አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሰው ሠራሽ አስተውሎት(Artificial Intelligence) የድኅረ-ምረቃ መርሐግብር ሊከፍት ነው።
ዩኒቨርሲቲው በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በቢግ ዳታ እና በሳይበር ሴኪዩሪቲ መስኮች የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር እየሠራ መሆኑን በተቋሙ የምርምርና ልህቀት ማዕከላት ዳይሬክተር ጌታቸው አዳም (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ባሉት ስምንት የልህቀት ማዕከላት የተለያዩ የድኅረ-ምረቃ መርሐግብሮችን በመክፈት ላይ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ባለፈው ዓመት በዩኒቨርሲቲው የተከፈተው የኒውክለር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የድኅረ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው የልህቀት ማዕከላቱን ታሳቢ ያደረገ የህንፃ ግንባታ እያካሕደ ሲሆን፤ እስካሁን የአራት ልህቀት ማዕከላት ግንባታ መጠናቀቃቸው ታውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ✅
✅ ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers