የሌሊት ወፍ
"የሌት ወፍ እንደ ዓይጥ ጥርስ አላት፤ እንደ ወፍም ከንፍ አላት፡፡ አንድ ጊዜ የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊቶች ተጣልተው አራት ቀን ሙሉ ጦርነት አደረጉ፡፡
የሌት ወፍ ግን በዳር ሁና ትመለከትና የዱር አራዊቶች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ ትሔድና እኔ እኮቁጥሬ ወደናንተ ነው እዩት ጥርሴን! እዩት ጡቴን እስቲ ከሰማይ ወፎች እንደኔ ጥርስና ጡት ያለው ማነው ትላቸዋለች፡፡
ደግሞ የሰማይ ወፎች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ
ትሔድና እኔ እኮ ቁጥሬ ወደናንተ ነው! እዩት ክንፌን እስቲ ከዱር አራዊት ወገን እንደኔ በከንፍ እየበረረ በአየር ላይ የሚሔድ ማነው ትላቸዋለች፡፡
ወደ ጦርነቱ ግን ምንም ቢሆን አትገባም፡፡
ከጥቂት ቀን በኋላ ዕርቅ ተደረገና ጦርነቱ ቆመ፡፡ ስለዚሁም የሰማይ ወፎችና አራዊቶች ትልቅ በዓል አደረጉ፡፡
የሌት ወፍም ወደ ወፎች ድግስ ብትሔድ እኛ እንደ አውሬ ጥርስ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡ ወደ ዱር አራዊትም ብትሔድ እኛ እንደወፍ ክንፍ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡
ከዚህ በኋላ አፈረችና ወፎችም አራዊትም እንዳያይዋት ቀን ቀን እየተደበቀኝ እየዋለች፤ ማታ ማታ ምግብዋን ለመፈለግ ጀመረች። ቀን ወፎችም ቢያገኝዋት! አራዊትም ቢያገኝዋት አይተዋትም ይገድልዋታል እንጂ
የሌት ወፍ የተባለችውም ከዚያ ወዲህ ነው ይባላል፡፡" (ብላቴን ጌታ ኅሩይ)
አንዳንዶች እንዲህ ናቸው፤ያጠቃ ያሸነፈ ከመሰላቸው ጋር ቦርጫቸውን ያስተካክላሉ፤ላጠቃው መወድስ ለተጠቃው ተረት አያጡም። ጥርሳቸውንና ክንፋቸውን እያቀያየሩ እያሳዩ "እኔ ያንተ አሽከር ያንተ ቡችላ" ይላሉ።
እንደ ንሥርም እንደ አንበሳም ኮራ ብሎ መብረር ወይም መንጎማለል የሚቻለው ወይ ወፍነትን ወይ አውሬነትን መምረጥ ሲቻል ነው!
ጦርነትም ሆነ ጠብ በእርቅ አልያም በመሸናነፍ ይጠናቀቃል። ያኔ እንደ ሌት ወፍ ሌት መጓዝ ይመጣል።
ያድኅነነ እመዓቱ ይሰውረነ
#መርቆሬዎስ ፳፭
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖