ ልማት የመጣው ከፍተኛ ባለሙያ ታዳሚዎቹ የነበራቸውን ጥያቄዎች ግልፅ ያደረገላቸው ሲሆን በስልጠናውም ይዘት መደሰታቸውን ታዳሚዎቹ አጋርተውናል።

#agriculture #investment #finance #training #Ethiopia




በግብርና ፋይናንስ ሂደት ላይ በነበረን የመጀመሪያ መርሀ-ግብር ባገኘነው አስደሳች የተሳታፊ ምላሽ መሠረት ሁለተኛ መርሀ-ግብር እንዳዘጋጀን ስንገልፅ በደስታ ነው። 🌟🌾


ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር በመውሰድ የግብርና ፕሮጀክትዎን ለማሳደግ ወይም ግብርና መጀመር የሚፈልጉ ከሆኑ ይህ ስልጠና ለእርስዎ ተዘጋጅቷል። የልማት ባንክ የብድር ሂደት፣ ብድር በመውሰድ ሂደት ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶች፣ መሟላት ያለባቸው ዶክመንቶች እና የመሳሰሉትን ብድር ነክ ጥያቄዎችን በጥልቀት እንመረምራለን። 💡 📈


📅 ቀን: መስከረም 12 2016

🕒 ጊዜ፡ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ረፋዱ 6 ሰዓት

📍 ቦታ፡ 22 ጫካ ቡና ፊት ለፊት


#agri_financing #የግብርና_ፋይናንስ #DBE #ኔትወርክ #network


የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምን አይነት የብድር አማራጮችን ይሰጣል? የብድር ጥያቄ ካስገባን ጀምሮ ብድሩን እስከምናገኝ ድረስ ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል? የግብርና ብድር ለመውሰድ ምን አይነት መስፈርቶችን ማሟላት አለብን?

እነዚህን እና የመሳሰሉትን ከግብርና ብድር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከመጣው ከፍተኛ ባለሙያ ጋር ውይይት አድርገናል። በተጨማሪም ማሳ ምን አይነት አገልግሎት እንደሚሰጥም ማሳየት ችለናል።

እርስዎስ ከልማት ባንክ ብድር ለመውሰድ አስበዋል? ግብርና ለመጀመር እና ብድር ለማግኘት ምን አይነት መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባችሁ ያውቃሉ? እነዚህን እና ሌሎችም እንዲመለስላችሁ የሚፈልጉትን ብድር ነክ ጥያቄዎች በሁለተኛው የስልጠና መርሀ ግብራችን ላይ በመታደም መጠየቅ እና ማማከር ትችላላችሁ።

ለበለጠ መረጃ LinkedIn እና Telegram ገፆቻችንን ላይ ይከታተሉን!


የመጨረሻው የእድገት ሳምንት፡ #የመድረቅ_ደረጃ

በመጨረሻው የመድረቅ ደረጃዎች ላይ ሰብላችን ጥሩ ፀሀይ እና ንፋስ መጠን የሚያገኝ ከሆነ የመድረቅ ሂደቱ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል። ሰሊጥ ከእርሻ ላይ መሰብሰብ ያለበት የእርጥበት መጠኑ ከ8% እስከ 12% ሲደርስ ሲሆን በመድረቅ ደረጃው ወቅት የፍሬ ከረጢቶቹን መክፈት ይጀምራል።

በዚህም ምክንያት የሰብላችንን የእርጥበት መጠን መከታተል፣ ሰብላችንን ለመሰብሰብ በቂ ዝግጅት ማድረግ እና የፍሬ ከረጢቶቹ ተከፍተው የምርት ብክነት ስጋት በማይኖርበት ጊዜ ምርታችንን መሰብሰብ አለብን።

#late_drying_stage #harvest #sesame #ethiopia #agriculture


አስራ ሁለተኛው የእድገት ሳምንት፡ #የመድረቅ_ደረጃ

ይህ ደረጃ ሰብላችን መድረቅ የሚጀምርበት ደረጃ ሲሆን የተክሉ አካላት በሙሉ ደርቀው ቡኒ ቀለም መያዝ ይጀምራሉ። ከዚህ ደረጃ ጀምሮ ሰብሉ በዘር ከረጢቶች ውስጥ የሚገኘውን ምርት ለማድረቅ ከረጢቶቹን ቀስ በቀስ መክፈት ይጀምራል። በመሆኑም የምርት መባከን እንዳያጋጥመን የመድረቅ ሂደቱን መከታተል የተክሉ የእርጥበት ይዘት መጠንም ተገቢው ደረጃ ላይ ሲደርስ ለስብሰባ ዝግጁ ይሆናል።

በዚህ ደረጃ ወቅት ምንም አይነት እርጥበት ባይኖር ተመራጭ ሲሆን ጥሩ መጠን ያለው የፀሃይ እና የንፋስ ተጋላጭነት ተፈላጊ ነው። አስፈላጊውን በሌላ መልኩ ሰብላችን እንደማንኛውም ደረጃ ለተባዮች በከፍተኛ መልኩ ተጋላጭ በመሆኑ ሰብላችንን የምንሰበስብበትን ጊዜ በጥንቃቄ መምረጥ ከዛም ለመሰብሰብ ዝግጅት መውሰድ አለብን።

#drying_stage #sesame #ethiopia #agriculture

10 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

453

obunachilar
Kanal statistikasi