Bahiru Teka dan repost
🔷 የረመዳን ወር መግባቱ የሚታወቀው በጨረቃ ነው ።
እስልምና የየአንዳንዱ ዒባዳ መመሪያ መለያ ያደረገለት ሲሆን ማንም በመሻርና በማፅደቅ እጁን ማስገባት የማይችልበት ከየትኛውም እምነት ለየት የሚያደርገው በመሎኮታዊ ድንጋጌዎች የተገደበ ነው ::
ከእነዚህ መመሪያዎች አንዱ የረመዳን ወር መግባትና መውጣት ( ማለቅ ) የሚታወቀው በጨረቃ መታየት መሆኑ ነው ::
አላህ በተከበረው ቃሉ ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል :–
" فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ……"
البقرة ( 185)
" ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው "፡፡
የረመዳን ወር መግባቱ የሚታወቀው ጨረቃ በመታየቱ መሆኑን የአላህ መልእክተኛ መናገራቸውን አስመልክቶ ዐብዱላሂ ኢብኑ ዑመር የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል : –
وعن ابن عمر – رضي الله عنهما – قال: أن رسول الله – صلى الله عليه وسلم – قال
" إذا رأيتموه ( هلال رمضان ) فصوموا، وإذا رأيتموه ( هلال شوال ) فأفطروا، فإن غم عليكم فاقدروا له "
أخرجه الإمام البخاري
" ( የረመዳን ወር ጨረቃን ) ባያችሁት ጊዜ ፁሙ, ( የሸዋልን ወር ጨረቃ ) ባያችሁት ጊዜ አፍጥሩ, ከተሸፈነባችሁ ወስኑለት ( የሻዕባንን ወር 30 ቀን ሙሉ) "
የረመዳን ወር መግባቱ አንድ ታማኝ የሆነ ሰው ጨረቃን አይቻለሁ ብሎ ከመሰከረ ረመዳን የሚያዝ ይሆናል ።
ይህም የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - አብዱላሂ ኢብኑ ዑመር - ረዲየላሁ ዐንሁማ - ጨረቃ ማየቱንን ነግሯዋቸው ፆም እንዲያዝ ማዘዛቸው የሚያመላክት ሲሆን በሌላም ጊዜ አንድ የገጠር ሰው ማየቱን ነግሯቸው አዘዋል ::
ማለቁ ደግሞ ሁለት ሰው መመስከር አለበት የአላህ መልእክተኛ ሁለት ሰው ከመሰከረ ፁሙ አፍጥሩም ብለዋል መግባቱ ከዚህ የወጣው ቅድም ባልነው የኢብኑ ዑመርና የገጠሩ ሰው ምስክርነት ነው ። በመሆኑም ሙስሊሞች ፆማቸውን የሚዙትም ሆነ የሚፈቱት ጨረቃ ሲታይ ነው ::
ምናልባት ደመና ሆኖ ጨረቃ ማየት ካልተቻለ ሻዕባንን 30 ቀን መሙላት እና ረመዳን አንድ ብሎ መጀመር ነው :: ሌላው አንድ ሀገር ላይ ጨረቃ ከታየ ሌላው ሀገር መፆም ግድ ይለዋል ወይ ? የሚለው ነው ።
ለዚህ ከዑለሞች የተሰጠው መልስ ሀገሮቹ የተቀራረቡና የጨረቃ መውጫቸው ተመሳሳይ ከሆነ አንድ ላይ መፆም አለባቸው የተራራቁና የጨረቃ መውጫቸው ( መጣሊዓቸው ) የማይገናኙ ሀገሮች የራሳቸውን እይታ ይከተላሉ የሚል ነው ::
በአንድ ሀገር ጨረቃ ከታየ የጨረቃ መውጫ መስመራቸው የተቀራረበና አንድ የሆኑ ሀገሮች መፆም ይኖርባቸዋል ። ከላይ እንዳልነው የረመዳን ወር ጨረቃ መግባቱ አንድ ታማኝ ( ዐድል) የሆነ ሰው ከተናገረ የሚመለከታቸው አካላት ምስክርነቱን ተቀብለው ፆም እንዲጀመር ማድረግ ይኖርባቸዋል ። ይህ ብይን ዐድል በሚለው መስፈርት እንጂ ከዚህ አገር ከሆነ በሚል ስላልሆነ የጨረቃ መውጫ መስመራቸው በሚገናኙ ሀገራት ውስጥ የትም ቢታይ ሊሰራበት ይገባል ።
ጨረቃ ያየ ሰው ምስክርነቱ ተቀባይነት ባያገኝ ምን ያደርጋል በሚለው ነጥብ ዑለሞች የተለያየ እይታ አላቸው ።
አንደኛ – ብቻውንም ቢሆን መፆም አለበት ሸዋልም ካየ ከጀማዓ እንዳይለይ በድብቅ ማፍጠር አለበት ።
ይህ የኢማሙ ሻፍዕይና የኢብኑ ሐዝም እይታ ሲሆን ኢማሙ አሕመድም ቀውል አላቸው ።
ሁለተኛ – ረመዳንን ይፁም ማፍጠሩ ግን ከሰዎች ጋር መሆን አለበት ።
የአቡ ሐኒፋና ኢማሙ ማሊክ እይታ ሲሆን ኢማሙ አሕመድም ቀውል አላቸው ።
ሶስተኛ – በእይታው መስራት የለበትም ። ከሰዎች ጋር ፆሞ ከሰዎች ጋር ማፍጠር አለበት ።
አንደኛው የኢማሙ አሕመድ ቀውል ሲሆን ሸይኹል ኢስላም ይህን መርጧል ።
http://t.me/bahruteka