የመዳን ትምህርት
(ነገረ ድኅነት) ክፍል ~ 3
ክርስቶስ ሞቶ ከተነሣ በኋላ ሞት ኃይሉን አጥቷል፤ ከዚያ በፊት ሞት ሰውን ዂሉ ወደ ሲኦል ወደ ሁለተኛ ሞት የሚያጓጉዝ ነበር፤ አሁን ግን ሰውን ወደ ሕይወት የሚያደርስ ነው፡፡ ሞት ወደ ገነት ወደ መንግሥተ ሰማያት የምንጓዝበት መንገድ ኾኗል፡፡ ሰዎች የሚፈሩት ሳይኾን የሚፈልጉት ኾኗል፤ ወደ እግዚአብሔር የምንሔድበት ስለ ኾነ፡፡ ከአዳም ጀምሮ እስከ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት ድረስ የበደሉትም ያልበደሉትም በመስቀል ላይ በተከፈለው ዋጋ ድነዋል፡፡ ጌታችን ይህን ድኅነት የሚናገሩ፣ የምሥራቹን የሚያወሩ፣ ላለፈው ይቅርታ መደረጉን፣ ለሚመጣው ሕግ መሠራቱን የሚመሰክሩ ሐዋርያትን መርጦ ሾመ፡፡ ለወደፊቱ ለሚመጣው ትውልድ ድኅነት እንደሚገኝ ለማስተማር በዓለም ዂሉ ላካቸው፤ በቃላቸውም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር (ሐዋ. ፪፥፵፯)፡፡
አሁን እንዴት እንድናለን?
የታመሙት ድነዋል፤ ሲኦል የነበሩት ወጥተዋል፡፡ እኛስ ድነናል ወይስ እንድናለን? እኛማ እንድናለን፡፡ ካሣው ለዂሉም ተከፍሏል፤ አምላካችን የሞቱትን አድኗልና፡፡ በሕይወተ ሥጋ ያለን እኛ ግን ድኅነቱን ተቀብለን በሃይማኖት (በእምነት)፣ በጥምቀት፣ ቅዱስ ሥጋውን በመብላት፣ ክቡር ደሙን በመጠጣት የተሠራውን ሕግ በመጠበቅ ድኅነትን እናገኛለን፡፡ ድነናል ብለን የምናወራ ከኾነ ሕግ ለምን አስፈለገን? በገነት ለሚኖሩት ከሲኦል ለወጡት ሕግ አያስፈልጋቸውም፡፡ በተጻፈ ሕግ አይመሩም፤ እኛ ግን በተጻፈ ሕግ ከኦሪት ወደ ወንጌል የተሸጋገርነው የምንጠብቀው እና የሚጠብቀን የሚያድነን ሕግ ተሠርቶልናል፡፡
በዚህ እንድናለን፤ በሕጉ ካልኖርን ደግሞ እንቀጣለን፡፡ ከዚህ ላይ ‹‹የሚድኑትን›› የሚለውን ቃል ልብ ማለት ያሻል፡፡ ‹‹የዳኑትን›› አይደለም ያለው፤ ‹‹የሚድኑትን›› አለ እንጂ፡፡ ስለዚህ ክርስትና ወይም ሕገ ወንጌል የዳኑትን ለማዳን የተሰጠ ሕግ ሳይኾን ያልዳኑት እንዲድኑ የተሰጠ ሕግ ነው፡፡ የኦሪት ሕግ (የኦሪት መሥዋዕት) ማዳን የሚችል አልነበረም፤ ወንጌል ግን ለዓለም ድኅነት የተሰጠ ሕግ ነው፡፡ ሐዋርያት ዓለም እንዲድን የሕይወትን ወንጌል ይዘው ዞሩ፤ አስተማሩ፡፡ ወንጌል የተሰበከው ለዳኑት ሳይኾን ለሚድኑት ነው፡፡ ስለዚህ ለመዳን ምን ያስፈልጋል? የሰው ልጅ ለመዳን የሚስፈልጉት ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፤
፩ኛ ማመን
የሰው ልጅ፣ ከዂሉ አስቀድሞ የዓለም መደኀኒት ክርስቶስ ሕግን እንደ ሠራለት አምኖ መመለስ ያስፈልገዋል፡፡ “ለሰው ዂሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም (ወደ ሰው) የመጣው ነው፡፡ በዓለም ነበረ፤ ዓለሙም በእርሱ ኾነ፤ ዓለሙ ግን አላወቀውም፡፡ ወደ ወገኖቹ መጣ፤ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም፡፡ ለተቀበሉት ዂሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች እንዲኾኑ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡ እነርሱም ከእግዚእሔር ተወለዱ …፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ (ዮሐ. ፩፥፱)፡፡ ቀደም ሲል የነበረው ድኅነት ለተቀበሉትም ላልተቀበሉትም የተደረገ፤ ላመኑትም ላላመኑት የተፈጸመ ድኅነት ነው፡፡ አሁን ግን ላመኑ እንጂ ላላመኑ የሚሰጥ ድኅነት የለም፡፡
፪. መጠመቅ
“ያመነ የተጠመቀ ይድናል” (ማር. ፲፮፥፲፮) ተብሎ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረው ለመዳን እምነት ያስፈልጋል፤ ከእምነት ቀጥሎ መጠመቅ ያሻል፤ ይህን ካሣ ተፈጽሞ የተሠራውን ሕግ መፈጸም ግዴታ ነው፡፡ ለመዳን ማመን ብቻ አይበቃም፡፡ እምነትማ አጋንንትም አላቸው፡፡ ዕለት ዕለት የሚድኑበት፣ የሚጨመሩበት መንገዱ እምነትና ጥምቀት ነው፡፡ የቅዱሳን ሐዋርያት ተግባርም ይህ ነበር፡፡ ሕይወትን ድኅነትን መስበክ፤ ያመነውን ማጥመቅ፤ የድኅነቱ ተሳታፊ ማድረግ ወደ ድኅነቱ ማስገባት፤ የሕይወትን ቃል ለዂሉ መመስከር ነው፡፡ ዓላማው ለማሳመን፣ ለማጥመቅ፣ ለማዳን ነው፡፡ ለመዳን አምኖ መጠመቅ የግድ አስፈላጊ መኾኑን በሐዋርያት ሥራ የተመዘገበው የጃንደረባው ታሪክ ያስረዳናል (ሐዋ. ፰፥፴፭-፴፯)፡፡
ማመን ብቻውን ስለማያድን ጃንደረባው ‹‹አምናለሁ›› ብሎ ከማመን አልፎ ሃይማኖቱን መስክሯል፤ ፊልጶስም ‹‹ድነሃል፤ ሒድ›› አላለውም፤ አጠመቀው እንጂ፡፡ ስለዚህ ከእምነት ቀጥሎ መጠመቅ ለድኅነት ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ዓለምን ለማዳን የመጣው አምላካችን ሐዋርያትን ወደ ዓለም ዂሉ የላከው (ማቴ. ፳፰፥፲፱)፡፡ ተልዕኮውም በቃ ‹‹አድኛቸዋለሁ›› አይደለም፤ እንዲያምኑ፣ እንዲጠመቁ፣ ትእዛዙን እንዲጠብቁ፣ ደቀ መዛሙርት እንዲኾኑ ነው፡፡ ድኅነት የሚገኘው በዚህ መንገድ ነው፡፡ በማውራት ብቻ ‹‹ድኛለሁ›› ብሎ ተዘልሎ በመቀመጥ አይደለም፡፡ “… እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፤ የሕይወትንም መንገድ ያስተምሯችኋል …” ተብሎ እንደ ተጻፈ (ሐዋ. ፮፥፲፯)፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት የመዳንን መንገድ የሚነግሩን እንድናየው አይደለም፤ እንድንጓዝበት ነው እንጂ፡፡ “… ‹ጌቶቼ፥ እድን ዘንድ ምን ላድርግ?› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፤ አንተ እና ቤተሰቦችህ ትድናላችሁ› አሉት፡፡ የእግዚአብሔርንም ቃል ለእርሱና በቤቱ ላሉት ዂሉ ነገሩአቸው … በዚያው ጊዜ ከቤተ ሰቡ ዂሉ ጋር ተጠመቀ፤” (ሐዋ. ፲፮፥፴-፴፬)፡፡ ከዚህ ላይ ‹‹ድናችኋል›› ሳይኾን ‹‹ትድናላችሁ›› የሚለውን ቃል ልብ ይሏል፡፡ “ዳግመኛ ከውኃ እና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” እንዳለ (ዮሐ. ፫፥፭)፡፡ ስለዚህ ሰው አምኖ ይጠመቃል፤ ከእግዚአብሔርም ይወለዳል፤ በዚህ ድኅነትን ገንዘብ ያደርጋል፡፡ ከእግዚአብሔር ካልተወለደ በፍጹም ሊድን አይችልም፡፡ መዳን ማለት የእግዚአብሔርን መንግሥት ወርሶ ስሙን ቀድሶ መኖር ነው፡፡ ስለዚህ የሕይወት እና የድኅነት ወንጌል ለዓለሙ ዂሉ ይሰበካል፤ ዂሉም ይድን ዘንድ (ማር. ፲፮፥፰)፡፡
ክፍል 4 ላይ እንመለስበታለን...
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo