ETHIO TECH™


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


የኮምፒውተር ትምህርቶች
የዌብሳይት ጥቆማ
የሞባይልና ኮምፒውተር መተግበሪያ
ሀኪንግ
ጠቃሚ የቴክኖሎጂ ምክሮች
አነቃቂ መልዕክቶች
Follow us 👇
https://t.me/yene_media
fb.me/eyorikatech
ጥያቄዎችን 👇
@Utoppiaaabot
Google
https://eat-world-solutions.business.site/

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
💥💥 ነፃ ኢንተርኔት 💥💥

ነፃ ኢንተርኔት ኢትዮጵያ ውስጥ አይሰራም ለምትሉ ይህው እኔ አየተጠቀምኩ ነው

ከላይ የምታዩት video ስለ ነፃ ኢንተርኔት ያሳያል

ለነፃ ኢንተርኔት የሚጠቅመንን file ሰሞኑን ቻናል ይለቀቃል ተቀላቀሉን

Tips

🔸Ethio Telecom
🔹Safaricom
በሁለቱም👆 መጠቀም ይቻላል channel ላይ በነፃ ይለቀቃል join

ቀድማችሁ በብር መግዛት ከፈለጋችሁ

Inbox me @Utoppiaaabot


ለግላችሁ አልያም ለድርጅታችሁ አጅግ ዘመናዊ እና ኋይለኛ ሰርች ኢንጂን ኦፕቲማይዜሽን ያካተተ ድረገጽ ማሰራት ከፈለጋችሁ በቴሌግራም አካውንቴ አነጋግሩኝ በጥራት እና በፍጥነት እሰራለሁ። ➥ @on_living @Utoppiaaa @Utoppiaaabot
Group 👇🏻🫶
@ethiopiandeveloper


ሰላም ዉድ የ ETHIO TECH™ ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ብዙ ልጆች ስለ ላፕቶፕ 💻 ለመግዛት ብዙ ጥያቄዎችን በተደጋጋሚ ስለጠየቁን ዛሬ ሙሉ መረጃ አዘጋጅተናል ።

አዲስ laptop ለመግዛት አስበዉ ነገር ግን ምን አይነት laptop እንደሚገዙ ግራ ከተጋቡ🤔 ይችን ምክር ያገንቡቧት።🔻

አዲስ ላፕቶፕ ከመግዛት በፊት ሊያገናዝቧቸው የሚገቡ ነገሮች

📝 በዋናነት ሁለት አይነት Laptop አለ!

◽️በ Windows OS የሚሰራ
◽️በ Mac OS(ለ Apple)ብቻ
(Kali Linux, Ubuntu...እራሳችን የምንጭናቸው Custom OS ስለሆኑ ብዛት እነዚ OS ያላቸውን ላፕቶፖች ገበያ ላይ አናገኝም!)

📌 በብዛት በWindows OS የሚሰሩ የLaptop ዝርዝር👇
◻️ Hp
◻️ Dell
◻️ Accer
◻️ Toshiba
◻️ Asus
◻️ LG
◻️ SONY....ወዘተ

📌በ Mac OS(ለApple ብቻ)
◻️ Macbook Pro
◻️ Macbook Air
◻️ Macbook Retina

🏷አዲስ Computer ሲገዙ ማየት ያለብዎት ነገሮች
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻
1️⃣ RAM (Random Access Memory)

🏷 RAM ማለት አሁን አየተጠቀምንበት ያለዉ application ወይም System Process የሚቀመጥበት ቦታ ነዉ።

🏷 በአንድ ጊዜ ብዙ Application ከፍተዉ ለመጠቀም ኮምፒተርዎ ብዙ RAM ቢኖረዉ ይመረጣል።

🏷 ምንም እንኳን window 10 ለ 32 bit 1GB እና ለ64 bit 2GB (macOS minimum 2GB ያስፈልገዋል) minimum ቢያስፈልገዉም ስራችንን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመስራት ይህ RAM አይበቃንም።

🏷 ስለዚህ አዲስ Computer ሲገዙ 8 GB እና ከዚያ በላይ RAM የለዉ ቢሆን ይመከራል።

2️⃣ Processor

🏷 Core i3 chips:ይህ Processor ዝቅተኛ ሀይል እና እርካሽ ዋጋያለዉ ነዉ።

🏷 Core i5 chips: ይኸ ተመጣጣኝ ዋጋ እና Performance የያዘ ነዉ ።

🏷 ተመጣጣኝ ዋጋ እና በቂ speed ያለዉ Computer ከፈለጉ ይኽን ይምረጡ።

🏷 Core i7 : የገንዘቡ ነገር እማያሳስቦ ምርጥ ኮምፒውተር መግዛት ከፈለጉ ከ Cori i7 በታች አይምረጡ።

3️⃣ Storage ባሁኑ ሰአት ሁለት አይነት የኮምፒዉተር Storage አሉ HDD(hard disk drive) እና SSD(solid state drive)
HDDs መረጃዎችን ለማስቀመጥ በፍጥነት የሚሽከረከሩ Magnetic Disk'ችን(Platters) ሲጠቀም flash memory ይጠቀማል።

🏷 SSD ያላቸው ኮምፒውተሮች የመጻፍ እና የማንበብ rate'አቸዉ HDD ካላቸዉ ኮምፒውተሮች በጣም ፈጣን ነው።

🏷 SSDs ምንም የሚንቀሰቀሱ part ስለሌላቸዉ lighter,cooler,quiter, more efficient and harder to damage ስለሆኑ ከ HDD ይልቅ ተመራጭ ናቸው።

4️⃣ Screen size

🏷 የ እስክሪን መጠን በብዛት የምንመርጠዉ #Laptop ስንገዛ ነዉ።
ላፕቶፖች ከ 11-17 _inch መጠን አላቸዉ።

🏷 ብዙ *window* ባንዴ የምንጠቀም ከሆነ ትልቅ እስክሪን መጠን የለዉ
#Laptop ብንገዛ አሪፍ ነዉ።

🏷 ነገር ግን ትልቅ የእስክሪን መጠን ያላቸዉ ላፕቶፖች ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ ያስቸግራሉ እንዲሁም ትንሽ የባትሪ እድሜ አላቸዉ።

🏷 ዴስክቶፕ ላይ
#Portability እና የባትሪ እድሜ ችግር የለዉም ነገር ግን ብዙ ሰዎች 24-inch ወይም ከዚያ በላይ #Monitor ይመርጣሉ።

4️⃣ Resolution

🏷 Resolution እንደናተ ምርጫ እና ገንዘብ ይወሰናል።

🏷 ምንም አይነት ሳይዝ ቢኖረዉ የእስክሪኑ
#display ጥራት የሚወሰነዉ በ #Resolution ነዉ።

🏷 አብዛኞቹ ላፕቶፖች በ 720p resolution ለትንሽ display size ይመጣሉ።

🏷 ከፍተኛ ላፕቶፖች *Ultra HD/ 4K display* ይመጣሉ ነገር ግን ዋጋቸዉ በጣም ዉድ ነዉ።

5️⃣ Size and Weight

🏷 አሁንም ሳይዝ እና ዉፍረት ለ
#desktop ብዙም ችግር የለዉም ነገር ግን ላፕቶፕ *portability_ ሊኖረዉ ይገባል።

🏷 ላፕቶፕዎን እንደፈለጉ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ 12-inch
Screen siz*e ወይም ከዚያ በታች ይምረጡ።

6️⃣Operating Syatem

🏷Windows ብዚ ጊዜ በስራ ቦታ እና ብዙ ሰዉ በምቾት የሚጠቀምበት #Operating System ነዉ።

🏷የApple ኮምፒዉተር ከገዙ Mac Operating System ይጠቀማሉ።

7️⃣ Generation
🏷ማወቅ ያለብዎ latest generation ምን ጊዜም efficient እና powerful ናቸዉ።
5th, 6th, 7th, 8th.....

8️⃣ Graphics Card
Graphics Card ማለት ከ ፎቶ እና ቪዲዮ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች በምንጠቀምበት ሰአት ፈጣን እና ከፍተኛ ጥራት ባለው መንገድ አቀናብሮ መስራት የሚያስችል የ ማትስ ቀመር የሚጠቀም Hardware Device ነው።

🏷 a single, high-powered graphics card ያለው ይምረጡ ይህም ኮምፒውተሮ ላይ በ3D የሚሰሩ ለሶፍትዌሮችን ማለትም እንደ AutoCad አይነት እንዲሁም ጌም የሚጫወቱ ከሆነ ይጠቅሞታል
9️⃣ ኮምፒውተሮን ሲገዙ አብረው external hard drive ይግዙ ይህም ዳታዎችዎን ባክ አፕ (መጠባበቂያ) ለማረግ ነው::

🔟 Battery (ባትሪ) የስአት ቆይታው ቢያንስ ከ4 ሰአት በላይ ቢሆን ይመረጣል!
- 10,000 mAh
- 20,000 mAh
- 30,000 mAh
WHO IS INTERESTED ?👇🏻👇🏻
@ethiopiandeveloper
የተማሩትን ማስተማር ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው !!! ለምታውቋቸው ወዳጅዎ Share አድርጉት!!!
https://t.me/InfoTechEthi


​​#Google

ስለ Google አስር የሚያስደንቁ ነገሮች

ስለ ጉግል 10 ሊያስገርምዎ የሚችሉ መረጃዎች እነሆ ። 😊👇🏻👇🏻

✅ ስያሜው
ግን ጉግል ምን ማለት ነው? ጉግል ስያሜውን ያገኘው በስህተት ነው።
በእንግሊዝኛው 'googol' ማለት በሂሳብ ቀመር 1 እና መቶ ዜሮዎች ማለት ነው።
እና ተሜው ተሳስቶ ስያሜውን ጉጎል ወደ ጉግል አመጣው፤ የጉግል ፈጣሪዎችም ይህንን ቃል ለመጠቀም መረጡ።

✅ የጀርባ ማሻ
የጉግል ፈጣሪዎች ላሪ ፔጅ እና ሰርጌይ ብሪን ለጉግል የሰጡት የቀድሞ ስም በእንግሊዝኛው 'Backrub' ወይም የጀርባ ማሻ የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ቃል ነበር።
ምክንያቱም ሰዎች ፈልገው የሚያገኙት መረጃ ጉግል ላይ ከሰፈሩ ሌሎች ድረ ገፆች ስለሆነ። ኋላ ላይ ስሙን ሊቀይሩት ተገደዱ እንጂ።

✅ የተንጋደደ
ጉግል ንግድ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጨዋታዎችም ይገኛሉ።
እንደማሳያ እስቲ ወደ ጉግል ይሂዱና ይህችን "askew" የእንግሊዝኛ ቃል መፈለጊያው ላይ ይፃፉት።

✅ ፍየሎች
ጉግል አረጓንዴ ምድርን እደግፋለሁ ይላል፤ ለዚህም ነው የመሥሪያ ቤቱን ሳር ማጨጃ ማሽኖች በፍየሎች የተካው። አሜሪካ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 200 ያህል ፍየሎች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተው የየትኛው አርብቶ አደር ዘመናይ ግቢ ነው ብለው እንዳይደናገሩ። ፍየሎቹ የጉግል ናቸውና።

✅ እየተመነደገ የሚገኝ 'ቢዝነስ'
ጂሜይል፣ ጉግል ማፕ፣ ጉግል ድራይቭ፣ ጉግል ክሮም ከተሰኙት በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጉግል በየጊዜው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የግሉ ሲያደርግ ቆይቷል።
ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ ግን እኛ እንንገርዎ፤ አንድሮይድ፣ ዩትዩብ፣ እንዲሁም አድሲን የተሰኙት ቴክኖሎጂዎች የጉግል ንበረቶች ናቸው።
ከሌሎች 70 ያክል ኩባንያዎች በተጨማሪ ማለት ነው።

✅ ዱድል
ዱድል የተሰኘው የጉግል ውድድር መድረክ አሜሪካ የሚገኙ ተማሪዎች የድርጅቱን ምልክት ፈጠራቸውን ተጠቅመው እንደአዲስ እንዲቀርፁት የሚያበረታታ ነው።
ይህ ውድድር ከተጀመረ ወዲህ የጉግል አርማ በየቀኑ ሲቀያየር ይስተዋላል።
አንዳንዴም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ቀናት በማስመልከት የጉግል መለያ ይለዋወጣል።

✅ ለሌሎች ያመለጠ ዕድል
በፈረንጆቹ 1999 ላሪ እና ሰርጌይ «ኧረ ጉግልን በአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገዛን» እያሉ ቢወትወቱ የሚሰሙ ጠፋ።
ዋጋው ላይ መደራደር ይቻላል ቢሉም ምንም ምላሽ አልተገኘም።
አሁን የጉግል ዋጋ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፤ ሚሊዮን አላልንም፤ ልብ ያርጉ ቢሊዮን ነው።

✅ መሪ ቃላት
'ከይሲ አይሁኑ' ከድርጅቱ ቀደምት መሪ ቃላት አንዱ ነበር።
'ምን አገባው' የሚሉ ብዙዎች ቢኖሩም ድርጅቱ ይህን መሪ ቃል አልተውም ብሎ ሙጥኝ ብሏል።

✅ ምግብማ ግድ ነው
ከጉግል ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰርጌይ ብሪን ነው አሉ ማንኛውም የጉግል ቢሮ አካባቢ ምግብ የሚገኝበት አማራጭ መኖር አለበት ብሎ ያዘዘው፤ በቢዛ 60 ሜትር ርቀት ላይ።
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ቢሯቸው እጅግ ያሸበረቀና ምግብ ባሰኛቸው ጊዜ ወጣ ብለው ሊመገቡበት የሚችሉበት እንደሆነም ይነገራል።

✅ የጉግል ባልንጀራ
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ውሾቻቸውን ወደ ሥራ ቦታቸው ይዘው መምጣት ይፈቅዳለቸዋል።
ውሾቹም ከቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሳቸውን እንዲያመቻቹ ሥልጠና ይሰጣቸዋል።

የተማሩትን ማስተማር ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው !!! ለምታውቋቸው ወዳጅዎ Share አድርጉት!!!

ምንጭ፦ BBC AMAHARIC


​​ፍላሽ ዲስክ እንዴት በፓስዎርድ ማሰር ይቻላል? 🤔
በፍላሽ ዲስክ የተለያዪ ሚስጥራዊ ዳታዎች እንይዛለን! ከራሳችሁ ውጪ ሌላ ማንም ሰው እንዳያየው የምትፈልጉት #ዳታ(ፋይል፣ቪድዮ፣ፎቶዎች ወዘተ...) በፍላሽ ዲስክ ትይዛላችሁ።
ስለዚህ ሚስጥራዊ ዳታችሁን ከናንተ ውጪ ማንም ሰው እንዳያየው ወይም እንዳይጠቀምበት የግድ ፍላሽ ዲስኩን በፓስወርድ መቆለፍ ይኖርባችኋል።
እሺ windows 10 የምትጠቀሙ ሰዎች ፍላሽ ዲስካችሁን በፖስወርድ ለመቆለፍ የሚከተሉትን ስቴፖች በመከተል መቆለፍ ትችላላችሁ።
1-ፍላሽ ዲስኩን ኮምፒውተራችሁ ላይ ሰኩት እና"This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ(Double click) አድርጉት
2- "This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ ስታደርጉት የሚመጣው ቦክስ ውስጥ ፍላሽ ዲስካችሁ ይመጣል
3- ፍላሽ ዲስኩን "right click" አድርጉ
4- ፍላሽ ዲስኩን "right click" ስታደርጉ "Turn BitLocker on" የሚለውን ሴሌክት (select)ማድረግ
5- ከዚያ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል፣ የማትረሱት ፓስወርድ አስገቡና "next" በሉት
6- ከዚያ "Encrypt entire drive" የሚለውን ሴሌክት በማድረግ "next" ማለት። በቃ አለቀ።ፍላሽ ዲስኩ በፓስውርድ ተቆለፈ።
ከዚህ በኋላ ያለ እናንት ሌላ ማንም ሰው ፍላሹን መጠቀም አይችልም።
ፍላሽ ዲስኩን መጠቀም ስትፈልጉ ኮምፒውተራችሁ ላይ ፍላሹን ደብል ክሊክ ስታደርጉ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል።ፓስወርድ በማስገባት መጠቀም ትችላላችሁ

የተማሩትን ማስተማር ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው !!! ለምታውቋቸው ወዳጅዎ Share አድርጉት!!!


ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች🤌🏼

1. ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች ዎልፔፐር አይጠቀሙ፡፡
2. ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡
3. አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡
4. የማይጠቀሙበት ሶፍትዌር ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት)፡፡
5. ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡
6. ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፕ አይነት አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ
7. Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::
8. ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
9. ብዙ ሶፍትዌሮችን ባንዴ አይክፈቱ::
10. ኮምፒውተርዎን update ያድርጉ!

via. MuhammedComputerTechnology
Comment ✉️ @on_living

#Like #shared


#Blue

በሀገራችን ልክ እንደ ፌስቡክ የሚያገለግል #ብሉ(blue) የተሰኘ ማህበራዊ ሚድያ ይፋ ሆኗል!!

ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትጠራበት የራሷ የሆነ የማህበራዊ ትስስር ሚዲያ ቢኖራት ብለው ያለሙ ወጣት ባለሃብቶች https://blue.et Blue - ብሉ የተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ይፋ አድርገዋል። ይህ ፕላትፎርም ልክ እንደፌስቡክ ለአጠቃቀም እጅግ ቀላል እና ብዙ ተግባራትን ለመከወን የሚያስችል ነው።

አካውንት ከፍታችሁ እንድትጠቀሙት በክብር እጋብዛችኃለሁኝ።የራሳችን የሆነ ነገርን ማበራታት አለብን ብዬ አስባለሁ።🇪🇹

የኔ አካውንት https://bit.ly/3Vy1Adj ነው
ጓደኛ ብንሆን ምን ይመስላችኋል ?😊😊

መረጃው ጠቃሚ ከሆነ #SHARE ለሌችም እንዲደርስ ይደረግ!


#Awareness
የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

🚩የሞባይል ባንኪንግ የባንክ አገልግሎቶችን ወደ ባንኮች ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ብቻ የባንክ አገልግሎቶችን ማለትም ገንዘብ መላክ እና መቀበል እንዲሁም የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

🚩የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የተጠቃሚዎችን ድካም ከመቀነስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቱን ተመራጭና ቀላል ያደርገዋል፤ ታዲያ ይህ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ውጤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተጓዳኝ የመረጃ መረብ ጥቃት ተጋላጭነት አያጣውም፡፡

🚩ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የሚከተሉትን ጉዳዮች ሊያውቋቸው እና ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው ይገባል ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ይመክራል፡፡

➊. የተረጋገጡና ትክክለኛ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን (application) ከተረጋገጡ ምንጮች አውርዶ መጠቀም፦ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ትክክለኛ በባንኩ እውቅና ያላቸው መሆኑንና የሚገኙትም በትክክለኛው የመተግበሪያ ቋት ማለትም ለአንድሮይድ የመተግበሪያ ቋት ወይም ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማውረድ መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡

➋. በስልኮች ላይ ያሉ ሌሎች መተግበሪያዎች ፍቃዶችን ማጥናት፡- በስልክዎ ላይ የሚገኙ ሌሎች መተግበሪያዎች የሚጠይቋቸውን ግንኙነቶች (አክሰስ) ልብ ይበሉ፡፡
መተግበሪያዎች ለአገልግሎቶቻቸው ከሚያስፈልጋቸው የሞባይል መረጃ ዉጪ ሌሎች መረጃዎች እንዲዳረሱ እንዳይፈቅዱ፡፡

➌. አፕሊኬሽኖችን /መተግበሪያዎችን ማዘመን፡- በስልኮች ላይ የሚገኙ የባንኪንግ መጠቀሚያ መተግበሪያዎችን ወቅቱን ጠብቀዉ ያዘምኑ፡፡
መተግበሪያዎች ላይ ለስርቆት የሚዳርጋቸው ክፍተቶች ሲገኙ በየወቅቱ ማዘመኛ ስለሚለቀቅላቸው የደህንነት ክፍተቶቹን ለመድፈንና የባንክ ሂሳብዎን ደህንነት ለማስጠበቅ በየጊዜው ያዘምኗቸው፡፡

➍. የሞባይል ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማዘመን፡- የስልክዎን ደህንነት ክፍተት ለመሙላት በየጊዜው ክፍተት መሙያና ማሻሻያ እድሳቶች ስለሚለቀቁ በየወቅቱ እየተከታተሉ ያዘምኗቸው፡፡

➎. ከህዝብ መገልገያ ዋይፋይ ይልቅ የሞባይል ዳታ ይጠቀሙ፡- የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በሞባይልዎ ለመጠቀም ለህዝብ መገልገያ የቀረቡ ነፃ ዋይፋዮችን ከመጠቀም ይልቅ የሞባይል ዳታዎችን ይጠቀሙ፡፡

➏. ዘርፈ-ብዙ የደህንነት ማስጠበቂያ የይለፍ-ቃሎችን ይጠቀሙ፦ ሞባይል ስልክዎን በአሻራ፣ ፊት ማንበብያ (ፌስ ሪኮግኒሽን)፣ ፓተርን፣ ፓስወርድ እና ፓስ ኮድ የመሳሰሉትን በመጠቀም ስልክዎን ይቆልፉ፡፡

➐. በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቋቸውን ግላዊ መረጃዎች ይገድቡ፡- በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁ መረጃዎች የተገደቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡

➑. ፀረ-ቫይረስ (ማልዌር) ይጠቀሙ

➒. የሞባይል ስልክዎን አካላዊ ደህንነት ያስጠብቁ

➓. የባንክ ሂሳብዎን ዘወትር ይከታተሉ፡- በተጨማሪ ተገቢውን ሁሉ ጥናቃቄ ካደረጉ በኋላም ስለ ባንክ አካውንትዎ የሚደርሱ ማንቂያዎችን (notifications) በአግባቡ መከታተል እንዲሁም በየጊዜው ስለ አካውንትዎ ሁናቴ (ስታተስ) መከታተል እና የማያውቁት የሂሳብ ለውጥ ካለ በአፋጣኝ ለባንክዎ ያሳውቁ፡፡


መረጃው ጠቃሚ ከሆነ ለሌችም እንዲደርስ
#SHARE ይደረግ
#EYORIKATECH


mohammed computer technology


#Telegram
የማንፈልጋቸው የቴሌግራም ግሩፖች(Groups) ላይ ማንም ሰው አድ(Add) እንዳያደርገን ማድረግ እንዴት ይቻላል?🤔

#ቴሌግራም ላይ ብዙ ዓይነት ግሩፖች አሉ፡፡ እነዚህ ግሩፖች ሁሉንም ላንፈልጋቸው እንችላለን፡፡ አንዳንዴ ግን ፈለግንም አልፈለግንም ሳናውቀው የተለያዩ ግሩፖች ላይ አድ)Add) ተደርገን እናያለን፡፡ እንደውም የማንፈልጋቸው ግሩፖች ላይ አድ እየተደረግን የተማረርን ሰዎች እንኖራለን፡፡
ስለዚህ ማንም ሰው እየተነሳ የፈለገው ግሩፕ ላይ አድ እንዳያደርገን ለማድረግ እንችላለን፡፡በጣም ቀላል ነው፡፡ እነዚህን ስቴፖች መከተል ነው።

1. ቴሌግራም አፕሊኬሽን እንክፈት
2. ከላይ በግራ በኩል ያሉት ሶስተ ሰረዞች ክሊክ እናድርግ
3. ከሚመጡት አማራጮች Settings የሚለውን ክሊክ እናድርግ
4. ከዚያ Privacy and Security የሚለውን ክሊክ እናድርግ
5. ከዚያ ከሚመጡት አማራጮች Groups የሚለውን ክሊክ ማድረግ
6. Groups የሚለውን ክሊክ ስታደርጉ ሁለት ምርጫዎች ይመጣሉ Everybody እና My Contacts የሚሉ፡፡ እናንተ My Contacts የሚለውን ምረጡ፡፡
7. ከዚያ ከላይ ማረጋገጫ(√) ክሊክ ማድረግ፡፡
በቃ ከአሁን በሁዋላ ማንም ሰው የፈለገው ግሩፕ ውስጥ አድ(Add) አያደርጋችሁም ማለት ነው፡፡

Comment📩 @On_living

#LIKE
#SHARE
#EYORIKATECH


https://imageresizer.com/
👆👆
እሄ ደሞ ሊንክ የፎቶዋችሁን መጠን ወደ 240 kb እንድትቀይሩ የሚያስችል ድረገጽ ነው
1. SELECT IMAGE
እዚህጋ የምትከቱት ቅድም 600 በ 600 ያደረጋቹትን ምስል ነው
2. ፎቶውን ከአስገባቹ ቡሃላ Resize ይሚለውን መንካት
3. Export settings በታች Target file size የሚለው ቦታ ውስጥ 240 ጻፉ
4. ውደ ታች ድሞ Save image as የሚለው ጋ በመንካት JPEG ን መምረጥ
5. RESIZE IMAGE በመንካት ዳውንሎድ አደረጉት ከዛ ዲቪ ፎርሙ ቦታ ላይ ማስግባት

አስተያየት @utoppiaaa




endimolalachu mtfelgu inbox @utoppiaaa


ETHIO TECH DV2024.docx
26.8Kb
የ2024 ዲቪ ምዝገባ ተጀምሯል😁
በዶክመንቱ መሰረት መሙላት ይቺላሉ😊
ሊንክ📎
https://dvprogram.state.gov/
እገዛዬን ለምትሹ አናግሩኝ✌️@utoppiaaa
November 8, 2022 ያበቃል!!🤗


📯ድርጅትዎ ዌብሳይት አለው?⁉️
🔺🔻🔺🔻🔺🔻🔺🔻🔺🔻🔺🔻🔺🔻
እንግዲያውስ ዛሬውኑ ይዘዙን በፈለጋቹት መጠንና መንገድ ድርጅቱን የሚገልጽ #website በሚገርም ጥራት ሰርተን እናስረክባለን ። 🔥🔥🔥
Company description 🏢💻📲📲🌐
E-commerce 📈💶💴💵
For Fashion and Branding 🖼
Photography website 📸📷
And other🚗🏎🎮...
እንዲሁም ለግል👤 ምትፈልጉ አናግሩን በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክባለን ከታች በአሉን አድራሻዎች 📎አናግሩን🙏🙏🙏👇👇
@On_living
@On_living
@On_living
@On_living
@utoppiaaa
@utoppiaaa
@On_living
@utoppiaaa
@utoppiaaa
@Utoppiaaabot
@Utoppiaaabot
@Utoppiaaabot
ስልክ 📱+251976103122

ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው እራስዎን ፣ ድርጅትዎ እና ምርት እና አገልግሎትዎን ለአለም ያስተዋውቁ ።

© eyorika technology startup company


#RAM
🖥💽💾
RAM
ራም (ራንደም አክሰስ ሜሞሪ) ኮምፒውተር በፍጥነት ኦፕሬቲንግ ሲስተም (ኦኤስ) ፣ Application ፕሮግራሞች እና መረጃዎች በአሁኑ ወቅት በሚቀመጡበት የኮምፒተር መሣሪያ ውስጥ ሃርድዌር ነው ፡፡
#RAM የሚጠቅመው #የተቀሰቀሱ/የተከፈቱ #ፕሮግራሞች #በፍጥነት እንዲሰሩ የሚጠቅም ነው፡፡ የ RAM ተግባር በተለዋጭነቱ ምክንያት ራም ቋሚ መረጃዎችን ማከማቸት አይችልም።
ይህ ሊሆን የሚችለው #ኮምፕዩተሩ እነዚህን የተቀሰቀሱ #ፕሮግራሞች ለጊዜው (ተቀስቅሰው እስካሉ ድረስ) ለምሳሌ #HHD ወይም ከሲዲ ከማንበብ ይልቅ ከራም ላይ ያነባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ራም #ጊዚያዊ ፕሮግራም ተሸካሚ ግን በፍጥነት አቅራቢ እንደማለት ነው፡፡ #ለምሳሌ አንድ ተጠቃሚ ኢንተርነት የሚቀዝፍ ከሆነ ቀዛፊውን ከፍቷል፡፡ ሰነድ የሚጽፍ ከሆነ ወርድን ከፍቷል #ፎቶ ወይም ቪዲዮ የሚሰራ ከሆነ የፎቶና ቪዲዮ #ፕሮግራሞች ከፍቷል፡፡ እና እነዚህ ፕሮግራሞች #እስከተከፈቱ_ድረስ_ራም_ለጊዜው_ተሸክሞ_ይይዛቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ራም ከፍ ባለ ቁጥር #የኮምፕዩተሩም_ፍጥነት የሚጨምረው፡፡ ያው አማካይ አዛዢም እራሱን የቻለ ሚና ቢጫወትም፡፡ #ራም ልክ እንደሌሎቹ ክፍሎች ዋና ቦርድ ቦታ ስላለው እዛ ይሰካል፡፡

💾Hard disk

#ዳታዎችን በቋሚነት #ለመያዝ ነው፡፡ #የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) #የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት #የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡ ለምሳሌ የሆነ #ሰነድ ጽፈው ለመያዝ ከፈለጉ የሚይዘው #HHD ላይ ነው፡፡ እንደተለመደው HHD ዋና ቦርድ ላይ ይሰካል፡፡ HHD ዳታ ሲያነብና ሲጽፍ ማግኔታዊ ነው።

Comment @On_living

#EYORIKATECH #share #like


#Attention ⚠️
ፌስቡክዎ መጠለፉን ለማወቅና ከጠለፋ እራስዎን ያውጡ!

1. Setting and Privacy ይግቡ
2. Setting ይንኩ
3. Security
4. Security and login
5. Where you are logged in
ከዚህ ውስጥ በምን ሞባይል ወይም ኮምፒውተር፣ የት ቦታና ሀገር፣ በምን ብራውዘር፣ ወይም አፕልኬሽን፣ መቼ ቀን ከዚህ በፊት እንደከፈታችሁት ያሳያችኋል። ነገር ግን ደግሞ Active now 🟩በሚል በአረንጓዴ የተጻፈው አሁን የከፈታችሁበትን ይነግራችኋል። ከዚህ በታች የተዘረዘረውን Session ስትመለከቱ የናንተ ካልሆነና የሚያጠራጥር ከሆነ ከታች ላይ Logout All Sessions የሚለውን በመጫን Logout የሚለውን በመጫን እራስዎን ከጠላፋ ማውጣት ይኖርብዎታል።
የተጠለፈ መሆኑ ከተጠራጥሩ በፍጥነት Password መቀየር ይኖርብዎታል።
ከአምስተኛው ተራ ቁጥር በመቀጠል ካለው Step Where you are logged in በታች Login ከሚለው በታች Change password የሚለውን በመጫን current password እና New password በማስገባት Save Changes የሚለውን ይጫኑ።

✅ በተጨማሪም Two factor Authentication On ቢያደርጉት ጥሩ ነው። ይህ On መሆኑ ምንም እንኳን የፊስቡክ አካውንትዎን Password ሰው ቢያውቅብዎ በስልካችሁ የሚላከውን Security code እስካላወቁ ድረስ መክፈትና መጠቀም አይችሉም። ስለዚህ On በማድረግ እንድትጠቀሙ እመክራለሁ። በፈለጋችሁ ሰአት Off ማድረግ የምትችሁ ይሆናል!

እራስዎን ከጠላፊዎች ይከላከሉ!
Comment 🔸
@On_living @On_living @On_living

#EYORIKATECH #SHARE #LIKE


አዲስ Smart 📱📲ሞባይል ስልክ ሲገዙ ማገናዘብ የሚገባዎ 13 ነገሮች ከምሳሌ ጋር ~+
መግዛት ያሰቡት smart ሞባይል ስልክ iPhone ወይም Samsung ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል።ማንኛውም smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ስልኩ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን 13 መመዘኛዎች ማሟላቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

1~ ፕሮሰሰር(Processor)
ብዙ ግዜ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ፣ቪድዮ የሚያዩ ከሆነ ወይም የቪድዮ ኤዲቲንግ የሚሰሩ ከሆነ የስልኩ ፕሮሰሰር Qualcom Snapdragon(652/820/821) ቢሆን ይመረጣል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ፕሮሰሰሩ MedaTek ከሆነ በቂ ነው።

2 ~ ካሜራ
ፎቶ የማንሳት ልምድ ያለው ሰው የስልኩ ካሜራ 13mp(Megapixels) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ግን 8mp በቂ ነው።

3 ~ ባትሪ
ብዙ ሰዓት ቪድዮ ለሚያይ፣ጌም ለሚጫወት ሰው ባትሪው 3500mAh(Miliamp Hour) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ለመካከለኛ ተጠቃሚ 3000mAh በቂ ነው።

4 ~ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS)
የተለያዩ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS) ቨርዥኖች አሉ።ለምሳሌ samsung galaxy ስልኮች ኪትካት፣ሎሊፓፕ፣ማርሽሜሎ...ወዘተ የተባሉ ቨርዥኖች አሉ። ስለዚህ latest ቨርዥን መምረጥ ይመከራል።

5 ~ Storage
ስልኩ በቂ የማጠራቀሚያ አቅም ቢኖረው ይመረጣል። 16GB/32GB/64GB..ከነዚህ ውስጥ መምረጥ ነው። ስልኩ ኤክስተርናል ሜሞሪ(microSD card) የሚቀበል መሆን አለበት።

6 ~ Headphone Jack
HeadPhone 3.5mm audio
jack ቢሆን ይመረጣል።

7 RAM ከተቻለ ከ4GB በላይ ቢሆን ጥሩ ነው ነገርግን ለመካከለኛ ተጠቃሚ 2GB በቂ ነው

8 USB File transfer USB 2.0 በአሁኑ ጊዜ ያለ ስለሆነ ይህ ፖርት ያለው ቢሆ ይነረጣል , USB 3.0 ቢሆን ጥሩ ነው.

9 Physical Size በኢንች ለናንተ የሚቸውንም መምረጥ አለባችሁ በተለይ ለአያያዝ ምቹ መሆኑን አረጋግጡ።

10 የሚቀበለው የሲም ካርድ አይነት መለየት።

11 Display: 6.5 inches በጣም ምርጥ ነው ለአያያዝ ምቹ ነው።

12 Resolution 1080 x 2400 pixels ቢሆን ይመከራል

13 Data 4G LTE ለመጠቀም ያመች ዘንድ 4G Support የሚያደርግ ቢሆን ይመረጣል


〽️ምሳሌ ከታች ያለውን Specification ተመልከቱ።
Dimensions: 75.8 x 164 x 8.9 mm
Weight : 205 g
SoC: MediaTek Helio P35 (MT6765)
CPU : 4x 2.3 GHz ARM Cortex-A53, 4x 1.8 GHz ARM Cortex-A53, Cores : 8
GPU : PowerVR GE8320, 680 MHz
RAM : 3 GB, 4 GB, 6 GB
Storage : 32 GB, 64 GB, 128 GB
Memory cards : microSD, microSDHC, microSDXC
Display : 6.5 in, TFT, 720 x 1560 pixels, 24 bit
Battery : 5000 mAh, Li-Ion
OS: Android 10
Camera : 8000 x 6000 pixels, 1920 x 1080 pixels, 30 fps
SIM card : Nano-SIM
Wi-Fi : a, b, g, n, n 5GHz, ac, Dual band, Wi-Fi Hotspot, Wi-Fi Direct
USB: 2.0, Micro USB
Bluetooth: 5.0
Positioning: GPS, A-GPS, GLONASS, BeiDou

Comment 💢 @utoppiaaa

#EYORIKATECH #LIKE #SHARE


5.ከሚከተሉት አቋራጭ ቁልፎች ውስጥ Refresh ለማድረግ የምንጠቀምበት የቱ ነው?
So‘rovnoma
  •   F5
  •   F10
  •   F12
  •   F4
33 ta ovoz


4. ከሚከተሉት ምርጫዎች አዲስ ዊንዶው ለመክፈት የሚጠቅመን ኮማንድ የቱ ነው?
So‘rovnoma
  •   A. Shift + N
  •   B. Ctrl + N.
  •   C. Alt + N
  •   D. Alt + F5
31 ta ovoz


3. በMicrosoft Word ላይ አንድን ቃል ኮፒ ለማድረግ የምንጠቀምበት ኮማንድ የቱ ነው?
So‘rovnoma
  •   A. Ctrl + Y
  •   B. Ctrl + C
  •   C. Ctrl + A
  •   D. Ctrl + X
36 ta ovoz

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

921

obunachilar
Kanal statistikasi