ƝƲƦƲ ቴክ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ይህ ቻናል ፈጠራዎችን ፣ መረጃዎችን በአማርኛ& English፣የቴክኖሎጂ እውነታዎችን ፣ የወደፊቱን ቴክኖሎጂ እና የአይቲ ምክሮችን በማካተት የቴክኖሎጂ ዓለምን ያቀርባል፡፡
በተጨማሪም፦ ዌብሳይት በተመጣጣኝዋጋ እንሰራለን
🔷 ማህበራዊ ሚዲያን ለእውቀት ብቻ እንጠቀምበት !
🔺 ጥያቄ እና አስተያየት ካለ በዚህ ቦት ያሳውቁን!
https://t.me/nurudish_bot

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል ፊጥር በዐል በጤና አደረሳችሁ ፤ አደረሰን!

ኢድ ሙባረክ!


ውድ የኑሩ ሳይቴክ ቤተሰቦች ተመልሰናል
በ DOC File እና በ DOCX File መካከል ያለው ልዩነት
**********
በኮምፒውተር የተለያዩ የጽሁፍ ስራዎችን ለመስራት ስናስብ በብዛት የምንጠቀምባቸው መጻፊያዎች DOC እና DOCX የሚባሉት ናቸው፡፡ ሁለቱም የማይክሮሶፍ ወርድ ዶክመንት ክፍሎች ሲሆኑ የተለያዩ ምስሎችን፣ የተለያዩ ቴብሎችን እና ቻርቶችን ለመጻፍ ያገለግላሉ፡፡ ለመሆኑ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ማይክሮሶፍት ዎርድ DOC የሚባለውን የመጻፊያ ስርዓት ዋና መገልገያ (default) አድጎት ቆይቷል፡፡ እስከ 2006 ድረስ DOC በምዝገባና በፈቃድ ጥቅም ላይ የሚውል ነበር፡፡ ከዚያ በኋላም የተለያዩ መሻሻሎች ተደርገውበታል፡፡ አሁን ላይ እንደ LibreOffice Writer፣ OpenOffice Writer፣ KingSoft Writer የመሰሉ በነጻ የቀረቡና በክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ መጠቀሚያዎችን አካትቶ ቀርቧል፡፡ እነዚህ ፐሮግራሞች የ DOC ፋይሎችን ለመክፈትና ለማስተካከል ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡
በሌላ በኩል DOCX የተባለው የመጻፊያ ፕሮግራም የ DOC ተከታይ ሆኖ በማይክሮሶፍት ወርድ የቀረበ ነው፡፡ በ2007 ተሻሽሎ በቀረበው የወርድ ወይም የመጻፊያ ፕሮግራም ቀዳሚ መጠቀሚያ ሆኖ የቀረበው DOCX ነው፡፡ ይህም የሆነው ማይክሮሶፍት ወርድ እንደ ኦፕን ኦፊስና ODF ካሉ ነጻና ክፍት መጠቀሚያዎቸ በገጠመው ፉክክር ምክንያት ነው፡፡
በ DOCX ውስጥ ያለው የኮድ መስሪያ በ XML የተሰራ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ያለችው X ይህንን የምታመለክት ናት፡፡ ይህ ኮዲንግ ሲስተም አዳዲስ መገለጫዎችን ጥቅም ላይ ያዋለ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ PPTX እና XLSX ያሉ ፎርማቶች ላይ ለውጥ አድርጓል፡፡ አሁን ላይ በሁለቱ መካከል ይህ ነው የሚባል ትልቅ ልዩነት ባይኖርም በጣም ትናንሽ ፋይሎችን ለመፍጠር DOCX የተሻለ አማራጭ እንደሆነ ይነገራል፡፡


የቴሌግራም ቻናል 👉 https://t.me/nurutech


🎯Telegram Update ከሆነ ቦኋላ ያመጣቸው አዳዲስ ገራሚ ፊውቸሮች🔥

፩ Protected Content in Groups and Channels🛡

ብዙዎችን ያስደሰተ በተለይ የTelegram ቻነል ና ግሩፕ ላላቸው ሰወች እንደምናውቀው Copypast እና Forward ለብዙ የቻነል Owneሮች ራስምታት ና ሲያስመርር የቆየ ነገር ነው አንዱ ላብን ጠብ አድርጎ ግዜውን ሰውቶ ቻነሉ ላይ የፃፈውን ማንኛውም Program ሌላኛው ዘና ፈታ ብሎ ወደ ራሱ ቻነል Copy past በማድረግ እራሱ እንዳዘጋጀው አስመስሎ ይለቃል ይሄ በራሱ የሚሰራውን ሰዉ Moral ይገላል አንዳንዶቹ ደግሞ Credit እያሉ Copy ና Forward ያደርጋሉ ከዚህ ቦኋላ ከማንኛውም ቻነል Copypast ና Forward ማድረግ አይቻልም.

ቁርጥሽ እወቂ አዳሜ እስካሁን ያዛጋቹን ይበቃል😏

፪ Auto Deleted Message

ይሄ ፊውቸር ደግሞ ለ አንድ ሰው መልክት ልከን ከ 24 ሰአት ከ 1ድ ሳምነንት ና ከ 1ድ ወር ግዜ ቦኋላ ከላክልነት ሰውዬ ጋር Automatically Deleted እንዲሆን የሚያስችል ነው.

፫ New emoji

ለምሳሌ የአንድ ሰዉ Bio ላይ ይሄን emoji 💔 ብንመለከት በቀላሉ ስለ ሰውየው feeling Guess እናደርጋለን እንደሚታወቀው emojiወች የሰወችን Emotion ወይም ስሜት ከቃላት በማይተናነስ መልኩ ይገልፃሉ Telegramምም ይህን በመገንዘብ ሰወች በይበልጥ የተሰማቸውን ስሜት እንዲገልፁ አዳዲስ emoji አምጥቷል
በጥቂቱ

😮‍💨😵🤝❤️‍🩹❤️‍🔥

፬ Delete My Message

ይህኛው ፊውቸር ደግሞ ከ አንድ ሰዉ ጋር ካወራነው የChat History ላይ የኛን Message ብቻ ከላክልነት ሰውዬ ጋር ነጥሎ ያጠፋል🔥

የClear History እህት በሉዋት😆

፭ Change Color / Theme

ይሄ ደግሞ የChat Background Color ና Themeን ለመቀየር ና ለማስዋብ የሚያስችለን Setting ሲሆን በፊትም ነበር ሲሆን አሁን ግን ተሻሽሎ በአዳዲስና ማራኪ Themeሞችና Background colors መቷል ሞክሩት

፭ Attach
ከስሙ እንደምንረዳው Attach ማያያዝ ሲሆን ማንኛውንም ፃሁፍ ከPhoto ጋር አንድ ላይ ለማያያዝ ያስችላል ትንሽ ቀለል ብሎ መጣ እንጂ ድሮም ያለ ፊውቸር ነው

እንደ ከአለም ጋለሪ የድንቃድንቅ
የግጥም Channel ላላቹ Owneሮች ምርጥዬ ናት 👌

፮ Automatic Terminate

ይሄ ፊውቸር ደግሞ ከኛ ስልክ ውጪ በሌላ ሰዉ ወይም በጓደኛችን ስልክ የTelegram አካውንታችንን Login ካደረግንና ከተጠቀምን ቦኋላ Automatically ከጓደኛችን ስልክ አካውንታችንን በራሱ Logout ያደርጋል እኛ Logout ማድረግ አይጠበቅብንም.🤗

ይሄ ሚሆነው ግን በገባንበት ሰው አካውንታችንን Automatic Terminate ከሞላን ነዉ

፯ Jump to Next Channel

እንደምናውቀው አብዛኞቻችን Telegram ላይ የተለያዩ ቻነሎች ውስጥ join ብለናል ይሄ ፊውቸር
ምንድነው የሚያደርገው አንድ ቻነል ላይ ተገብታቹ የሆነ ነገር እየተመለከታችሁ ወይም እያነበባቹ ወደ ሌላኛው ቻነል
ለመሄድ ከዛ ቻነል መውጣት አይጠበቅብንም የስልካችንን Screen ወደ ላይ Scroll ስናደርገው ወደ ሌላኛው ቻነል ይወስደናል or ያልፋል🚀


፰ Live Stream

live stream is a one-way
video broadcast System.

Live Stream ማለት ባጭሩ ቀጥታ ስርጭት ማለት ነው

ለምሳሌ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ሲያዘጋጅ እኛ ቤታችን ሆነን በቀጥታ በTvያችን ቴዲን እንመለከታለን እሱ ግን እኛን አያየንም ቴዲ መመልከት የሚችለው ኮንሰርቱን ላይ የታደሙትን ነው ስለዚህ Live Stream የተባለው Technology አንድን ሰው የትም ቦታ ሆነን በTv በTablets በስልክ ቀጥታ መከታተል ያስችላል ኮንሰርቱን ታደምን ማለት ነዉ Telegram ይህን ፊውቸር ነው ያመጣው 🙈

፱ Flexible Forwarding

ይሄ ፊውቸር ጥቅሙ ለምሳሌ አንድ ሰዉ message ቢልክልን ያን መልክት ለሌላ ሰዉ ሶስተኛ ወገን ስልንክ መጀመሪያ የላከውን ሰው Name Hide ያደርጋል ይሄ ደግሞ መጀመሪያ ላይ ለላከው ሰውዬ privacy ደህንነት የተጠበቀ ያደርገዋል.🤟

፲ Unpin All Message

ቻነላቸን ላይ Pin ያደረገውን Post በሙሉ በአንዴ Unpin ለማድረግ የሚያስችል ፊውቸር ነው እያንዳንዱን Post Unpin ከማድረግ ይታደገናል😎

Telegraph ሌሎችም ብቹ ገራሚ ፊውቸር አምጥቷል Telegram በዚህ ከቀጠለ Social mediaውን መቆጣጠሩ አይቀርም Facebook IG Twitter WTs'App የመሳሰሉት ላይ የሌለ ፊውቸር ነው እያሳየን ያለው Developeሮቹ ማሻሻያውን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል👍


#የፌስቡክ_ፕሮፋይላችንን_እንዴት_መቆለፍ_እንችላለን?

የፌስቡክ ፐሮፋይላችሁን እንድትቆልፉ እመክራለሁ፡፡

ፌስቡክ ላይ ፖስት የምታደርጉት ፎቶ፤ቪዲዮ፤ ወይም መልዕክት ከፌስቡክ ጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያየው ለማድረግ ፐሮፋይላችንን መቆለፍ ይኖርብናል፡፡

እንዲሁም ፕሮፋይላችንንም ከጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያይ ፕሮፋይላችንን መቆለፍ አለበት፡፡

ለአንድሮይድ ስልኮች ላይ ብቻ ነው ይሄ አገልግሎት ያለው፡፡iOS ስልኮች ላይ አይገኝም፡፡

እንዴት ነው የፌስቡክ ፕሮፋይላችንን ሎክ /መቆለፍ የምንችለው?

1ኛ፦ፌስቡክ አፕሊኬሽን እንከፍትና ወደ ፕሮፋይላችንን እንገባለን

2ኛ፦ በቀኝ በኩል በመደዳ የሚታዩትን ሶስት ነጥቦችን ክሊክ ማድረግ፤

3ኛ፦ “Lock Profile” የሚል አማራጭ ሲመጣ እሱን ክሊክ ማድረግ፤

4ኛ፦ ቀጥሎ “Lock Your Profile“ የሚል ምርጫ ከስር ይመጣል፡እሱን ክሊክ ማድረግ፤

5ኛ፦ በመጨረሻ‘You Locked Your Profile' የሚል ይመጣል፤እዛው ላይ OK ብለን እንጨርሳለን፡፡

አሁን ፌስቡክ ፕሮፋይላችን ተቆልፋል፡፡

ፕሮፋይላችንን ጨምሮ ፖስት የምናደርጋቸው ፎቶዎች፤ቪዲዮዎች እና መልዕክቶች ከፌስቡክ ጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ማንም ሰው ማየት አይችልም፡፡


አንድ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ #ጎጂ ወይም #ጠቃሚ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?

ከGoogle Play Store ላይ የምናወርዳቸው አፕሊኬሽኖች ጠቃሚ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው እና ጎጂ እንዳልሆኑ የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡

ነገር ግን አንድ አንድ ግዜ ጠቃሚ መስለው ጎጂ አፕሊኬሽኖችን Play Store ላይ ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡

ታድያ Play Store ላይ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ስናደርግ አፕሊኬሽኑ ጠቃሚ ወይም ጎጂ መሆኑን እንዴት መለየት እንችላለን?

1. አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ እንደተደረገ መመልከት

ዳውንሎድ ማድረግ የፈለግንው አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ (Download Count) እንደተደረገ በደንብ መመልከት

ለምሳሌ ዳውንሎድ የምታደርጉት አፕሊኬሽን አንድ ሚሊዮን ግዜ ወይም ከዚያ በላይ ዳውንሎድ እንደተደረገ ካያችሁ ወድያው አፕሊኬሽኑ የተለቀቀበት ቀን በደንብ መመልከት፡፡

ምክንያቱም አብዛኛው አፕሊኬሽን ከተለቀቀበት ግዜ ጀምሮ አንድ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የቆየ ሲሆን ነወ ከሚሊዮን በላይ ዳውንሎድ ሊኖረው የሚችለው፡፡ ስለዚህ እናንተ ማውረድ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ከተለቀቀ አንድ ዓመት ካልሞላው እና ዳውንሎድ የተደረገው ከሚሊዮን በላይ ከሆነ አፕሊኬሽኑን ከማውረድ ብትቆጠቡ ይሻላል፡፡

2. ስለ አፕሊኬሽኑ የተሰጡ የተወሰኑ አስተያየቶችን ማንበብ

ዳውንሎድ ማድረግ የምትፈልጉት አፕሊኬሽን ከማውረዳችሁ በፊት ከዚህ በፊት አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ያደረጉ ሰዎች ስለ አፕሊኬሽኑ አስተያየት (Reviews)ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህን አስተያቶች በጥንቃቄ ማንበብ፡፡

ስለ አፕሊኬሽኑ በጣም የሚያማርሩ አስተያየቶች ካነበባችሁ አፕሊኬሽኑ ከማውረድ እንደጥቆጠቡ እመክራለሁ፡፡

3. የአፕሊኬሽኑ ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ

አፕሊኬሽኑ ከላይ የተጠቀሱትን ፍተሸዎች ካለፈ ዳውንሎድ ታደርጉታላችሁ፡፡ ከዚያ ኢንስቶል ስታደርጉት የአፕሊኬሽኑን ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡

ሁላችንም ማለት ይቻላል አፕሊኬሽን ኢንስቶል ስናደርግ ስምምነቱን ሳናነብ "Accept" እንላለን፡፡ ልክ አይደለም፡፡
ምክንያቱም የሳይበር ወንጀለኞች ይህንን ባህሪያችን ስለሚያውቁ እኛን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን ስምምነቱ ላይ በማስገባት ጥቃት ሊፈፁሙብን ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ስምምነቱን ስታነቡ ለምሳሌ data mining, data sharing, pop-ups ወዘተ የሚሉ ቃላት ከተመለከታችሁ የአፕሊኬሽኑን ኢንስቶሊንግ ሂደት እንድታቋርጡ እመክራለሁ፡፡፡


ስለዚህ ዳውንሎድ ማድረግ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ቢያንስ እነዚህን 3 ፍተሸዎችን ካለፈ ጎጂ አይደለም ማለት ነው፡፡


ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያዎችን ለመጀመር በሙከራ ላይ ነኝ ብሏል።

የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ የሆነው ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት ለመጀመር በሙከራ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ይህ ሥርዓትም ቢያንስ ከ1000 በላይ ተከታይ ባላቸው ቻናሎች ላይ እንደሚጀመር ነው የገለጸው።

ከዚህ ቀደም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት የሌለው ቴሌግራም አሁን ላይ ተጠቃሚዎች ቻናላቸውንና ቡታቸውን በክፍያ እንዲያስተዋውቁ የሚያስችላቸውን አሰራር መዘርጋቱን ነው ይፋ ያደረገው።

የቴሌግራም መስራች እንዲሁም ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ እንደጠቀሰው በሙከራ ላይ የሚገኘው የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓቱ የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን የግል መረጃን አይጠቀምም ብሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ማስታወቂያዎቹ በግል እና በቡድን መልዕክት መለዋወጫ ሰሌዳዎች ላይ የማይታዩ መሆናቸውንና በክፍያ የሚቀርቡት ማስታወቂያዎች በቻናሎች ላይ ብቻ እንደሚቀርቡ ገልጿል።

ማስታወቂያ ማስነገር የሚፈልጉ አስተዋዋቂዎች ቻናላቸውን ወይም ቡታቸውን ከ160 ባልበለጡ ፊደላት ገለጻ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን በቋንቋ፣ በይዘት እንዲሁም በልዩነት ማስታወቂያው እንዲተላለፍላቸው የሚፈልጉትን ቻናል መርጠው ማስተዋወቅ ይችላሉ ተብሏል።

ቴሌግራም ከቻናል ባለቤቶች ጋር የትርፍ ክፍፍል የማድረግ እቅድ እንዳለውም ያስታወቀ ሲሆን ይህ የሚሆነው ግን መሰረታዊ ወጪዎቹን ከሸፈነ በኋላ እንደሆነ ገልጿል።

@nurutech @nurutech


ለሞባይል ጥገና የሚያስፈልጉን መሳሪያወች

መፍቻ ፦ ስልካችን ለመፍታት እና ለመግጠም ይጠቅማል ።

መልቲ ሜትር:- ሬዚስታንስ ፣ ቮልቴጅ እንዲሁም ከረንት ለመለካት እና የሰርኪዩት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ይጠቅመናል ።

ቲነር ፦ ዝገት ለመከላከል እና ቆሻሻ ለማስወገድ ይጠቅማል ።

ፔስት ፦ አይሲዎችን በመንቀያና በማስቀመጫ ሰአት ቦርዳችንና የሚነቀለዉ አይሲ በሙቀት እንዳይጓዳ ይጠቅማል ።

ብሎወር ፦ ሙቀትን በመስጠት አይሲዎችን ለመንቀልና ለማስቀመጥ ይጠቅማል ።

ካዉያ ፦ ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ ይጠቅማል ።

ሊድ ፦ ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ እንደ ቀላጭ የምንጠቀምበት ነዉ ።

ጃምፐር ዋየር ፦ ሁለት የተለያዩ የሰርኪዩት ክፍሎችን /የተላቀቁ ክፍሎችን/ ለማያያዝ የሚጠቅም ቀጭን ሽቦ ነዉ ።

ትዊዘር(ፒከር) ፦ አይሲ ወይንም ሌሎች የሞባይል ክፍሎች በብሎወር ስናሞቅ እንደ መቆንጠጫ የምንይዝበት ነዉ ።

ዲሲ ፓወር ሰፕላይ ፦ ከባትሪ የምናገኘዉን 3.7 ቮልት የሚሆን ቮልቴጅ የሚሰጥ ክፍል ነዉ። ከዚህም በተጨማሪ ስልካችን ኦፕን ይሁን ሾርት ወይም ስልኮች የሶፍትዌር ችግር እንዳላቸዉና እንደሌላቸዉ ሊያሳየን የሚችል በጣም ጠቃሚ መሳሪያ ነዉ ። በተጨማሪም ስፒከርን ወይም ሪንገርን ለመፈተሽ ይጠቅመናል።

ኮምፒውተር ፦ ለሶፍትዌር ጥገና ፣ ለሃርድዌር ላይብረሪ እና ሙዚቃ ለመጫን ይጠቅመናል ።

ፍላሽ ቦክስ ፦ በሶፍትዌር ጥገና ሰአት በሞባይልና በኮምፒዉተር መሃል የሚገኝና ሁለቱን አካሎች የሚያግባባቸዉ መሳሪያ ነዉ ።

ቦርድ ፕሌት :- የስልካችንን ቦርድ በምንበይድበት ጊዜ ወይም አይሲ በምንነቅልበት ጊዜ ቦርዱ እንዳይነቃነቅ የሚያደርግ መሳሪያ ነዉ ።

ሶፍትዌር ኬብል ፦ በሶፍትዌር ጥገና ስአት ስልካችንን ከፍላሸር ቦክስ ጋር የሚያግባባ ነዉ።

ቫይብሬተር ፦ ዉሃ ዉስጥ ገብቶ ወይም ስታክ ያደረገ ስልክ እንዲሰራ ቫይብሬተር ዉስጥ ተዘፍዝፎ ፣ የተወሰነ ደቂቃ ይቆያል ።

@nurutech @nurutech


የተለያዩ አይሲዎችን ለመለየት የሚጠቅም ዘዴ

1. ሲፒዩ :- ወርቃማ እግር አለዉ ።
2. ቻርጅ አይሲ:- R22 የሚል አነስተኛ ሬዚስተር አጠገቡ ይገኛል ።
3. ዩአይ አይሲ :- 20 እግር አለዉ እግሮቹም ወጣ ወጣ ያሉ ናቸዉ ።
4. ቪሲኦ :- አብዛኛዉን ጊዚ በቆርቆሮ የታሸገ ነዉ አልያም በወርቃማ መስመር ብቻዉን የታጠረ ነዉ ። ቪሲኦ የሚገኘዉ Rx ክፍል ዉስጥ ነዉ ።
5. ክሪስታል ኦሲሌተር :- ጠፍጣፋ ሬክታንግል መልክ ያለዉ ነዉ ።
6. ኔትወርክ አይሲ :- ከክሪስታል ኦሲሌተር አጠገብ ይገኛል ። ኔትወርክ አይሲ Rx ክፍል ዉስጥ ይገኛል ።
7. ፓወር አምፕሊፋየር :- አብዛኛዉን ጊዜ የመጀመሪያዉ (ከላይ የሚገኝ) አይሲ ነዉ ።
8. ኤፍ ኤም አይሲ(ሬዲዩ አይሲ):- አጠገቡ ባለቀለም ኢንዴክተር ይኖራል : ቀለሙም ደማቅ ወይም ደብዛዛ ሰማያዊ ነዉ ።
9. ብሉቱዝ አይሲ :- ሬክታንግል ቅርፅ ያለዉ ነጭ : አነስተኛና ጠፈር ያለ አካል ካጠገቡ ይገኛል ።
10. ፓወር አይሲ:- አጠገቡ ትንሽ እና ቀጭን አካል (አርቲስ) ሁሌም ይኖራል ።
11. ባካፕ ባትሪ :- የሰአት አይሲ የሚመስል ነዉ ።
12. ላይት አይሲ :- አጠገቡ ጥልቅ ሽቦ (ቡስተር ኮይል) ይኖራል ።
13. ሲም አይሲ :- ትንሽ : አንጸባራቂ : ብራማ ከለር ያለዉና ከሲም ማስቀመጫ አጠገብ ወይም ማስቀመጫ በስተጀርባ ይገኛል ።
14. ኪይ ፓድ አይሲ :- ከኪይ ፓድ እና ከኮኔክተር አጠገብ ወይም ከሲፒዩ አጠገብ ይገኛል ።
15. ካፓሲተር :- ቀለል ያለ ቡኒ ቀለም ያላቸዉ ናቸዉ ።
16. ኢንደክተር :- ጥቋቁር እና አብዛኛዉን ጌዜ ከካፓሲተሮች በመጠናቸዉ ተለቅ ብለዉ ይገኛሉ።
17. ሬዚስተር :- ጥቋቁር እና ትናንሽ ክፍሎች ናቸዉ።


የፌስቡክ ኩባንያ 100 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተከሰሰ


በኦሂዮ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ክስ የቀረበበት ፌስቡክ በህጻናት ላይ ባደረሰው ጉዳት 100 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል ክስ ቀርቦበታል

የፌስቡክ ኩባንያ 100 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍለ ተከሰሰ፡፡

የኩባንያውን ስም ወደ ሜታ የቀየረው ፌስቡክ 100 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል በኦሃዮ ፍርድ ቤት መከሰሱን የሩሲያው አርቲ ዘግቧል፡፡

ኩባንያው ክስ የቀረበበት በፈረንጆቹ 2021 ዓመት ውስጥ ካለፈው ሚያዝያ እስከ ጥቅምት ባሉት ወራት ውስጥ በፌስቡክ ህጻናትን ላልተገባ ጉዳት የሚያጋልጡ ጎጂ ይዘቶች በፌስቡክ በመተላለፋቸው መሆኑን የኦሂዮ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዴቭ ዮስት ተናግረዋል፡፡

እንደ ክሱ ከሆነ ፌስቡክ በህጻናት ላይ አሉታዊ መልዕክቶች እንዳይዘዋወሩ መከላከል የሚያስችል አሰራር ቢተገብርም ትርፉን ለመሰብሰብ ሲል ተግባራዊ አለማድረጉ ተገልጿል፡፡

እነደ ዘገባው ከሆነ ፌስቡክ ላደረሰው ጉዳት 100 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል እና የእርምት እርምጃዎችን እንዲወስድ ተጠይቋል፡፡

የሜታ ኩባንያ ቃል አቀባይ ጆ ኦስቦርን በበኩላቸው ክሱ በእውነት ላይ ያልተመሰረተ በመሆኑ ራሳችንን እንከላከላለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ፌስቡክ ላይ ክሱ የቀረበው የቀድሞ የኩባንያው ሰራተኛ አማካኝነት በወጣ ሪፖርት መነሻነት ሲሆን ፌስቡክ የተለያዩ ግጭት ቀስቃሽ እና ሌሎች የተለያዩ ማህበረሰብ አካላትን ሆን ተብለው የሚጎዱ መልዕክቶች ሲዘዋወሩ ኩባንያው ለትርፍ ሲል እርምጃ አልወሰደም የሚል ክሶች ቀርበውበታል፡፡

የሜታ ኩባንያ መስራች እና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ በበኩላቸው በድርጅታቸው ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ አድረገው ትርፍን እንደማያስቀድም ተናግረዋል፡፡

@nurudish


Samsung S9+
128Gb
Used
Price negotiable

👉 @nurudish_bot


✴️5 ምርጥ አለምአቀፍ ነፃ የትምህርት ዕድል (scholar ship)ማግኛ ድህረ ገፆች(Websites)

▫️1 - StudentScholarships.org
▫️2 - collegeboard.org
▫️3 - StudentScholarships.org
▫️4 - ScholarshipExperts.com
▫️5 - SuperCollege.com

@nurutech


ሰላም ውድ የኑሩ ሳይቴክ ተከታታዮች ከዛሬ ጀምሮ ከምንሰጣችሁ የቴክ መረጃዎች በተጨማሪ ጧት እና ማታ ሁሌም አነቃቂ ንግግሮችን እናደርሳቹሃለን

በዚህ ዙሪያ አስተያየት ካላችሁ 👉 @nurudish_bot


Facebook እና Instagram እንቢ ካላችሁ በVPN እየሰሩ ስለሆነ Vpn ተጠቀሙ

@nurutech @nurutech


የፌስቡክ ኩባንያ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልዕክትን መሰረዙን የኢትዮጵያ መንግስት አወገዘ።

ግዙፉ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ጠቅላይ ሚንስትሩ በተረጋገጠ የፌስ ቡክ ገፃቸዉ ያስተላለፉትን መልዕክት የሰረዘዉ መልዕክቱ ግጭትን ያባብሳል በሚል ምክንያት ነዉ።ጠቅላይ ሚንስትሩ "አሸባሪ" ያሉትን ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)ን "ለመቅበር" ኢትዮጵያውያን እንዲነሱ ጥሪ ያስተላለፉበት ነበር።አንድ የፌስ ኩክ ኩባንያ ቃል አቀባይ ለአሜሪካዉ ዜና አገልግሎት AP እንደነገሩት የጠቅላይ ሚንስትሩ መልዕክት ሁከትን ማባባስን የሚያግደዉን የኩባንያቸዉን ደንብ የጣሳ ነዉ። የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ግን ፌስ ቡክ መልዕክቱን በመሰረዝ ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ጋር ማበሩን አስመስክሯል በማለት ወቅሷል።የኮሚኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ ፌስ ቡክና ሌሎች በስም ያልጠቀሳቸዉን ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ራሳቸዉን ኢትዮጵያ ዉስጥ «ግጭት እንዲባባስ የሚሰሩ» በማለት ወቅሳቸዋል።ፌስ ቡክ ከዚሕ ቀደምም የቀድሞዉን የአሜሪካ ፕሬዝደንት የዶናልድ ትራምፕን እና የብራዚሉን ፕሬዝደንት የያር ቦልሴናሮን ቦመልዕክቶች ሰርዞ ነበር።

[DW]


#የሞባይል_ስልካችን_ሜሞሪ_ሞልቷል_የሚል_መልእክት_ለምን_ይመጣል ?

አብዛኞቻችን በስልካችን ላይ ቪድዮ፣ ሙዚቃ፣ አፕልኬሽን.. ስንጭን ሜሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage) የሚል መልእክት እየመጣ የፈለግነውን እንዳንጭን ይከለክለናል።እንዲህ ዓይነት ችግር ሲገጥመን እንዴት ሚሞሪያችንን ነፃ( free) ማድረግ እንደምንችል እንመልከት።

ከዚያ በፊት ግን ሜሞሪ ሞልቷል (Insufficient storage) የሚል መልእክት ለምን ይመጣል?

የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም አንዱ ስራ አፕልኬሽን install ስናደርግ አፕሊኬሽኖችና ከነሱ ጋር የተያያዙ ፋይሎችን ለማስቀመጥ ነው።አፕሊኬሽኖችና ከነሱ ጋር የተያያዙ ፋይሎችን ማስቀመጬ ቦታ ሲያጣ ሜሞሪ ሞልቷልይ ይለናል።

አፕልኬሽኖች የሞባይላችንን storage ይጠቀማሉ።እንዴት?

1ኛ፦ አፕሌክሽኖቹ ለራሳቸዉ የሚወስዱት ቦታ አለ።

2ኛ፦ የአፕልኬሽኖቹ data ማስቀመጫ የሚጠቀሙበት ቦታ አለ።

3ኛ፦ የአፕልኬሽኑ ካሽ(ጊዜያዊ ፋይል) ማስቀመጫ ቦታ ይፈልጋል።

እነዚህ ካሽ(ጊዜያዊ ፋይሎች) ጣም ብዙ ቦታ ሊይዙ ይችላሉ።

✔ መፍትሄ

ከመፍትሔው በፊት መጀመራያ እስቶሬጃችሁን ምን ምን እንደሞላዉ እዩት።

የስልካችሁ ስቶሬጅ መረጃ ለማየት ከታች ያሉትን ስፔፖች ይከተሉ ።

1⃣፦ Setting ዉስጥ ይግቡ

2⃣፦ ከዛ Storage የሚለዉ ዉስጥ ይግቡ ።
ከዚያ የ RAM ፤ Internal Storage ፤ SD Card የያዙትን መጠን በ% ያሳያችሗል።

3⃣፦ Internal Storage የሚለዉን ይጫኑት ።

#Avaliable ፦ የሚለው ላይ አሁን ያላችሁ ነፃ የሆነ የሚሞሪ መጠን ነው። System ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ለራሱ እና ከስልኩ ገር ለሚመጡ ለአንዳንድ አፕልኬሽኖች(እንደ Setting ፤ Chrome ፤ Phone ፤GMail ፤Google ፣Contacts ፤ Photo. ..) ለማስቀመጥ የተጠቀመበት memory ያሳየናል።

#Owners የሚለው ላይ እኛ የጫንናቸዉን አፕሌኬሽኖች፣ፎቶዎች፣ ወዘተ በዝርዝር ያሳየናል።
አሁ ከላይ ካያችኋቸው ፋይሎች ዉስጥ ብዙ ቦታ ይዞ ሚሞራያችሁን የሞላዉን ትመርጣላችሁ።
አፕልኬሽን ከሆነ ብዙ ጊዜ የማትጠቀሙበትን uninstall ማድረግ።

#Uninstall ለማድረግ Setting->Apps ከዛ uninstall ለማድረግ የፈለጋችሁትን አፕልኬሽን መርጣችሁ ስትጫኑት uninstall የሚል ሲመጣ አሱን ይጫኑት።
ፎቶ ከሆነ የማትፈልጉትን ፎቶ አየመረረጣችሁ ማጥፋት አለባችሁ።Video ከሆነ የማትፈልጉትን Video እየመረጣችሁ ማጥፋት።Audio ከሆነም ምረጡና ያጥፉ።

ከዚያም Clear data የሚለዉን በመጫን ሚሞሪ ላይ ያሉትን ፋይሎችያጥፉ

SD Card የስልኩ default ማስቀመጫ ለማድረግ ከፈለጋችሁ፦Setting-> Storage->default write disk የሚለዉጋ Phone Storage የሚለዉን ተመርጦ ታገኙታላችሁ አናንተ ግን SD card የሚለዉን ምረጡ።


Jeff Bezos የየትኛው ድርጅት መስራች ነው
So‘rovnoma
  •   Google
  •   Facebook
  •   Amazon
  •   You tube
409 ta ovoz


ላፕቶፓችን ላይ ያለውን ኢንተርኔት እንዴት ያለምንም ሶፍት ዌር በሞባይላችን
መጠቀም እንችላለን?

1. cmdን በአንሜኒስትሬተር ያሩጡት (right click በማድረግ run as
administrator የሚለውን መጫን)

2. ላፕቶፓችን ኔትዎርክ ሼር ለማድረግ ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ:netsh
wlan show drivers የሚለውን ጽፎ ከሚመጣልን ዝርዝር ውስጥ Hosted
network supported :Yes ይህ ከመጣ ላፕቶፓችን ይችላል ማለት ነው

3. በመቀጠል ይህንን ኮማንድ ማስገባት: netsh wlan set
hostednetwork mode=allow ssid=Hotspotname key=password
⚠️ማሳሰቢያ: SSID የሚለውን በፈለግነው ስም መቀየር እንችላለን: KEY የሚለው የዋይ ፋይ ፓስዎርዳችን ስለሆነ የምንፈልገውን መስጠት እንችላለን

4. በመቀጠል የኔት ዎርክ አዳፕተራችንን በመክፈት እና እሱላይ right click
በማድረግ : Allow other network users to connect through this
computer's internet connection የሚለውን እንመርጥያ ከስር ካለው ሊስት ውስጥ የፈጠርነውን የዋየርለስ ኔትዎርክ እንመርጥለታለን። ከዛም OK በለን እንወጣለን

5. በመጭረሻ ወደ CMD ተመልሰን:
ለማስጀመር netsh wlan start hostednetwork የሚለውን ኮማንድ
እናስገባለን ለማቆም netsh wlan stop hostednetwork የሚለውን እናስገባለን

6. አሁን ሞባይላችንን wifi ከፍትን SSID ላይ ያስገባነውን የኔትዎርክ ስም
መርጠን ለሚለው KEY ላይ ያስገባነውን በመስጠት መጠቀም መጀመር እንችላለን።


ፌስቡክ የስያሜ ለውጥ ሊያደርግ መሆኑ ተነገረ፡፡

ግዙፉ የማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገጽ ኩባንያ ፌስቡክ በቅርቡ የስያሜ ለውጥ ሊያደርግ እንደሚችል የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡

ሬውተርስ የቴክኖሎጂ መረጃ ምንጭ የሆነውን ዘ ቨርጅ ድረ-ገጽ ዋቢ አድርጎ ባወጣው መረጃ ፌስቡክ በቀጣዮቹ ሳምንታት የስያሜ ለውጥ በማድረግ በአዲስ መልክ የመቅረብ እቅድ እንዳለው ተገልጿል፡፡

በአዲሱ ስያሜ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በጥቅምት ወር መጨረሻ በሚደረገው ዓመታዊ የኩባንያው ጉባኤ ላይ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ማርክ ዙከርበርግ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

ኩባንያው በአዲስ ስያሜ እና አወቃቀር ሲቀርብ ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም ኦኩለስ እና ሌሎች የኩባንያው መተግበሪያና አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በሚደራጀው ኩባንያ እንደሚተዳደሩ ይጠበቃል ሲል መረጃው አትቷል፡፡ (EAII)


የፌስቡክ ፣ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም ገፆች ትናንት ለ6 ሰአት መቋረጥ ቴሌግራም ላይ 70 ሚልየን አዲስ ተጠቃሚዎች ጨምሯል ሲል አርቲ ሚዲያ ዘግቧል።


✴️ በህንድ ሲም የሚቀበል ነጠላ ጫማን ለኩረጃ ሊያውሉ የነበሩ ተፈታኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

🧧በህንድ ራጃስታን ግዛት ከዚህ ቀድም ከፍተኛ ጥቅም ያስገኛል የተባለውን የመምህራን ፈተናን ለመስጠት በሚል ኢንተርኔት ቢቋረጥም የኩረጃ መልኩ ተቀይሯል።ነጠላ ጫማን በብሉቱዝ በማገናኘት ፈተናውን ቀድመው ተፈትነው የወጡ ተፈታኞች ውስጥ ላሉ ጓደኞቻቸው መልስ እንዲነግሩ ተደርጎ ተመቻችቷል።

🧧በዚህም መሰረት ነጠላ ጫማው ሲም የሚቀበል ሲሆን በአይን ለማየት እጅግ አዳጋች የሆነ ቀጭን የጆሮ ማዳመጫ በጆሮዋቸው በማድረግ ወደ መፈተኛ ክፍል ያመራሉ።አንዳንዶቹ የጆሮ ማዳመጫውን በጊዜያዊነት በጆሮዋቸው ውስጥ ለማስቀበር ሲሞክሩ እንደነበረም ተሰምቷል።ከውጪ ስልኩ ሲደወልላቸው በእግር ጣታቸው ስልኩን ያነሳሉ።

🧧ለአንድ ነጠላ ጫማ 600ሺ ሩፒ ወይም 8ሺ ዶላር ይጠየቅበታል።በዚህ ድርጊት እጃቸው አለበት የተባሉ አደገኛ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል።ህንድ ተፈታኞች ነጠላ ጫማ አድርገው ወደ መፈተኛ ክፍሎች እንዳይገቡ ከልክላለች።
©ethio techs
════❁✿❁ ═══════

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

4 252

obunachilar
Kanal statistikasi