ይድረስሽ ላንች ነው!!
➖➖➖➖➖➖
''አንች ስደተኛ''
--------------------
ቆርጠሽ የዘመትሽው ረጅሙን ጉዞ፡
መንገድሽ በሙሉ እሾህ ተጎዝጉዞ፡
አእምሮሽ ናፍቆትን ትዝታን አርግዞ፡
በሰላም ተመለሽ፤
ልብሽ ጥሩ አቂዳ እጅሽ ገንዘብ ይዞ፡
አሏህ ያስደስትሽ፤
ድካምሽን ክሶ ሀዘንሽን ሰርዞ፡
ህይወትሽ ሳቅ ይሁን፤
መከፋት መታረዝ ስቃይ ተደልዞ፡
በምትደጉሚያቸው የሚጠፋ ስምሽ፡
በተጠጋሻቸው የሚሰበር ቅስምሽ፡
ራስሽን ትተሽ ለሌላ እምትኖሪ፡
ለተራበው ሁሉ ቀለብ የምትሰፍሪ፡
ማንም ምንም ቢልሽ የማታሳፍሪ፡
ግን የዋህነትሽ በጣም ስለበዛ፡
ሁሉም ሰው ተጠቅሞሽ የጣለሽ ወደዛ፡
ከረሀብ ያዳንሽው የሚያይሽ በዋዛ፡
ንፁህ መስሎ ቀርቦሽ በምላሱ ዋሽቶ፡
የገዛሽለትን ያንችን ስልክ ዘግቶ፡
አላማው ሲሳካ የሚጠፋ ሸሽቶ፡
ሌላን እንዳታምኝ አንችን አበላሽቶ፡
ሁሌ እማይረሳ መጥፎ ስራ ሰርቶ፡
እሱ ግን በድብቅ ህይወቱን መስርቶ፡
ከአንች ገንዘብ ዘርፎ ንፁህ ሀብት አፍርቶ፡
በማይሆን አላማ አንችን አሳስቶ፡
ተጨባጭ በሌለው በነገር ቀስቶ፡
ይገርማል ጭካኔው የዚህስ ይከፋል፡
ልቧ አልበቃው ብሎ ገንዘብም ይዘርፋል፡
ከዚያ ሁለቱንም ያለርህራሔ ይዞባት ይጠፋል፡
መለወጥ ፈልገሽ ከሀገር የወጣሽ፡
ችግሩ መከራው ናፍቆቱ የቀጣሽ፡
እቅድሽ ተሳክቶ አሏህ ሰላም ያምጣሽ፡
የስኬትን ፅዋ ጌታችን ያጠጣሽ፡
አትንከራተች ምነው ምን በወጣሽ፡
ላንች እምመኘውን ልመርቅ አሚን በይ፡
አሏህ ነው ፈፃሚው በደስታ ተቀበይ፡
ከትላንት እስከ አሁን በጣም ስለማውቅሽ፡
አሚን በይ እህቴ እስኪ ልመርቅሽ!!
በሄድሽበት መንገድ እግርሽ በረገጠው፡
ባረፍሽበት ቦታ ልብሽ በመረጠው፡
የተሻለ ይቅናሽ በሁሉም አቅጣጫ፡
ወርቅ ይነስነስበት የአንች መቀመጫ፡
መልካም ይሁንልሽ የክፋት ማምለጫ፡
ተውሒድ ሱና ይሁን የአንች መገለጫ፡
አንች ከፍ ስትይ ምቀኛሽ ይንጫጫ፡
የበደለሽ ሁሉ ይሁን መወጣጫ፡
ረግጠሽው ውጭ ወደ ስኬት ጣራ፡
ጠላት ይክሰምበት የሸረበው ሴራ፡
አሚን በይ...!!
🤝ይቀጥላል......!
=
t.me/selahudin_Islamic_knowlages
➖➖➖➖➖➖
''አንች ስደተኛ''
--------------------
ቆርጠሽ የዘመትሽው ረጅሙን ጉዞ፡
መንገድሽ በሙሉ እሾህ ተጎዝጉዞ፡
አእምሮሽ ናፍቆትን ትዝታን አርግዞ፡
በሰላም ተመለሽ፤
ልብሽ ጥሩ አቂዳ እጅሽ ገንዘብ ይዞ፡
አሏህ ያስደስትሽ፤
ድካምሽን ክሶ ሀዘንሽን ሰርዞ፡
ህይወትሽ ሳቅ ይሁን፤
መከፋት መታረዝ ስቃይ ተደልዞ፡
¶አንች ማለትኮ...!!
በምትደጉሚያቸው የሚጠፋ ስምሽ፡
በተጠጋሻቸው የሚሰበር ቅስምሽ፡
ራስሽን ትተሽ ለሌላ እምትኖሪ፡
ለተራበው ሁሉ ቀለብ የምትሰፍሪ፡
ማንም ምንም ቢልሽ የማታሳፍሪ፡
ግን የዋህነትሽ በጣም ስለበዛ፡
ሁሉም ሰው ተጠቅሞሽ የጣለሽ ወደዛ፡
ከረሀብ ያዳንሽው የሚያይሽ በዋዛ፡
ንፁህ መስሎ ቀርቦሽ በምላሱ ዋሽቶ፡
የገዛሽለትን ያንችን ስልክ ዘግቶ፡
አላማው ሲሳካ የሚጠፋ ሸሽቶ፡
ሌላን እንዳታምኝ አንችን አበላሽቶ፡
ሁሌ እማይረሳ መጥፎ ስራ ሰርቶ፡
እሱ ግን በድብቅ ህይወቱን መስርቶ፡
ከአንች ገንዘብ ዘርፎ ንፁህ ሀብት አፍርቶ፡
በማይሆን አላማ አንችን አሳስቶ፡
ተጨባጭ በሌለው በነገር ቀስቶ፡
ይገርማል ጭካኔው የዚህስ ይከፋል፡
ልቧ አልበቃው ብሎ ገንዘብም ይዘርፋል፡
ከዚያ ሁለቱንም ያለርህራሔ ይዞባት ይጠፋል፡
¶ ለማንኛውም ግን....
መለወጥ ፈልገሽ ከሀገር የወጣሽ፡
ችግሩ መከራው ናፍቆቱ የቀጣሽ፡
እቅድሽ ተሳክቶ አሏህ ሰላም ያምጣሽ፡
የስኬትን ፅዋ ጌታችን ያጠጣሽ፡
አትንከራተች ምነው ምን በወጣሽ፡
ላንች እምመኘውን ልመርቅ አሚን በይ፡
አሏህ ነው ፈፃሚው በደስታ ተቀበይ፡
ከትላንት እስከ አሁን በጣም ስለማውቅሽ፡
አሚን በይ እህቴ እስኪ ልመርቅሽ!!
በሄድሽበት መንገድ እግርሽ በረገጠው፡
ባረፍሽበት ቦታ ልብሽ በመረጠው፡
የተሻለ ይቅናሽ በሁሉም አቅጣጫ፡
ወርቅ ይነስነስበት የአንች መቀመጫ፡
መልካም ይሁንልሽ የክፋት ማምለጫ፡
ተውሒድ ሱና ይሁን የአንች መገለጫ፡
አንች ከፍ ስትይ ምቀኛሽ ይንጫጫ፡
የበደለሽ ሁሉ ይሁን መወጣጫ፡
ረግጠሽው ውጭ ወደ ስኬት ጣራ፡
ጠላት ይክሰምበት የሸረበው ሴራ፡
አሚን በይ...!!
🤝ይቀጥላል......!
=
t.me/selahudin_Islamic_knowlages