አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ✝


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


"ትክክለኛው ቻናላችን ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኛ አይደሉም"
የአባታችን ብጽዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ትምርት የሚቀርቡበት መንፈሳዊ ገፅ ነው፡፡
"የንስሀ አባት ማለት እርሱን ስትመለከት እግዚአብሔርን እና ትዕዛዛቱን የምታስታውስበት
ሰው ማለት ነው።"
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

ለማንኛውም ሓሳብ እና አስተያየት
@RomareBot ይላኩልን፡፡

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


✝#ሰውን_ወዳጁና_ርህርሁ_እግዚአብሔር

ሰው ጨካኝ ሲሆን #እግዚአብሔር ግን ሁሉን የሚወድ ቸርና ርህርህ ነው፡፡ ለዚህም ነው ንጉስ ዳዊት ከሦስቱ ቅጣቶች መካከል አንዱን እንዲመርጥና አማራጩ ሲቀርብለት የተናገረው ቃል ድንቅ ነው፡፡ " ምህርቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ በሰው እጅ ግን አልውደቅ፡፡" 2ኛ ሳሙ 24 ፥ 14፡፡ ጻድቁ እዮብም በሦስቱ ባልደረበቹ እጅ በወደቀ ጊዜና እነርሱም እርሱን መውቀሳቸውን ባላቋረጡ ጊዜ እንዲህ ነበር ያላቸው ፡- "ነፍሴን የምትነዘንዙ በቃልስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው? ይኸውም ስትሰድቡኝ አሥር ጊዜ ነው፡፡" ኢዮ 19 ፥ 2 - 3፡፡ #እግዚአብሔር ግን ከሰው በእጅጉ በተለየ መልኩ መሐሪና ርህርህ መሆኑን በሚከተሉት ውስጥ እንመለከታለን፡፡

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ


🌻
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቀም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።
🌻
ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - መንፈሳዊው መንገድ መጽሐፍ አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)
🌻
የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን።
🌻


" ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳልና "
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ


✝ የርኩሳን መናፍስት ስብስብ

በሰይጣን የሚመሩት ርኩሳን መናፍስት ንስሓ በገቡትና በአማኞች ላይ ስለሚከፍቱት ውጊያ ዕቅድ ለማውጣት ይወያዩ ዘንድ ጉባኤ ተቀመጡ ። በዚህ ጊዜ ሊቀ መንበሩ አማኞችን ሊያጠፋ የሚያስችል እጅግ አዲስ ዕቅድ እንዲያቀርቡ አባላቱን ጠየቀ ።

አንደኛው ርኩስ መንፈስ እንዲህ አለ : " #የእግዚአብሔርን ሕልውና እንዲጠራጠሩ እናድርጋቸው ። "

ሁለተኛው " መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጠራጠሩ እናድርጋለው ። " አለ ።

ሌላኛው ደግሞ " ዘላለማዊነትን እንዲጠራጠሩ እናድርጋቸው ። " አለ ።

አራተኛው " በምኞትና በፈተናዎች እናታላቸው ። " ብሎ ተናገረ ።
እነዚህን የሚሙስሉ አሳቦች ከየአቅጣጫው መወርወራቸው ይቀጥል እንጅ ሊቀ መንበሩን አንዱንም አሳብ ሊያጸድቅ አልፈለገም ፤ ሁሉም የቆዩና ከዚህ በፊት #የተጠቀሙባቸው_ዕቅዶች_ነበሩና ። ሁሉም እርግጠኛ የሆኑ ውጤቶች ሊያቀርቡ ስላልቻሉ ብዙ ሰዎች ከእነርሱ እያመለጡ ወደ እምነት ጎራ መግባት ቻሉ ።

አንድ የሚሻል ልምድ ያለው ርኩስ መንፈስ የሰው ልጆችን ሊያጠፋ የሚችል አንድ አዲስ እና ስኬታማ ዕቅድ ለማዘጋጀት ኃላፊነቱን ከወሰደ በኋላ እንዲህ በማለት ተናገረ ፦ " ስለ #እግዚአብሔር ሕልውና ፤ ስለ መጨረሻው ፍርድ እውነትነት ፤ ስለ ዘላለማዊው ቅጣት ፤ ስለ ገነትና ስለ ሲዖል መኖር መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነገር ሁሉ ትክክለኛ እና እውነት መሆኑን አጉልተን እናሳያቸው ። ከዚህ በተጨማሪ ንስሓ አስፈላጊና መቅረት የማይገባው ጉዳይ መሆኑንም እናሳያቸው ..." በዚህ ጊዜ እያንዳንዱ ርኩስ መንፈስ እጅግ በቁጣ ተሞልቶ ንግግሩን ከመጨረሱ በፊት አቋረጡትና ዕቅዱን በውግዘት ውድቅ አደረጉበት ። ተቃውሞአቸው እጅግ መራር ነበር ።
በዚህ ጊዜ ሊቀ መንበሩ ርኩስ መንፈሱ እቅዱን ገልጾ እስኪጨርስ ድረስ እንዲረጋጉ ምልክት ሰጣቸው ።

ይህን ተንኮል አዘል አሳብ ያቀደው ርኩስ መንፍስ ንግግሩን እንዲህ በማለት ቀጠለ ፦ " እነዚህን ነገሮች በሙሉ ለሰው ልጆች እጅግ አጉልተን ስናሳያቸው ከእኛ ጋር ተደላድለው መኖር ይጀምራሉ ፤ በምክራችንም ይታመናሉ ። በዚህ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ ንስሓ የሚያደርሷቸውን ቀና እርምጃዎች መራመድ ሲጀምሩ ንስሐቸውን ለጥቂት ጊዜ ምናልባትም እስከ ነገ ድረስ እንዲያቆዩት እናድርጋቸው ። ይህን የምናደርገውም ኃጢአትን እስከሚሰናበቱትና ፍላጎታቸውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያረኩ ነው ። በዚህ መንገድ ንስሓ ለመግባት ከተዘጋጁ በኋላ እስከ ነገ ድረስ እናቆየው እያሉ ይቆያሉ ። በመጨረሻም ቀናቶቻቸው ስለሚጠናቀቁ ንስሓ የመግባት ዕድሉን ከነጭራሹ ያጡታል ። "

እያንዳንዳቸው ብድግ ብለው ርኩሱ ጥበቡን በማድነቅ አጨበጨቡለት ። ታውቃላችሁ? ! ከዚያን ጊዜ በኋላ ሰዎች በቡድንም ሆነ በነጠላ በኃጢአት መውደቅ ስለ ጀመሩ መጨረሻ ወደሌለው ጥልቅ ጉድጓድ ይወድቁ ጀመር ። ይህ ሊደርስባቸው የቻለውም #በእግዚአብሔርና በመጽሐፍ ቅዱስ ወይም በዘላለማዊነት ስላላመኑ አይደለም #ንስሓ_የመግባት_ዕድሉን_ካገኙት_በኋላ_ለነገ_በማለት_ስላዘገዩት_እንጂ ።

ወንድሜ ሆይ ፦ እንዲህ ያለውን አጭበርባሪ ወጥመድና አረመኔያዊ ብልጠት ተጠንቀቀው!! " ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ. .." [ዕብ 4*7 ] የሚለውን የመጽመፍ ቅዱስ ቃል በውስጥህ ሸሽግ ።
አንተ ዛሬ ልትሞት ስለምትችል ንስሓህን እስከ ነገ ድረስ አታዘግየው ።
ወይም ደግሞ ነገ ሊመጣ ቢችልም ባተሌ ልትሆንና ብዛት ባላቸው ነገሮች ልትወጠር ትችላለህ ። ወይም ደግሞ ነገ ልብህ ሊደነድንና የመንፈስን አነሳሽነት ልታጣው ትችላለህ ።
ለንስሓ እጅግ ተመራጩ ጊዜ አሁን ነው ፦ " በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳን ቀን ረዳሁህ ይላልና ፤ እነሆ ፦ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው እነሆ ፦ የመዳን ቀን አሁን ነው ። " [ 2ኛ ቆሮ 6*2]

ንስሓ ትገባ ዘንድ #እግዚአብሔር አምላክ ጸጋውን ያድልህ ።
አባት ዘካርያስ ቡትሮስ እንደጻፉት

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ


✝ #እግዚአብሔርን_ተስፋ_አድርግ

ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ #እግዚአብሔርም በፍጥረታቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር በዝምታ ይሠራል። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው #የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሰራ አድርገው ያስባሉ። እነርሱ #እግዚአብሔር አይሰራም በሚያስቡበት ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ በጥልቅ እየሰራ ነው። ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ #የእግዚአብሔርን ሥራና የስራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይነቻቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል።" #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ ልብህም ይጽና #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፡፡" መዝ 26 ፥ 14።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ


†እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ራሱን በራሱ ያጎሳቁል ለነበረው ወጣት ያደረገችው ተአምርና የሰጠችው ምክር †

ራስን በራስ ማጎሳቆል የዚህ ዘመን ትልቁ ፈተና ነው፡፡ ብዙ ወጣቶች በዚህ ሱስ ይያዛሉ፡፡ ወደ ትዳር ገብተው ራሱ ከዚህ ሱስ መውጣት አቅቷቸው ከትዳር አጋራቸው ጋር የተገባ ሩካቤን የማይፈጽሙ ቊጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ እነዚህ ሰዎች ንስሓ መግባት ራሱ ያሳፍራቸዋል፡፡

እስኪ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ክሪሶስቶሞስ (አፈ ወርቅ) የተባሉ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ራሱን በራሱ ያጎሳቁል (Masturbate ያደርግ) ስለ ነበረ አንድ በዓሥራዎቹ ዕድሜ ስለሚገኝ ወጣት የጻፉትን ላካፍላችሁ፡-

“አንድ ወጣት አንድ ጊዜ የሚከተለውን ነገረኝ፡፡ በዓሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያለ ለስፖርቶች በተለይም ለትግል ልዩ ፍላጎት ነበረው፡፡ ወደ ዓሥራ አምስት ዓመቱ ገደማም አንድ የቡድን ጓደኛው ራስን ስለ መበደል ኃጢአት አስተዋወቀው፡፡ ከማፈሩ የተነሣም ንስሓ አልገባም ነበር፡፡ አንድ ቀንም ከአንድ ወር በኋላ ከታላቅ ወንድሙ ጋር እየታገሉ እያለ በወንድሙ ደረት ላይ ዘፍ ብሎ ወደቀ፡፡ መተንፈስ አልቻለም፡፡ ሞተ፡፡

“በዚህ ውስጥ ኾኖም የገዛ አስከሬኑን፣ ወንድሙና እናቱ ተደናግጠው እርሱን ለመርዳት ሲሯሯጡ፣ ነፍሱ ደግሞ በጠባቂ መልአኳ ታጅባ ከቤቱ ስትወጣ፣ ከሚኖርበት ከተማም እጅግ ከፍ ብላ በመጨረሻም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ስትኼድ ይመለከት ነበር፡፡ ከዚያም ጥልቅ በኾነ ጨለማ ውስጥ ራሱን አገኘው፡፡ ከዚያ አልፎም መጨረሻ ላይ ብርሃንንና ገነትን ተመለከተ፡፡

“ወደዚህ ብርሃን እንደ ገባም ወላዲተ አምላክን አያትና ጠባቂ መልአኩን ለምን እንደ አመጣው ጠየቀችው፡፡ መልአኩም የልጁን አሟሟት በዝርዝር ነገራት፡፡ በዚህ ጊዜ እመቤታችን ለዚያ ልጅ ‘ትድንላት ዘንድ እናትህ አጥብቃ እየለመነቺኝ ነው፤ ልጄም ጸሎቷን ሰምቷል” አለቺው፡፡ ያ ልጅ ግን በገነት ውበት ስለ ተማረከ በዚህ ይቆይ ዘንድ ለመናት፡፡ ወላዲተ አምላክ ግን ‘አይኾንም' አለቺው፡፡ ‘ለእናትህ ስትል መመለስ አለብህ፡፡ ነገር ግን አድምጠኝ፡- ከአንድ ወር በፊት ስለ ሠራኸው ኃጢአት ልትናዘዝ ይገባል፡፡ ይህ እጅግ አስጸያፊ ኃጢአት ነው፡፡ ይህን ለካህን ካልተናዘዝክ፥ ምን እንደሚያገኝህ ተመልከት፡፡' ከዚህ በኋላ ወላዲተ አምላክ የሲዖል ሥቃይ ምን እንደሚመስል እንዲያሳየው ለቅዱስ ሚካኤል አዘዘችው፡፡ የሚመለከተው ነገር እጅግ የሚያስፈራ ከመኾኑ የተነሣ፥ ልጁ ራሱን እስከ መሳት ደረሰ፡፡

“ከዚያ በኋላም ወደ ጥልቁ ጨለማ፣ ቀጥሎም ወደ ሰማያት፣ ዝቅ ብሎም ይኖርበት ወደ ነበረ ከተማ - ወደ መኖሪያ ቤቱ - ቤተሰቦቹ አስከሬኑን ከብበው ወደሚያለቅሱበት ክፍል ወረደ፡፡ በሰውነቱ ላይ ከፍተኛ የኾነ መጫጫን ከተሰማው በኋላም ነፍሱ ወደ ቦታዋ ተመለሰች፤ ዓይኖቹንም ከፈተ፡፡ ከዚያም የኾነውንና የተመለከተውን ኹሉ ለቤተሰቦቹ ነገራቸው፡፡ በኀዘን ተጎድታ የነበረችው እናቱም ይህን በሰማች ጊዜ እመቤታችን ከልጇ ከወዳጇ ስላማለደቻት አመሰገነቻት፡፡ እጅግ እያለቀሰችም ልጇን ዕቅፍ አድርጋ ሳመችው፡፡”

ፈጣኗ ደመና ወላዲተ አምላክ በዚህ ሱስ ውስጥ ያሉትን ኹሉ ከዚህ በደል ይወጡ ዘንድ ትድረስላቸው፡፡


​​✝በጸሎት ውስጥ በመትጋት ብዛት ወደ #እግዚአብሔር መድረስ ትችላላችሁ !!

#እግዚአብሔርን ከወደዳችሁት ትጸልያላችሁ ። አብዝታችሁ የምትጸልዩ ከሆናችሁ ከቀን ወደ ቀን ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እየጨመረና እየጠለቀ ይሄዳል ። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው ምክንያቱም አንድ ሰው ከወደዳችሁ ከእርሱ ጋረ መነጋገርን ትወዱታላችሁና ። ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጸሎት ነው ።

በመጸለይ እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ ። ለማለት የፈለግሁት ወደ እርሱ ፍቅር በሚመራችሁ መንገድ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ ትማራላችሁ ለማለት ነው ።

በጸሎት ውስጥ በመትጋት በጸሎታችሁ ውስጥ ወደ ምትናገሩት ወደ እያንዳንዱ ቃል ጥልቀት ልትደርሱ ትችላላችሁ ። ከዚህ በተጨማሪ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ወደ #እግዚአብሔር እየተጠጋችሁ ትመጣላችሁ ከእርሱ ጋር ለመነጋገርም ትናፍቃላችሁ ። ስለሆነም ጸሎት እንዴት #እግዚአብሔርን መውደድ እንዳለባችሁ ያስተምራችሗል ።
እንዲህ ባለ ጠባይ በጸሎታችሁ ውስጥ #ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩ አንደበታችሁ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ እየለመደ ይመጣል ። ይህ ደግሞ አዲስ ቋንቋ መማር የሚፈልግ ሰው ይመስላል ። ይህ ሰው ይህን ቋንቋ በሚገባ ባያውቅና መጀመርያ ላይ ቢሳሳትም እንኳ ይህን ቋንቋ መናገር አለበት ። ብዙ ጊዜ በመደጋገም ግን አንደበቱ ቋንቋውን ይለማመደዋል በሚገባ እስከሚጠቀምበት ድረስም ቀላል እየሆነለት ይመጣል ።


በእናንተም ቢሆን እንዲሁ ነው ይበልጥ #ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገራችሁ ስትመጡ አንደበታችሁ ይበልጥ ከእርሱ ጋር መነጋገርን እየለመደ ይመጣል ። ከዚህ በኋላ በፍቅር ስሜት ውስጥ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር መነጋገርን ታውቃላችሁ ።

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ


✝​መስጠት ወይም ልግስና ትእዛዙን ሟሟላት ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስ "እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና።" /2ቆሮ 9፥7/ እንዲል። #እግዚአብሔር የምትሰጠውን ገንዘብ ሳይሆን የመጀመሪያውን ፍሬ እና ቃል ኪዳን የሆነውን ከማዕረጎች ሁሉ የሚልቀውንና ያለ ነቀፋ በነፃነት የሚሰጠውን ፍቅር ከአንተ ይጠብቃል።

ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ የመጀመርያ ፍሬ ነው። ስለዚህ ጌታ የኤፌሶንን ቤተ ክርስቲያን በነቀፋ ንሥሓም እንዲገባ በጠራው ጊዜ ነቀፋውን የተወሰነ ኃጢአትን በመግለጽ ሳይሆን በአንድ ሐረግ አጠቃልሎ "ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።" /ራዕ 2፥4/ በማለት ነው።

#እግዚአብሔር ይህንን ፍቅር ይፈልጋል ስለዚህ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።" /ምሳ 23፥26/ አለ። ትእዛዙን መፈጸም የፍቅር ተፈጥሮአዊ ፍሬ ነው።

ውጪያዊ የንሥሓ ሕይወት ብቻ የሚኖሩ ነገር ግን ውስጣዊ ፍቅር የሌላቸው ይወድቃሉ። ምክንያቱም ሥራዎቻቸውና #ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት ፍቅር የጎደለው ነውና።
#መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሕግ ማንኛይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው መልስ "ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፣ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርሷም ባልጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትል ናት። ኦሪትና ነቢያት በነዚህ በሁለቱም ትእዛዛት ጸኑ።" /ማቴ 22፥36-40/ የሚል ነበር።

በዚያን ቀን ብዙዎቹ "ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም በስምህ አጋንንት አላወጣንም?" /ማቴ7፥22/ ይሉታል። ነገር ግን እርሱ ይህን ሁሉ ትቶ በውስጣቸው ስላለው ፍቅር ይጠይቃቸዋል።

ይህ የተአምራት እና የስጦታዎች ችግር አይደለም፣ ባሏቸው በተሰጡአቸው ስጦታዎች የተነሳ የሚጠፉ ብዙዎች ናቸውና። ለዚያ ነው ሐዋርያት ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ባወሩ ጊዜ ሁሉ ይህንን ከሁሉ ይልቅ በተሻለ መንገድ አብራርተውታል።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ


✝መስጠት ወይም ልግስና ትእዛዙን ሟሟላት ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስ " #እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና ።" /2ቆሮ 9*7 / እንዲል ። #እግዚአብሔር የምትሰጠውን ገንዘብ ሳይሆን የመጀመሪያውን ፍሬ እና #ቃል_ኪዳን የሆነውን ከማዕረጎች ሁሉ የሚልቀውንና ያለ ነቀፋ በነፃነት የሚሰጠውን #ፍቅር_ከአንተ_ይጠብቃል ።

ፍቅር #የመንፈስ_ቅዱስ የመጀመርያ ፍሬ ነው ። ስለዚህ ጌታ የኤፌሶንን ቤተ ክርስቲያን በነቀፋ ንሥሓም እንዲገባ በጠራው ጊዜ ነቀፋውን የተወሰነ ኃጢአትን በመግለጽ ሳይሆን በአንድ ሐረግ አጠቃልሎ " ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና ። " / ራዕ 2*4 / በማለት ነው ።
እግዚአብሔር ይህንን ፍቅር ይፈልጋል ስለዚህ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ ።" / ምሳ 23*26 / አለ ። #ትእዛዙን_መፈጸም_የፍቅር_ተፈጥሮአዊ_ፍሬ_ነው ።

ውጪያዊ የንሥሓ ሕይወት ብቻ የሚኖሩ ነገር ግን ውስጣዊ ፍቅር የሌላቸው ይወድቃሉ ። ምክንያቱም ሥራዎቻቸውና #ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት ፍቅር የጎደለው ነውና ።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሕግ ማንኛይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት ? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው መልስ " ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ ፣ ታላቂቱና ፊተኛይቱ #ትእዛዝ_ይህች_ናት ። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርሷም ባልጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትል ናት ። ኦሪትና ነቢያት በነዚህ በሁለቱም ትእዛዛት ጸኑ ። " / ማቴ 22*36-40/ የሚል ነበር ።

በዚያን ቀን ብዙዎቹ " ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም በስምህ አጋንንት አላወጣንም ...? " /ማቴ7*22/ ይሉታል ። ነገር ግን እርሱ ይህን ሁሉ ትቶ በውስጣቸው ስላለው ፍቅር ይጠይቃቸዋል ።
ይህ የተአምራት እና የስጦታዎች ችግር አይደለም ፣ ባሏቸው በተሰጡአቸው ስጦታዎች የተነሳ የሚጠፉ ብዙዎች ናቸውና ። ለዚያ ነው ሐዋርያት ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ባወሩ ጊዜ ሁሉ ይህንን ከሁሉ ይልቅ በተሻለ መንገድ አብራርተውታል ።

#አብነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ


✝ ሁል ጊዜ ሕሊናህን በመንፈሳዊ ነገሮች ሙላ !!

ይህን የምታደርግ ከሆነ ዲያብሎስ መጥፎ አሳብ ሊያስተዋውቅህ ሲመጣ እንኳን ደህና መጣህ የሚለው ሕሊና አያገኝም። እንደ መከላከያ መፍትሔ ይሆንህ ዘንድ ዘወትር ራስህን በሥራ ባተሌ አድርግ። ዲያብሎስ ወደ እርሱ ገብቶ የወደደውን ዘር እንዳይዘራበት ሕሊናህን ባዶ አታድርገው።

መንፈሳዊ ንባብ ሕሊናን በሥራ ለመጥመድና መጥፎ አሳቦችን ለማራቅ ብቻ ሳይሆን ሌላም ታላቅ ጥቅም አለው። ንባብ ሕሊናን በተመስጦ ሊሞላ የሚችል መንፈሳዊ ዘዴ ከመስጠቱም በላይ ተቃዋሚ አሳቦችን የሚያጠፋውንና #እግዚአብሔርን መውደድ የሚያስችለውን ስሜት በልብ ውስጥ ያጎናጽፋል።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ


ችው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በላይ በክልላችን ውስጥ ያለው ጭፈራ ቤት ይሻላል!" ሲባል እኮ በጭብጨባና በፉጨት እንዲሁም በዝምታ ድጋፋችን የገለጥን ብዙዎች ነን! ኧረ መልሱ አንዲት ቤተክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው!?
~
እህቶች ለምንላቸው የውጪ አብያተ ክርስቲያናት ይቅርና በአንዲት እናት የምንጠራም እርስ በእርሳችን ገና አልተዋወቅንም፣ አልተረዳዳንም፣ ችግራችን አልተካፈልንም። ይህንን ወዴት ያደርሰን ይሆን!? መፍትሔውስ ምን ይሁን!? በቃ ዝም እንበል!? ወንድም እህቶቼ የአሐቲ ቤተክርስቲያን እና የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ትርጉም ገብቶናል ብላችሁ ታስባላችሁ!? ገና የአንዲት ቤተክርስቲያን ትርጓሜ አልገባንም!! አልተረዳንም!! ሁላችንም ከዘረኝነት እንውጣ!! ዋሽቶ የማያውቅ የእግዚአብሔር ቃልም እንዲህ ይላል፦ "እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ # ሰባትንም_ነፍሱ_አጥብቃ_
ትጸየፈዋለች ፤
፩.ትዕቢተኛ ዓይን፥
፪.ሐሰተኛ ምላስ፥
፫.ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
፬.ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥
፭.ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
፮.በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፥
፯. # በወንድማማች_መካከልም_ጠብን_የሚዘራ ።" ምሳ.6፥16-19
~
እግዚአብሔር ለሁላችን ይርዳን!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ወለወላዲቱ ድንግል፤
ወለመስቀሉ ክቡር።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
መስከረም 15 - 2013 ዓ.ም Fikre Abrha
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


"አኃት አብያተ ክርስቲያናት" እና "አሐቲ ቤተክርስቲያን"
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
▬▬▬▬▬▬▬
ይህንን ጽሑፍ በተለያየ ምክንያት ለአቅመ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ያልደረሳችሁ ሰዎች እንድታነቡት አይመከርም!! ፅሑፉ ከተፃፈበት ዓላማ (intention) ውጪ እንደ ፍላጎትህ አድርገህ ማንበብ ነውር ነው!!
~
"አኃት አብተ ክርስቲያናት" ትርጉሙ ምን ማለት ነው!?
~
ምናልባት የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት የተማርን ሰዎች ይህንን ጥያቄ ሲጠየቅ በጣም ቀለል አድርገን "እንዴ! አኃት አብያተ ክርስቲያናት እማ ግብፅ፣ ሶርያ፣ አርመን፣ ሕንድ፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ ናቸው፤ ይህንን ምን ጥያቄ ያስፈልገዋል!?" ልንል እንችላለን። ነገር ግን ከምር የእህትማማችነት ትርጉም ገብቶናል ወይ!?
~
አኃት የሚል ቃል በራሱ የግእዝ ቃል ሆኖ ትርጉሙም እህትማማቾች ማለት ነው። እንደሚታወቀው እህትማማቾች ሲባል መንትዮች ሊሆኑም ላይሆኑም የሚችሉ፣ በዕድሜ ሊበላለጡም ላይበላለጡም የሚችሉ፣ እኩል የሆነ መልክና ቁመና ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም የሚችል ነገር ግን የአንድ ደም ዘር ያላቸው፣ ከሌላው በፊት ቀድመው የሚተዋወቁ፣ ደግና ክፉውን አብረው በኖሩበት ጊዜ ያሳለፉ፣ የአንዷን እህት ደስታ ደስታቸው የሚያደርጉና ሕመምዋም ተጋርተው የሚታመሙ ማለት ነው። እውነተኞች እህትማማቾች አንዷ እህታቸው ሲቸግራት ችግርዋን ባላየ ባልሰማ የሚያልፉ ሲመቻት ደግሞ ልታይ ልታይ የሚሉና በደስታዋ ቀን የሚያኮርፉ አይደሉም።
~
የሆነ ሆኖ ሁልጊዜ ሸምድደንና አቀላጥፈን እንደምንናገረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እህቶች የሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግብፅ፣ ሶርያ፣ አርመን፣ ሕንድና በኋላም ኤርትራ ናቸው። እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ልደታቸው የተለያየ፣ አመጣጣቸው ለየቅል፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስትና ያልተቀበሉ ሲሆኑ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ከተቀበሉ በኋላ ግን # አንድ ዓይነት ዶግማ (Doctrine) ያላቸው ናቸው። ይህ ማለት ግን የቀኖና እና የሥርዓት ልዩነት የላቸውም ማለት አይደለም። እንደ አንዳንዶቹ አተረጓገም አኃት ማለት መንትዮች ብቻ ሳይሆን እንደተሰጣቸው ጸጋ መጠን ያላቸውን መክሊትና አቅም የሚጠቀሙ ናቸው።
~
በእህትማማችነት ኑሮ ውስጥ ብዙ ጸጋና መክሊት የሌላት እህት ብዙ ጸጋና መክሊት ላላት (ለተሰጣት) እህት ለምን ይህንን ነገር ተሰጠሽ?፣ ለምን ይሄንን ንዋይ ቅዱስ ትጠቀሚያለሽ?፣ በእኔ ዘንድ የሌለ ባንቺ ቤት እንዴት ሊኖር ይችላል? ልትላት አትችልም፤ ምክንያቱም ይህንን # ምቀኝነት_ነው ! የእውነተኛ እህትነት ጠባይም አይደለም። በተመሳሳይ መልኩም ብዙ ጸጋና መክሊት ያላት (የተሰጣት) እህት ብዙ ጸጋና መክሊት ለሌላት እህት ለምንድነው ይህንን ነገር የማታደርጊው?፣ ለምን ይሄንን ንዋይ ቅዱስ አትጠቀሚም?፣ በእኔ ዘንድ ያለ ጉዳይ ባንቺ ቤት እንዴት አይኖርም? ልትላት አትችልም። ምክንያቱም ይህንን # ትዕቢት_ነው! የእውነተኛ እህትነት ጠባይም አይደለም። ስለዚህ ሁሉም ተከባብረው አንዷ የአንዷን ጸጋ አክብራ ትኖራለች። ከዚህ በተጨማሪም አንዷ እህት ከቸገራት ሌሎች እህቶቿ ይረዷታል! በአከባቢዋ ካሉ ጎረቤቶቿ ይልቅ በሩቅ ያለች እህቷ ልትደርስላት ያስፈልጋል። የእህትማማቾቹ ልጆችም በደምብ ተዋውቀው ዝምድናቸውን አጠናክረው ሊያስቀጥሉና ሊተባበሩ ይገባል።
~
በዘመናችን እየታየ ያለው ሁኔታ ግን በጣም ያሳፍራል። አባቶቻችን በዓላማ ያደረጉት ቁምነገር እንደ ምናምንቴ ቆጥረን ለዓላማቸው "አኃት" ብለን ከመናገር የዘለለ ምንም ፋይዳ እንደሌለው እየተመለከትነው ነው። አብዛኞቻችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እናትነት ሥር ተጠልለን የምንገኝ ልጆች እንኳንስ የእናታችንን እህቶች አውቀን ለልጆቻቸው ራርተን እንደ ወንድሞቻችን ልናያቸው ይቅርና የአንዲት እናት ልጆች ሆነንም ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን መራራት አቅቶናል፤ ችግራቸው ችግራችን አድርገን መቀበል አልቻልንም፤ እየተገፉ፣ እየተጨነቁ፣ እየተሰቃዩና እየተገደሉ ያሉ ወንድምና እህቶቻችን የእናታችንን መለያ ሰንደቅ ስለያዙ መሆናቸው ገና አልገባንም፤ ያሳዝናል!
~
እንዴ! እየተገፋና እየተገደለ ያለው ወገንህ እኮ አንተ የምታመልከው አምላክ ስላመለከ ነው፤ አንተ የምታከብራቸው ቅዱሳን ስላከበረ ነው፤ አንተ በኩራት በአንገትህ ያሰርከው ማዕተብ ስላሰረ ነው። ሁልጊዜ ቅዱሳን አባቶቻችን ባስቀመጡት በዘወትር ጸሎታችን ላይ ከውስጣችን አምነን "ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት፤ ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን" እያልን እየጸለይን በተግባራችን ግን እየካድነው ነው፤ ፈጽመን አናምንም። "አሐቲ (አንዲት)" ማለት ምን ማለት ነው!? በአንድ አከባቢ ብቻ የተወሰነች ማለት ነው እንዴ!? ቤተክርስቲያናችን ዓለም አቀፋዊት (Catholic) ናት! በሁሉም ክፍላተ ዓለም ቁጥር ልክ መርበቦችዋ ዘርግታ የምትገኝ የእግዚአብሔር መርከብ ናት። እንዲህ በዝታ ተባዝታ እያለች አንዲት መባሏ ታድያ ምሥጢሩ ምንድን ነው!? ከተባለ መልሱ በየትም ትኑር የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ # አካል ስለሆነች ነው። እኛም በእናታችን ቤተክርስቲያን በኩል የክርስቶስ አካላት ሆነናል ማለት ነው።
~
ታድያ በዚህ ከተስማማን አንዲትና አካላችን ያልናት ቤተክርስቲያን ስትመታ የማናለቅሰው፣ ስትንቋሸሽ የማንሳቀቀው፣ ስትወረር የማንጮኸው ለምንድነው!?
# ምናልባት_ከኣካሏ_ተቆርጠ
ን_ወድቀን_ተለይተን_ይሆን_እንዴ !? ወይስ በአካላቶቿ እያለን ሽባ (paralysis) ሆነን ነው!? እስኪ ራሳችንን እንፈትሽ!?
~
እናት ቤተክርስቲያን የኦሪት ታሪክ፣ የዘመነ ሐዋርያት ታሪክ፣ የዘመነ ሰማዕታት ታሪክ፣ የዘመነ መናፍቃን ታሪክ፣ የዘመነ ጻድቃን ታሪክ ብላ ያስተማረችን የታሪክ ተመራማሪዎችና አዋቂዎች ለመሆን ብቻ ነው እንዴ!? በህይወታችን እንድንኖረው አይደለም!? ታድያ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው እሩቅ ካለችውና አካላችን ከሆነችው እህታችን ይልቅ በቅርብ ከምናውቃቸውና ከማይመስሉን ጎረቤቶቻችን የወገንነው!? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ ይላል፦ "በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ
# አንድ_ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር
# አንድ_አምላክ የሁሉም አባት አለ።" ኤፌ.4፥4-6
~
እስኪ በሞቴ መልሱልኝ ልጠይቃችሁ! ማን ነው አሁን ስለ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ስማቸውና ታሪካቸው በዝርዝር አውቆ # በሶርያ በግፍ እየተጨፈጨፉና በረሃብ እያለቁ ያሉ ወገኖቹ (አካላቱ) የሚጨነቅ!? ማን ነው በግብፅ ስለታረዱት ኦርቶዶክሳውያን የሚገደው!? ማናችን ነን ስለ ኤርትራ፣ ስለ ህንድና ስለ አርመን ቤተክርስቲያን አስበን የምናውቀው!? ይቅርታ አድርጉልኝና ነገሩ አሰፋሁት መሰለኝ! ወደ እህቶቻችን አብያተ ክርስቲያናት ዘልዬ ገባሁ! ለካ በአንድ የቤተክርስቲያን መጠርያ ስም የምንጠራ አካላትም ተጨካክነናል! ለካ በሶማሌ ክልልና
# በሆሳዕና_ከተማ ላለችው የእኛው ቤተክርስቲያንም ማሰብ ትተናል! ለካ ከክልላችን ውጪ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በአፋር... ስላሉት አብያተ ክርስቲያናትም በፖለቲካው ጦስ ምክንያት ተቆራርጠናል! ያሳዝናል! ደግሞ እኮ አናፍርም ሁልጊዜ "ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን..." እያልን ነው የምንጸልየው! አንድ መሆኗ መቼ ነው ያመንነ

​ው? "በሌላ ክልል ላይ ካለ


✝ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ መንፈሳዊ ቻነል ምንጽፋቸው ከአቡነ ሺኖዳ መጻሕፍት መሰረት አድርገን ነው።

📚እንደሚታወቀው በቤተ ክርስቲያን ታርክ ሁለት ታላላቅ ትምህርት ቤቶች ነበሩ ። አንደኛው የእስክድርያ ሲሆን ሁለተኛው የአንጾኪያ የሥነ መለኮት ትምህርት ቤት ነው ።

የእስክንድርያው ትምሕርት ቤት ጌታችንን በተመለከተ የሚሰጠው ትምህርት ከአምላክነቱ ጀምሮ ሰው ወደ መሆኑ የሚወርድ የትምህርት አሰጣጥ ዘይቤ ሲሆን የአንጾኪያው ትምህርት ቤት ግን ከሰውነቱ ጀምሮ ወደ አምላክነቱ የሚያመራ የትምህርት አሰጣጥ ዘይቤ ይከተላሉ ።

እነዚህ የትምሕርት አሰጣጥ የራሳቸው ተጽዕኖ ነበሩዋቸው ። የእስክንድርያው ትምሕርት ሰሚውን ወደ ፈሪሃ እግዚአብሔር ሲመራ የአንጾኪያው ግን በክርስቶስ ሰውነት ላይ ያተኮረ ትምሕርት የሚሰጥ በመሆኑ ወደ ፍቅረ #እግዚአብሔር የሚመራ ነው ።

የአንጾኪያው እነ ቅዱስ ኤፍሬምን ፤ እነ ቅዱስ ዩሐንስን አፈወርቅን እነ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግን ሲያፈራ ። የእስክንድርያው መንፈሳዊ ትምህርት ቤት እነ ቅዱስ አትናቴዎስ ፤ እነ ቅዱስ ቄርሎስ እና በቅርብ ደግሞ ብጹዕነታቸውን አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊን አፍርቷል ።
የብጹዕነታቸው ትምሕርት ለግብጽ ምእመን ብቻ ሳይሆን በአለም ያሉ ክርስቲያኖች በሙሉ እሚጠቀሙበት ሆኗል ፡፡ በርካታ መጽሐፍትን የጻፍ ሲሆን ምእመኑ ፈርሃ #እግዚአብሔር እንዲኖረውና ዲያብሎስ ከሚያመጣው ፈተና እራሱን በልምምድ አሸንፎ #ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት ኖሮት ምግባር ሰርቶ ዋጋውን ከክርስቶስ እንዲቀበል ማድረግ ነው ።

የዚህ ፔጅ ተከታታዮች በሙሉ የምንጽፍላችሁን የብጹዕነታቸውን ትምህርት በጥሞና እየተከታተላችሁ ቀስ በቀስ እራሳችሁን ወደ መንፈሳዊነት እንድታቀርብ ነው ።

መንፈሳዊ ሰው ማለት አገልግሎት ላይ ያለ ብቻ አድርገን የምናስብ ጢቂቶች አይደለንም ። መንፈሳዊነት ማለት ግን አንድ ሰው አምኖ ከተጠመቀ በሗላ የአምላኩን ትእዛዝና ፍቅር እየጠበቀና እየተጋደለ ምግባር ትሩፋት እየሰራ #የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቅ ማለት ነው ። ብዙዎቻችን እንፈልጋለን ግን ከተጫነብን የዓለም ገለባ መውጫ ቀዳዳ ጠፍቶብን ስንኳትን እንገኛለን ፡፡

ብጹዕነታቸው ልዩ የሚያደርጋቸው አምላክ በሰጣቸው ጸጋ ተጠቅመው አሁን ያለንበትን የዓለምን ክፍ ስራ በመግለጥ እንድናውቅበትና እንዴት ድል ነስተን እንደምናሸንፈው ረቂቁን አጉልተው በሚገባን መልኩ ፅፈው አስተላልፈውልናል ።

እኛም #እግዚአብሔር እንደፈቀደ እያቀረብን እንገኛለን ። ይህን አታላይ የሆነ አለም በጥንቃቄ ለመሻገር በአሁኑ ግዜ ወደ እግዚአብሔር መቅረቡ መልካም ነውና በይበልጥ መጸሐፎቻቸውን እየገዛችሁ ብትጠቀሙ ለህይወታችሁ ጥሩ ነው ።

ቻነሉን ከወደዳችሁት ለሁልንም እንዲደርስ ሼር እያደረግን ወደ ጓደኞቻችን እንድናዳርስ #በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡

#የአቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
በረከታቸው ይደርብን !! አሜን🙏


✝ ቻይ እና ትዕግስተኛ የሆነ ሰው ይጸልያል ስለሚሰጠውም የእግዚአብሔር መልስ አይጨነቅም ። እግዚአብሔር ጸሎቱን እንደሚሰማው እርግጠኛ ነው ። ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ጥበብና ፈቃድ እንደሚሆን በተገቢው ጊዜና መንገድ መልስ እንደሚሰጠው በማመን ለእግዚአብሔር ፍቅር ይተዋል ። አንዳንድ ሰዎች ይህ መሰል ትዕግሥት የላቸውም ። እግዚአብሔርን መውቀስ እና ከእርሱ ስሕተት መፈለግ እንጂ መጠባበቅ አይችሉም ። እርሱን ይወነጅሉታል እርሱ ግን እጅግ ይታገሳቸዋል ወቀሳቸውንም ይሸከማል ። እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር ለእነርሱ እንደሚሰራ ማመን አለባቸው ።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ


* ትውፊት *
ከአቡነ ሺኖዳ መፅሀፍ የተወሰደ ። ትውፊት ከመፅሀፍ ቅዱስ ቃል ቀጥሎ ስለክርስትና የሚነግረንና ከቅዱሳን ሀዋሪያትና ከአባቶቻችን የተቀበልነው ትምህርት ነው ።ፕሮቴስታንቶች በትውፊት አያምኑም ነገር ግን መፅሀፍ ቅዱስን ብቻ የሙጥኝ ይላሉ ።በዚህ ሁኔታ ቤተክርስቲያን ከቀደሙት አባቶች የተቀበለቻቸውን ክርስቲያናዊ ውርሶች ማለትም እንደ የሀዋሪያት መፃህፍት ፣ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጽሁፎችና የቅዱሳን ሲኖዶሶችን ውርሶችን ሳያገኟቸው ቀርተዋል።እስቲ ትውፊትን ከመፅሀፍ ቅዱስ ጋር እያገናኘን እንይ ። ለምሳሌ ቅዱስ ጳውሎስ ሙሴን የተገዳደሩትን የሁለቱን ጠንቋዮች ስም "ኢያኔስና ኢያንበሬስም " በማለት ፅፏል ። /2ጢሞ 3:8/ የነዚህ ጠንቋዮች ስም በሙሴ መፃህፍት በጭራሽ አናገኝም። ሀዋሪያው እነዚህን ስሞች ያገኘው በትውፊት ነው ።ወንጌል ወይም መልዕክት ሳይፃፍ ብዙ አመታት / ምናልባትም ወደ 20 ግድም / አልፏል ። በዚያን ጊዜ ወንጌል ይሰበክ የነበረው በትውፊት ነው ።ጌታ ትምህርቱን ሲጀምር " ዘመኑ ተፈፀመ የእግዚአብሔርም መንግስት ቀርባለች ንስሀ ግቡ በወንጌልም እመኑ ይላቸው ነበር ። /ማር 16:15/ ሆኖም በዚያን ጊዜ የተፃፈ ወንጌል አልነበረም ። ነገር ግን ወንጌል አፍአዊ ነበር ። ጌታችን ራሱ ወንጌልን የሰበከው በትውፊት ነበር ።ጌታችን ያደረጋቸው ድንቆች ሁሉ በመፅሀፍ ቅዱስ አልተፃፉም ። የሉቃስን ቃል መጥቀስ ለዚ በቂ ነው ። " ፀሀይም በገባ ጊዜ በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙ በሽተኞችን ሁሉ እጁን ጭኖ ፈወሳቸው ። " /ሉቃ 4:40/ ታዲያ የታመሙት ስንት ናቸው ? የህመሞቹስ አይነት ስንት ነው ? ወንጌላዊው ማቴዎስም ኢየሱስ በየምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግስቱንም ወንጌል እየሰበከ በህዝቡም ያለውን ደዌና ህመም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር። /ማቴ 4:23/ይለናል ። ሆኖም የዳኑበት ዝርዝር ሁኔታና የምኩራብ ትምህርቶቹ አልተፃፉም ።በማርቆስ ወንጌልም ወደ ቅፍርናሆም ሄደ በምኩራብ ገብቶም አስተማረ እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው ነበርና በትምህርቱ ተገረሙ ይላል ። /ማር 1:21/ ታዲያ አይሁድን ያስደነቀው ትምህርት ምን ነበር ? አልተፃፈም ።ትውፊት ሀዋሪያት ያስተማሩት ትምህርት ነው ። ብዙ ሀዋሪያት መልዕክት አልፃፉም ። ታዲያ ትምህርታቸው የታለ ? የተሰጣቸውስ ተስፉ የት ደረሰ ? በነቢያት የተነገረው የመንፈስ ቅዱስ ስራስ የታለ ? የፃፉትም ሀዋሪያት የፃፉትን ብቻ ነው የተማሩት ማለት የማይታመን ነው ።ለምሳሌ ይሁዳ ባለ 1 ምዕራፍ መልዕክት ብቻ የተማረው ማለት የማይቻል ነው ። ያልፃፉትስ ሀዋሪያት አልተማሩም ሊባል ነውን ? ከነርሱ ምንም ቃል አላገኘንም ሊባል ነውን ? ለቤተክርስቲያንስ ምን ትተው አለፉ ? ያለጥርጥር በብዙ ሁኔታ ትምህርታቸውን ለእኛ በትውፊት ደርሶናል ።ትውፊት ብዙ ስርአቶችን እና ትምህርቶችን ጠብቆ አቆይቶልናል።


አንድ በተቆለፈ ሳጥን ላይ ተቀምጦ የሚለምን ለማኝ ነበር ። ከእለታት በአንዱ ቀንም በዚያ መንገድ የሚያልፍ ሰው ወደሱ ጠጋ ብሎ ለመሆኑ የተቀመጥክበትን ሳጥን ከፍተህ ውስጡን አይተህ ታውቃለህን ? ብሎ ጠየቀው ።፡ለማኙም አረ አላቅም አለና ከፍቶ ቢያየው ሳጥኑ በወርቅ በብር የተሞላ ነበር ። እኛም እንደዛ ነን እኔ ዋጋ የለኝም አልረባም ብኖር ባልኖር አልጠቅምም እንላለን ።፡ግን አንድም ቀን ውስጣችንን አይተን አናውቅም ።፡ውስጣችን ግን ወርቅ በመሰሉ አላማዎች እንቁ በመሰሉ በጎ ሀሳቦች የተሞላ ነው ። ማይልስ እንዳለው የአለም ውድ ሀብት ያለው በአረብ ሀገራት የነዳጅ ቦታ ውስጥ አይደለም የአለም ውድ ሀብት ያለው በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ቦታዎች ውስጥም አይደለም ።፡የአለም ውድ ሀብት ያለው የመቃብር ቦታዎች ውስጥ ነው ።፡ም/ቱም ብዙዎች ወደዚህ አለም ይዘው የመጡትን አላማና ራዕይ አውጥተው ሳይኖሩትና ለአለም ሳያበረክቱት ስለሚሞቱ ነው ። ማግኘት ማጣት የጊዜ ጉዳይ ነው ። ማንም ባዶ የለም ምንአልባት አሁን ባዶ እጃችንን እንሆን ይሆናል ነገር ግን ባዶ ልባችንን አልተፈጠርንም ።ለዝች አለም የምናበረክተው አንዳች ነገር በውስጣችን አለ ። እኛ ምን አልባት ለቤተሰቦቻችን በስህተት የተወለድን ይመስላቸው ይሆናል ። ነገር ግን በስላሴ ዘንድ መለኮታዊ አጀንዳ ተይዞልን ለአለማ ተወልደናል ። አለም ላይ ላሉ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳብ የያዝን አለን ፡ ለተዘበራረቀው ፖለቲካችን የተስተካከለ የአመራር ብቃት ያለን አለን ፡ እየጠፉ ላለው ስነፅሁፋችን የተባ ትንቱግ ብዕር የጨበጥን አለን ፡ ብቻ ሁላችንም ውስጥ ውድ ሀብት አለ ። እኛ ግን ቆልፈንበት ተቀምጠናል እናውጣው እንጠቀምበት


ምክረ አበው dan repost
መምህራችን ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በላከው ሁለተኛ መልእክቱ ምዕራፍ 13 ውስጥ የጠቀሰልንን ሁልንም የፍቅር ዓይነቶች ተግባራዊ እናድርግ።

➡️"ፍቅር ሁልን ይታገሳል፣" ሰዎችን ሁሉ በትዕግስት ቻል።

➡️"ፍቅር አይቀናም፣" በሌሎች ላይ ላለመቅናት እንለማመድ።

➡️"ፍቅር ራሱን አያስመካም፣" አንድ ሰው ሌሎች ሰዎች ሊያገኙት በሚችሉት ነገር ላይ ሊመካባቸው አይገባም።

➡️"ፍቅር አይታበይም፣" እግዚአብሔር አምላክ ትዕቢተኞችን ስለሚቃውምና ለትሑታን ጸጋን ስለሚሰጥ ትዕቢት አደገኛ ማነቆ ነው።

➡️"ፍቅር ክፉ ነገር አያሳስብም፥" ሰውን የሚወድ ሰው በክፋት አይናገርም በትሕትና እንጂ ልክ ጣፋጭ ውኃ እንደሚያመነጭ ንጽህ ምንጭ።

➡️" ፍቅር ብቻየን ይድላኝ አይሰኝም፣" ሰዎች የሚወድ ሰው ራሱን ወዳድ አይደለም ሌሎችን ይወዳል እንጂ፡እርሱ ለእነርሱ መሥዋዕት ይሆናል ያለውን ሊሰጣቸውም ዝግጁ ነው ራስ ወዳድነት የብዙ ችግሮች ምክንያት ስለሆነ እርሱን ከእናንተ አርቁ።

➡️"ፍቅር አይበሳጭም፣" ብስጭት(ቁጣ) የእግዚአብሔርን ጽድቅ ስለማይሰራ አትበሳጩ።

➡️"ፍቅር ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፣" ሌሎች ሰዎችን የሚጎዳ ውድቀት አይመኝም። ሕሊናቸው ንጹህ ለሆኑ ሰዎች ሁሉም ነገር ንጹህ ነው። ንጹሓን ሰዎች ከራሳቸው ይልቅ ሌሎች ሰዎችን ያስቀዳማሉ።
➡️"ፍቅር ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል ፣"ፍቅር ያለው ሰው ሰዎች ስኬት ወይም ሀብት ወይም ደስታ ወይም ልጆች ወይም በሌሎች እግዚአብሔር በሚሰጣቸው በረከቶች ይደሰታል ።ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ ከምያለቅሱም ጋር አልቅሱ።"ሮሜ11፥15

➡️"ፍቅር ሁሉን ይታገሳል ፣" ታጋሽ ሰው ለመሆን ተለማመድ። እጅግ ከባድ የተባሉ ስሕተቶች ላይ ብትወድቅም እንኳን ቁጣህ ፈጥና አትቀጣጠል የሰዎችን ፍቅርና ክብር ታጣለህና። ለመታገስ የሚቻለው ለማፍቀር ሲቻል ነው። ስለዚህ ሁሉንም ነገሮች ሁሉንም ሁኔታዎችና ሁሉንም ሰዎች ያለ ምንም ማማረር ታገሡ።

➡️"ፍቅር ሁሉንም ያምናል፥" ፍቅር ቀላል ነው እንጂ አታላይ አይደለም ፍቅር ጠቢብና አርቆ አሳቢ ነው።ተስፋ የሚያደርገው ለሌሎች ሰዎች መልካምነት ነው ።

➡️" ፍቅር በሁሉ ይጸናል ፣" ከእርሱ ጋር የሕይወት አክሊል ስለሚመጣ ትዕግስትን ተለማመድ። ሌሎች ሰዎችን መቻልም ተለማመድ እነዚህ ሰዎች ችግር ፈጣሪዎች ቢሆንም እንኳ ይህን ስታደርግም ትዕግስትህ መልካም ነገር እንደሚያሰገኝልህ በማወቅ ይሁን።

➡️"ፍቅር ለዘላለም አይወድቅም ፥" የተለያዩ ፈተናዎችና መከራዎች ቢገጥሙም እውነተኛ ፍቅር ፈጽሞ አይወድቅም፡በማንኛውም ፈተና ፊት በጽናት ይቆማል እንጂ: -"ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና ፥........ብዙ ውኃ ፍቅርን ይጠፋት ዘንድ አይችልም ፈሳሾችም አያሰጥሟትም ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ ይንቁታል።"ምሳ 8፥6-7
#ጸሎት_ንሰሐና _ተምስጦ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
#አቡነ_ሺኖዳ_ሳልሳዊ


✝ደካማነትህን አስታውስ፣ ያን ጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም።

📚የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ፣ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል፡፡ በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል። ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል።

📚ሞት እንዳለ አስታውስ፣ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ "ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው።" መክ. 1፥14 ማለትን ትረዳለህ።

📚 በእግዚአብሔር ፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፣ ያኔ ኃጢአት አትሠራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና።

📚 ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ። በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህም በከንቱ በመኖር አታጠፋውም፣ "በዋጋ ተገዝታችኋልና..." 1ቆሮ. 6፥20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ።

📚በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፤ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ።

📚 በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ
ዘወትር አስታውስ። ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ።

📚በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግሥተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ። ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና።

📚 የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ። በውስጥህ ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን። ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ


✝ የተስፋ ቃላት

📖 እኛ ዛሬ ወደፊት የምንኖርባት #የእግዚአብሔር ሀገር በተስፋ ዓይኖቻችን ልንመለከት እንጂ ይሁን ሁካታና ግርግር የበዛበት ዓለም ልንመለከት አይገባም።

📖 ለእኛ በጣም አስቸጋሪ መስሎ የሚታየን ችግር #በእግዚአብሔር ዘንድ መፍትሔ አሉትም። ማንኛውም የተዘጋ በር ለመክፈት በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ቁልፍ አንድ ብቻ ሳሆን ብዙ ቁልፎች ናቸው። በእንደዚህ ዓይነት መንገድ የተከፈተውን ማንም ሊዘጋው አይችልም ፡፡ ራዕ 3፥7።

📖 ተስፋ ፍርሀትን ጭንቀትን ግራ መጋባትን በመከላከል ዕረፍትን ይሰጣል።ተስፋ ዕረፍትን ከመጠቱ በላይ በተስፋ ደስ እንዲለን ተነግሮናል። ሮሜ 12፡2

📖 መጥፎውን ወደ በጎ መቀየር የሚቻለውን #የእግዚአብሔር አሠራር ሳትይዝ ወደ ችግሮችህ ብቻ አትመልከት።

📖 #እግዚአብሔር ሁሉም አጋጣሚዎች እርሱ በወደድው መንገድ ማስኬድ ይቻለዋል።

📖 በሰዎች ድካም ሊደረግ የማይቻለው ሁሉ #በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ይቻላል። የሰዎች ጥበብ ሊወጣው ያልቻለውንም #የእግዚአብሔር ጥበብ ያመጣዋል።

📖 ምንጊዜም በመለከታዊ ዕርዳታ የተከበብክ ስለሆንህ ብቻህን ላለመሆንህ እርግጠኛ ሁን፡፡
የሰማያት ወዳጆቻችንና ቅዱሳን ሁሉ በአንተ ዙርያ ሁነው ስለ አንተ እንደሚማልዱም እወቅ።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
የተስፋ ሕይወት ከሚለው መጽሐፋቸው


አባቶቻችን እንዲህ አሉ +
በኀዘን ጊዜ የማያጉረመርሙ ከንፈሮች ከቅዱሳን ሰማዕታት እኩል ናቸው - #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
በሃይማኖት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች ከጠየቃችሁኝ አንደኛው ትሕትና ሲሆን ሁለተኛውም ትሕትና ነው:: ሦስተኛው ደግሞ ትሕትና ነው - #ቅዱስ_አውግስጢኖስ
ሕይወታችን ለሌሎች የሚያበራ ቢሆን ኖሮ ስብከት ባላስፈለገ ነበር:: በምግባራችን መመስከር የምንችል ብንሆን ኖሮ ቃላት ባላስፈለጉ ነበር:: እውነተኛ ክርስቲያኖች ብንሆን ኖሮ አረማውያን ባልበዙ ነበር - #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ሰዎች ወደ ተራሮች ከፍታ ይወጣሉ ወደ ኃይለኛው የባሕር ሞገድና ወደ ውቅያኖስ ስፍሐት ይቀዝፋሉ : የከዋክብትን ክበባዊ ዑደት ያደንቃሉ [ግሩምና ድንቅ የሆኖ የተፈጠረ] ሰውነታቸውን ግን ሳያደንቁ ያልፉታል:: -
#ቅዱስ_አውግስጢኖስ
"ጌታ ሆይ ክርስቲያን አድርገኝ ክርስቲያን ሆኜ ልኑር ክርስቲያን ሆኜ ልሙት ዳግም ልትፈርድ ስትመጣም ክርስቲያን ሆኜ ልገኝ" #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
Deacon Henok Haile

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

19 704

obunachilar
Kanal statistikasi