♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
.
.
🌹...ክፍል 37...🌹
.
.
አይ ኤፍዬ የሆነ ሌላ አገር የምሄድና የምንራራቅ አስመሰልከው እኮ ሁለታችንም የተለያየ ቦታ እንሁን እንጂ ከድሬ አልወጣን ዛሬ ብንለያይ መገናኘት በፈለግን ሰአት በደቂቃዎች ውስጥ መገናኘት እንችል የለ እንዴ የሆነ አየር መንገድ አድርሰኸኝ የምትመለስና ወደ ሌላ ቦታ የምበር መሰለህ እንዴ?"
"ልክ ነሽ መገናኘቱንማ ማን ይከለክለናል" አልኳትና አሁንም ዝም አልኩ። ንግግሯ በድጋሚ አቃጨለብኝ።
ለካ እሱም አለ። ያንን ስሜትማ መቋቋምም አልችል። አያምጣው ነው እንጂ አያድርስ አለች ዘፋኟ።
እስከግቢ ሸኝቻት ስመለስ ወደዛ ቤት መግባት ቢያስጠላኝም ግድ ነው እና ገባሁ። ፍራሼ ላይ ጋደም እንዳልኩ ምን ግዜ እንቅልፍ እንደጣለኝ አላውቅም ብንን ስል መሽቷል ።
ተነስቼ ከቃልዬ ጋር በስልክ አወራሁና ወጣ ብዬ ገኒ ሱቅ ሄጄ በሩ ላይ ቁጭ እንዳልኩ ገኒ ሳላዛት ቀዝቀዝ ያለ ቢራ ይዛ መጥታ ከፍታ ሰጠችኝና እዛው አጠገቤ ቁጭ አለች።
እንዴት ነበር የሄድክበት ፕሮግራም ኤፍዬ መች መጣህ ?"
"አሪፍ ነበር ገንዬ በጥዋት ነው የመጣሁት ገብቼ ተኛሁ"
"ኪያ ክከትናንት ወዲያ መጥተህ መሄድህን ሲያውቅ ቆሌው ነው የተገፈፈው ••••" ብላ ልትቀጥል ስትል
"እንኳን ቆሌው ቆዳውም ይገፈፍ አይመለከተኝም በናትሽ ገንዬ በዚህ ርእስ ላይ የማውራት ፍላጎቱ የለኝም ሌላ ነገር እናውራ ከይቅርታ ጋር" አልኳት።
"ውይ እንደዚህማ አታምርር ኤፍዬ ደሞ ቀሽት ያዱገነት ችክ መያዝህን ነግሮኛል" እያለችኝ ሌላ ሰው ለማስተናገድ ተነስታ ሄደች ። መልስ አልሰጠኋትም።
ትንሽ ቆይቶ ኪያ እራሱ መጣ ሱቁ በር አከባቢ እስኪደርስ መኖሬን ስላላስተዋለ እንዳየኝ እንደመደንገጥ አለና
"አማን ነው ኤፏ የት ሄደህ ነው እህትህ ትናንት ካንድም ሁለቴ መጥታ አጣችህ ስልክህን ዘግተህ የት ጠፍተህ ነው?"
"የትም" አልኩት። ዝም አለ ።
ለህቴ ሳልነግራት መሄዴ ልክ እንዳልነበር እያሰብኩ አሁን ብሄድ ባለቤቷ እቤት ስለሚሆን እሱ ደሞ ለኔ ካለው ጥሩ አመለካካት የተነሳ እንድትናገረኝ ስለማይፈልግ እሱ ፊት ብዙ አትበሳጫጭብኝም አሁኑኑ ሄጄ ብገላገል ይሻላል አልኩና ተነስቼ ወደ እህቴ ቤት ሄድኩ።
ስገባ ባሌቤቷ እቤት የለም።
"ቁጭ በል" አለችኝ ። ቁጭ አልኩ። የታላቅነቷን ትንሽ ቆጣ ቆጣ አለችና ወድያው ቀዝቀዝ ብላ እራት እንድበላ እያቀረበችልኝ
"ኤፍዬ እቁቡን ችላ አትበለው እንጂ፣ ቆይ ባጃጅ ሹፌር ሆነህ መቅረት የምትፈልገው? እስካሁን ስምንት ወር ጥለኻል የቀረህ አራት ወር ብቻ ነው። እኔ እቁብ ጥለህ ባጃጁ የተገዛበትን ሂሳብ ለኔ ትመልሳለህ ያልኩህ ሆን ብዬ ነው። ላንተው መሻሻል ነው ጭንቀቴ እንደምንም ብለህ ጨርስ። ከዛ ሀረር ያለውን የአያቶቻችንን ቤት •••"
ስትል አቋረጥኳት።
"እታለም እንሸጠዋለን ልትይኝ ባላሆነ ? ተይ መሸጥ በሚባል ነገር እኔ አልስማማም እንዲሁ እየተከራየ ቢቆይ ይሻላል ። መሻሻል ካለብኝም በራሴ ደክሜ በማመጣው እንጂ በመሸጥ መሆን የለበትም"
"እስቲ መጀመሪያ እኔን አስጨርሰኝ እኔም ሙሉ በሙሉ ቤቱን እንሽጠው አላልኩም ። ግቢው ሰፊ ነው አምስት መቶ ካሬ ሜትር ስለሆነ ሁለት መቶ ሀምሳውን ከፍለን ባዶ መሬቱን ብቻ በመሸጥ ከእቁቡ ጋር ቀላቅለን የሚበቃ ከሆነ ሚኒባስ ገዝተህ ሀረር ድሬ መስመር እንድትሰራ ነው ያሰብኩት። ካልበቃ እኔ እጨምርልሀለሁ የሚተርፍህ ከሆነ ደግሞ ጎሮ አነስ ያለች ቦታ ገዝተህ ቀስ በቀስ ጎጆህን ትቀልሳለህ" አለችኝ። በእህቴ ሀሳብ በጣም ደስ አለኝ። ከሀረር መልስ የተጫነኝ ድብርት በኖ ጠፋ።
"አመስግናለሁ እህቴ በጣም ምርጥ ሀሳብ ነው" አልኳት።
"በል በርታ በልና የቀረችውን እቁብ ጥለህ ጨርስ ። መንጃ ፍቃድም ማውጣት አለብህ ነገ ዛሬ ሳትል ጀምር!"
"የምን መንጃ ፍቃድ መንጃ ፍቃድማ ገና አስራ አንደኛ ክፍል እያለሁ እኮ ነው የወሰድኩት እቴቴ"
"ነው እንዴ ? እና እሱ የባጃጅ አይደል እንዴ?"
"ኧረ የምን የባጃጅ የባጃጁንማ አስረኛ ክፍል ሆኜ ነው የወሰድኩት ከዛ ሶስተኛ ወሰድኩ ረሳሽው እንዴ እታለም?"
"ለካ ገና ሳትፈተን ነው የወደቅከው ?"
"ማለት?"
"ሹፌር የመሆን ህልምህን ስታሳድድ ነዋ ትምርቱን ችላ ያልከው ቤት በኩል ታልፋለህ ፣ የማይፈልጉት ፈተና አይታለፍ"
"እህእ በይው " ብያት ከእህቴ ቤት በጣም ደስ ብሎኝ ነው የወጣሁት። ከአራት ወር በኋላ የሚኒባስ ባለቤት እንደምሆን ሳስበው ፊቴ ድቅን ያለችው ቃልዬ ነች።
አብሮ የመኖር ህልሜ በአጭር ግዜ ውስጥ እንደሚሳካ ሳስበው መንገድ ለመንገድ እንደህፃን ልጅ እየቦረቅኩ ነበር ወደ ገኒ ሱቅ የሄድኩት።
የጀመርኩትን ቢራ እንደቅድሙ በድባቴ ሳይሆን በአዲስ ተስፋ እና ደስታ እያጣጣምኩ ስጎነጨው ቆየሁና ገብቼ ተኛሁ።
በንጋታው በአዲስ የመነቃቃት ስሜት ስራዬን ጀመርኩ። ቀንም ማታም በርትቼ መስራቴን ቀጠልኩ።
ሀረር ሄደን ከመጣን ግዜ ጀምሮ በኔና በቃልዬ መሀል ያለው ፍቅር ይበልጥ ተጋግሎ ሳንተያይ ማደር ሁለት ሶስቴ ሳንደዋወል መዋል የማይሞከር የማይታሰብ ሆኗል።
ሀረር ከመሄዳችን በፊት በነበሩት ስድስት ወራት ፍቅር እኔን እያንገላታ ቃልዬን የሚያሞላቅቅበትን ምክንያት እንዲነግረኝ እንዳልጨቀጨኩት ለምን ፍትሀዊ አትሆንም እያልኩ እንደወቀስኩ እንደረገምኩት ሁሉ ቃልዬንም ተቆጣጥሮ ፍቅራችንን በማመጣጠን እኩል የምንነፋፈቅ፣ እኩል የምንንሰፈሰፍ፣ እኩል አንዳችን ለአንዳችን የምንጨነቅ አድርጎ ሲሰራንም ከማመስገን አልቦዘንኩም።
ቃልዬ አብራኝ ሆና የሚደወልም ከኔ አጠገብ ሄዳ የምታናግረውም ፣ ብዙ ግዜ ሀሙስ እና ቅዳሜ አይመቸኝም የምትለው ነገርም ከሀረር መልስ ቀርቷል።
እኔ እንደማፍቅራት ታፈቅረኝ ይሆን እኔ እንደምታመንላት ትታመንልኝ ይሆን በሚባል የስጋት ማእበል የማይናጥ ፣ ከዛኪ ጋር ሌላ ግኑኝነት ይኖራቸው ይሆን? ቢሚል የጥርጣሬ ውሽንፍር የማይናወጥ ፍቅራችንን ተዝቆም ተቀድቶም በማያልቀው የፍቅር ውቅያኖስ ላይ በፍቅር እየቀዘፍን መንሳፈፉን የየእለት ውሎ አዳራችን ሆነ ።
በሳምንት ውስጥ በትንሹ ሁለት ቀን አብረን እናድራለን። ጌትነት የሚባል እናቱ በሂወት የለሉ አባቱ በስራ ምክንያት ብዙ ግዜ ድሬ ዳዋ የማይኖሩ ለቤተሰቦቹ ብቸኛ የሆነ ጓደኛዬ ከድሮም ጀምሮ እሱ ካባቱ ጋር ከድሬ ውጪ ከሆነ እቤታቸው እያደረን የምንጠብቅላቸው እኔና ጓደኞቼ ነን።
ደውሎ ኤፊ ፋዘር ጋር ልሄድ ነው ከጓደኛህ ጋር እቤት እደሩልኛ ይለኛል (ጓደኛ የሚለው ኪያን መሆኑ ነው )
ከሀረር መልስ እንደዛ ብሎ ሲደውልልኝ የምን ጓደኛ ፍቅረኛህን አትልም እንዴ እያልኩ በሆዴ ቃልዬን ይዣት እሄዳለሁ።እዛ ዙርያውን በግንብ በታጠረ ሰፊ ግቢ ውስጥ ባለ ቪላ ቤት እኔና ቃልዬ ብቻችንን ስናድር ስሜቱ ልዩ ነው። በተለይ ቃልዬ እንደድሬ ሴቶች ሺቲዋን ለብሳ እራት ለመስራት ቡና ለማፍላት ጉድ ጉድ ስትል ሳያት አባ ወራ የሆንኩ ይመስለኛል።
እንዲህ በራሳችን ቤት የምንኖርበት ግዜ መች ይሆን እያልኩ በምኞትም እቀልጣለሁ መሆኑ እንደማይቀር እስብና በነገ ተስፋ ዛሬዬን በደስታ እሞላታለሁ። በቃልዬ ደስተኛ ነኝ።
ሁሌም የሚረብሸኝ ኪያ አለፍ አለፍ እያለ በሚሰነዝረው ቀፋፊ ሀሳብ እና በሚጠይቀኝ ግራ የገባው ጥያቄ ብቻ ነው።
ገብቼ ገና አረፍ ስል ይጠብቅና "ኤፊ ቃልዬ እንዴት ነች?"
"ደና ነች "
"እንዴት ነው ታድያ?"
"ምኑ"