ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_፲፩
..."ምን ተፈጠረ ሜርሲ" እያለ ወደኔ መጣ ባባ ነበር ነፍሴ አሁን ተረጋጋች ምንም መልስ ሳልሰጠው መሬቱ ላይ ተንጋለልኩ "ሜርሲ" እያለ ወደኔ ተጠጋ ከተኛሁበት ደግፎ አንስቶ አቅፎ ወደ ድንኳናችን ይዞኝ መሄድ ጀመርን ላወራው እየፈለኩ ነው ግን አንደበቴ ሊታዘዘኝ አልቻለም ብቻ በአይኖቼ ሽቅብ እየተመለከትኩት ድንጋጤውን ከፊቱ ላይ እያነበብኩት ነበር ዞሪያ ገባውን እየቃኘ በፍጥነት ይራመዳል ከበድኩት መሰለኝ ማለክለክ ጀመረ ትንሽ እንደተጓዝን ቀጥ ብሎ ቆመ ምን እንደተመለከተ ባላውቅም ቀስ አድሮጎ አስቀመጠኝና ወደ ተመለከተው ነገር ጉዞ ጀመረ ከዚ ጫካ ቶሎ መውጣት እንዳለብን እና የደረሰብኝን ነገር ብነግረው ምነኛ ደስ ባለኝ ነበር ትንሽ ከተራመዳ በሗላ ጎንበስ ብሎ የሆነ ነገር አነሳ ምን እንደሆነ ባላስተውለውም ከዛን ወዲያውኑ እርምጃውን ጨምሮ ወደኔ መጣ በእጁ ላይ ጫማ ይዟል የቅድስቴ ጓደኛ ጫማ ነበር በዛ ክፉ ሰው ጥቃት እንደደረሰበት ተረዳሁ ከተቀመጥኩበት እንደምንም የዛፍ ግንድ ተደግፌ ተነሳሁ ጫማው ወደተገኘበት ቦታ ባባን ምርኩዝ አድርጌ ተጠጋሁ...ይመስለኛል ከድንኳኑ ጫማው እስከተገኘበት ስፍራ ድረስ ተሸክሞ ነው ያመጣው...ጫማውን ካገኘንበት በሗላ ደግሞ መሬት ላይ እንደተጎተተ የሚያሳይ የመሬት ቅርፅ አለ...ቀስ እያልኩ ወደፊት በመሄድ መመልከት ጀመርኩ በጫካው ውስጥ አነስ ብላ ጠንከር ያለች ተክል ተመለከትኩ ቅጠሎቿ እና አነስተኛ ቅርንጫፎቿ በደም ተለውሰዋል ይመስለኛል ሰውየሰው የቅድስትን ጓደኛ ሲጎትተው ተክሏን የሙጥኝ ይዟት ነበር ከዛም ሲመነጭቀው የውስጥ እጆ ተቦጫጭሮ ተክሏን ደም እንደለወሳት ተሰማኝ...አሁንም ባባን ተደግፌ ወደፊት እየተጓዝን ነው "ሜርሲ ከዚ ቦታ ቶሎ እንውጣ በጣም አስፈሪና ለኛም ጥሩ አይደለም የሆነው ሆኗል እኛ ከዚ መሄድ አለብን" አለኝ ባባ ወደሗላ እንድንመለስ እየጠቆመኝ እንደምንም ብዬ አንደበቴን ከፍቼ "ያ..ን ሰ..ሰ..ውዬ ሳ..ል..ገ..ለ..ው አልሄድም አልኩት "እየቀለድሽ መሆን አለብት እነዳለ እንድናልቅ ካልፈለግሽ በቀር ሌላ ምንም የሚያቆየን ነገር የለም" አለኝ ቁጣ ሀይል በተቀላቀለው ድምፅ "የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም" ይላል ያገሬ ሰው አልኩኝ ለራሴ ምን እንደሆነ ባላውቅም ውስጤን እልህና በቀል ይሰማኛል "እንሄዳለን ግን ቢያንስ ወዴት እንደወሰደው ለማወቅ ትንሽ ወደፊት ሄደን እንይ" አልኩት በሚቆራረጥ ድምፅ "እሺ" ብሎ ደግፎ ወደፊት ወሰደኝ የተጎተተበትን ምልክት እየተከተልን ትንሽ እንደተጓዝን የልብስ ብጫቂ ተመለከትን ባባን ለቀኩትና ወደ ብጫቂው ጨርቅ ዝቅ አልኩኝ በእጄም ይዤ አነሳሁት ሹል ድጋይ ላይ ነበር የተጣበቀው እላዩ ላይ ትንሽ የስጋ ቁራጭ አለበት ይመስለኛል በመሬቱ ላይ ሲጎትተው ድንጋዩ ጀርባውን ፍቆታል ድንጋዩም ስጋውንና የልብሱን ብጫቂ እራሱ ላይ አስቀርቶታል ስቃዩን ሳስበው የሚያወጣውን የሲቃ ድምፅ በምናብ ሳደምጠው ልቤ ተሸበረ ግን ደሞ ክፉኛ እልህ ውስጥ ገባሁ "የሚበቃሽን ያህል ተመልክተሻል አሁን ተነሺና ከዚ ቦታ እንሂድ" አለኝ እጁን እየዘረጋልኝ ባባ እጅግ ተጨንቋል ፊቱ ላይ ይነበብበታል እኔም እጄን ሰጠሁትና ከተቀመጥኩበት ተነሳሁኝ የባባንም ሀሳብ ተቀብዬ ወደፊት ማዝገም ጀመርን "አንቺ ግን እንዴት እንደዚ አይነት ጦስ ውስጥ ራስሽን ትከቻለሽ ለራስሽ አታስቢም እንዴ" ብሎ ጠየቀኝ "እንደዚ ከባድ መሆኑን አላወኩኝም እኔማ የቅድስቴን ጓደኛ ይዤ ምመለስ መስሎኝ ነው እንደዛ እየሆነች እያየሗት ምንም አለማድረግ ለኔ ከባድ ነው" ብዬ መለስኩለት "እንዳልሽውም ያ ሰው ክፉና መጥፎ ነው ከረፈደ ይሄን መረዳቴ ቢፀፅተኝም ዳሩ" አለ ባባ ልክ መሆኔን እየነገረኝ "ከሰውዬውጋ ተገናኝታችሁ ነው እንደዚ ያደረገሽ" ብሎ ጠየቀኝ እሱን በምሸሽበት ጊዜ የተፈጠረ አደጋ መሆኑን ቀለል አድርጌ አስረዳሁት እኔን ላለማስደንገጥ እንጂ ሁኔታዬ በጣም እንዳስጨነቀውና የደረሰብኝ ነገር አሳስቦታል ግን በንግግር አልገለፀውም ለደቂቃዎች ከተጓዝን በሗላ የፀሃይን ወገግታ ሙሉ ለሙሉ ተመለከትኳት ጫካው ውስጥ ያን ያህል ዘልቃ አትገባም ነበር እኛ ድንኳናችንን የጣልንበት ስፍራ ዙሪያው በጫካው ተከቧል መሀሉ ባዶ ነበር እና ፀሃይ በሃይል ታገኘዋለች ትንሽ እንደተጓዝን ድንኳናችንን ተመለከትኩት ከእርምጃዎች በሗላ ደረስን ሰውነቴ አቅም አንሶታል ድቅቅ ብያለሁ "ወደ ሀኪም ቤት እንሄዳለን" አልኩት ባባን "አዎ ግድ ነው በጣም ተጎድተሻል እኮ" አለኝ ሀሳቡን መደገፌን በጭንቅላቴ ንቅናቄ አውንታዬን አሳየሁት ከጥቂት እርምጃ በሗላ ድንኳኑጋ ደረስን ከኔ ድንኳን ፊት ለፊት ያለው ድንጋይ ላይ አስቀምጦኝ እሱ ወደ ድንኳኑ ተጠጋ እኔም ለማስተዋል እንደቻልኩት ሁለቱም ድንኳን ክፍት ነበር ባባ በድንጋጤ "ባርሳ ቅድስት" እያለ እየተጣራ ድንኳኖቹን ቢያይም ማንም አልነበረም ዞር ብሎም ድምፁን ከፍ አርጎ "ሜርሲ እነ ባርሳ የሉም" አለኝ................
_part #12 ___ ይቀጥላል
ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱