Entrance hub 2014


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


Entrance hub Natural Students

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ጥሩ ውጤት የሰራችሁ እስቲ ላኩልን🙏🙏


Entrance Hub 2014 dan repost
እስቲ ውጤት እንዴት ነበር?
So‘rovnoma
  •   ከ50% በላይ
  •   ከ50% በታች
83 ta ovoz


ውድ የ Entrance hub 2014 ቤተሰቦቻችን እንዴት ናችሁልን😍
በቅድሚያ እንኳን ለዚህ የእረፍት ቀን በሰላም አደረሳችሁ😍

ያን ሁላ የጭንቀት ቀናት አልፋችሁ ለዛሬ መድረሳችሁ ከፈጣሪ ምህረት እንጅ ከእናንተ ብርታት እንደልሆነ ግልፅ ነው😇

እኛም ከእናንተ እኩል እየተጨነቅን፣ ለእናንተ ይጠቅማል ያልነውን ሁሉ አቅማችን በፈቀደው መጠን ለመስጠት ስንሞክር ነበር።
ሁሉንም ትምህርት አይነቶች በቂ ኖት አቅርበናል፤ በተለያ መንገድ ለማስተማር ሞክረዋል፣ በቂ ጥያቄዎችን ስናቀርብ ነበር።

በዚህ አብዛኞቻችሁ እንደተጠቀመችሁ ተስፈኞች ነን😊

ማንኛውም ስራ ከጅምሩ ስሆን ብዙ ፈተናዎች እና እንቅፋቶች እንደምኖሩ ግልጽ ነው፣
እኛንም በ2014 ብዙ ተስፋ ሚያስቆርጥ እንቅፋቶች አጋጥሞን ነበር።

እናንተ የEntrance hub መጀመሪያ አመት ተማሪዎች ስለሆነችሁ የአንዳንድ ክፍተቶች ሰለባዎች ነበረችሁ🙈

👉 የሰዓት ጉደይ= አንዳንዴ በሰዓቱ አለማቅረባችን

👉አልፎ አልፎ መጥፋት በተለይ ወደ መጨረሻው አከባቢ🙈


👉ሁሉም ትምህርት በእኩል አለማቅረባችን

👉የመጨረሻውን Exam ለሁላችሁም በሚሆን መልኩ በቀላሉ Access እንድታደርጉ አለማድረጋችን እና ሌሎች ጥቃቅን ክፍታቶች እንደነበሩብን ተገንዝበናል።

ሆኖም ግን የአቅማችንን ያህል ጥረት ስናደርግ ነበር፤ በዚህ ደስታኞች ነበር።

አሁን ከእናንተ አንድ ነገር እንፈልጋለን🙏
የነበረን ቆይታ እንዴት ነበር? ምን ያህል ተጠቃሚ ነበረችሁ?
ለEntrance Exam ዝግጅ እንድታደርጉ የእኛ አስተዋጽኦ ምን ያህል ነበር?
ከዚህ በኃላ Entrance hub ለመማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች ስለ Entrance hub ምን ትላላችሁ?
እናዚህ እና መስተካከል ያሉብንን ነገሮችን ጨምራችሁ👇👇
በ Voice ወይም በText ብቻ ለእናንተ በሚመቻችሁ መንገድ በcomment box አስቀምጡልን🙏
የእናንተ አስተያየት ለእኛ በጠም በጠም በጠም አስፈላጊ ስለሆነ ሁላችንም ብትሳተፉ ደስ ይለናል😍
ስለ ትብብራችሁን ከልብ እናመሰግናለን🙏🙏🙈


ተወዳጆች እንኳን በሰላም አጠናቀቃችሁ🙏

አብዛኞቻችሁ ወደ ቤታችሁ ጉዞ ላይ ነው ያላችሁት እና ክፉ እና እንቅፋት ሳይነካችሁ ወደ ቤት ግቡልን🙏🥰

1k 0 1 10 13

ተወዳጆች ሆይ እንደምን አደራችሁ! ቀኑም ደረሰ ፣ ዛሬ ጥቅምት 4 ላይ እንገኛለን። ከትምህርት ቤት የቀራቹን ነገር አስተካክሉ ፣ ከማህበራዊ ሳይንስ ለዩኒቨርሲቲ የሚያሰፍልጋችሁን መረጃ ጠይቁ ።

በሉ እንድግዲህ በእኛ በኩል ከእናንተ ጋር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተባብለን ፣ አንጠራራም ፣ የ Freshman course ተማሪዎች ናችሁ ፣ ትሆናላቹም ‼️ 🥰

ተወዳጆች ሆይ ምንም አትፍሩ ። እንሆ ከወዲሁ እኛም መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን።

የፈተናው ቀን ለእናንተ የተሰጠኝ ወብ ቀን ናት እና የከፍታችሁ፣ የሰላማችሁ ፣ የምትከብሩበት ቀን ትሁንላችሁ! ሰላማችሁ የበዛ ይሁን! እናንተና የእናንተ የሆነው ሁሉ ይጠበቅ! ለምልሙ! አብቡ! ይመርባችሁ! ያቀዳችሁት ይሳካላችሁ! ምንም ክፉ አጠገባችሁ አይቅረብ! ይህንን ሁሉ ፈጣሪ ያድርግላችሁ! እነዚህና ሌሎችም መልካም ነገሮች ሁሉ ሲሆኑላችሁ ግን ሞልቶ ለሌሎች መትረፉንና ማካፈላችሁን አትዘንጉ!

ሁሌም የእናንተ የእናንተ ነው ‼️ ማንም አይነካውም ። እንዳትፈሩ አደራ 🙏

መልካም ግዜ ይሁንላችሁ 😊
Entrance Hub Ethiopia

@EntranceHubEthiopia


👉ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤

👉 ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።

👉አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።

👉ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።

👉 በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር::

👉 ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤

👉በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።

👉ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።

👉በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።

👉ወቅቱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ወቅት ነውና ለተፈታኞች በሙሉ መልካም ፈተና ተመኘን👏👏👏👏


☝️በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!
========================
👉ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው 👉ያይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤

ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤
------------------------------------------------
☝️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።

☝️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡

👌ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። 

☝️ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።

☝️ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ እርማት እንድናረግም ያግዘናል።

☝️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። 


በትምህርት ምንስቴር ውሰኔ ደስተኛ ናችሁ?
So‘rovnoma
  •   አዎ ነኝ ፣ ተመችቶኛል
  •   በጠም ያስጠላል፣ ምንም ለውጥ የለውም
119 ta ovoz


ያው የደወላቹልኝ ተማሪዎች ታውቃላችሁ ብዬ አስባለሁ 😊 ከደወላቹልኝ ሰዓት ጀምሮ ነው ፣ እንደገና ተመልሼ Chemistry እና Biology Answer ይዘጋጀሁት ። Already Biology 97% በላይ Solve ለማድረግ ሞክሪያለው ። ነገር ግን Chemistry 73% የሚሃለውን ያህል ነው Solve ለማድረግ የሞከርኩት ሌሎቹን እናንተ ሞክሯቸው።

በዚህ ጊዜ እኛ ሙሉ ለሙሉ 2015 ተፈታኞች ፣ ዝግጅት እያደረግን ነበር ‼️ እናንተ ላይ አሁን በቅርቡ እንደመጀመራችን አንጻር ብዙ ክፍተቶች ነበሩብን ፣ ለ2015 ተፈታኞች እሄንን ክፍተት ለማስወገድ እና ተጨማሪ ነገሮችን ለመጨመር ጥረት እያደረግን ስለሆነ ነው ትንሽ የዘንጋናችሁ 🙏 ለማንኛውም በርቱ ፈጣሪ ከእናንተ ጋር መልካም ፈተና ይሁንላችሁ 🙏












Chemistry ይቀጥላል ትንሽ ጠብቁን.....


Biology Grade 12 Answer.pdf
84.7Kb
ከላይ የለቀቅነው የጥያቄዎቹ መልስ ነው ።

ጥያቄዎቹ ሲዘጋጁ የተዘለለ ተራ ቁጥር አለ ። ከሱ ውጪ ሁሉንም መልስ አቅርቢያለው ።

በርቱ ፣ እኛ ከጎናችሁ ነን ።




👆👆👆👆👆👆👆
እሄንን File ተመልከቱ👆

ዛሬ ከ Entrance Hub ተደውሎልን ነበር ። Chemistry እና Biology ለምንድነው የ12ኛ በUnit ክፍል የተከፋፈለውን ጥያቄ መልስ ያልቀረበልን የሚል ነበር ። 😊 እስከዛሬ የመቆየቱ ሁኔታ የእናንተ ችግር ነው ‼️ ምክንያቱም እኛ ነሃሴ 27 ነበር Programኡን ያጠናቀቅነው ፣ እሄንን ደግሞ እናንተን አማክረን የወሰነው ውሳኔ ነበር ። ነገር ግን በማሃል እስከ አሁን እገዛ እያደረግን ነበር ‼️ እናንተ ግን የሚያስፈልጋችሁ ሲቆም እራሱ ዝም ነበር የምትሉት።

ይሁን እና ዛሬ ሁለቱንም እናቀርባለን እና በተቻላችሁ አቅም ለመጠቀም ሞክሩ ፣ ፈጣሪ ከእናንተ ጋር ይሁን 🙏





20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

171

obunachilar
Kanal statistikasi