ለ20 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት የሚያገለግሉ ግብአቶች ድጋፍ ተደረገ።
(ህዳር 11/2017 ዓ.ም) የግብአት ድጋፉ በ2017ዓ.ም በ20 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተቋቋሙ የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት የድጋፍ መስጫ ማዕከላት ለአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ከተመደበ በጀት በተፈጸመ ግዢ መሰራጨታቸውን ከቢሮው የልዩ ፍላጎት/ አካቶ ትምህርት ስራ ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ድጋፉ የተለያዩ የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የሚያገለግሉ የሞንቶሶሪ ዕቃዎች በተለይም ለአይነስውራን እና መስማት ለተሳናቸው እንዲሁም የአካል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የሚያገለግሉ ዊልቸሮችና ክራንቾችን ጨምሮ የተለያዩ ቁሳቁሶች እንደሚገኙበት የቢሮው የልዩፍላጎት አካቶ ትምህርት ባለሙያው አቶ ፀጋዬ ሁንዴ ጠቁመው ግብአቶቹ 1,456,565 ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ ወጪ መደረጉን አስታውቀዋል።
ግብአቶቹ ለልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት ተማሪዎች እንዲያገለግሉ ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ ተደርጎባቸው እንደመሰራጨታቸው ቢሮው በቀጣይ በየትምህርት ቤቱ በመገኘት ግብአቶቹ ለተገቢው አገልግሎት መዋላቸውን በድጋፍና ክትትል የሚያረጋግጥ መሆኑን የልዩ ፍላጎት የጎልማሶች እና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ትግስት ድንቁ አመላክተዋል።