ተፈቀደ‼️
የኢንዱስትሪ ፓርኮች የምርታቸውን 50 በመቶ ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ ተፈቀደ‼️
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች 50 በመቶ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ መፈቀዱን #የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች ምርታቸውን ሙሉ በሙሉ ለውጭ ገበያ እንጂ ለሀገር ውስጥ ማቅረብ ሳይፈቀድላቸው መቆየቱን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን ለኢዜአ ገልጸዋል።
ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ተጽዕኖ ሥር የነበሩ ባለሃብቶችን ለማበረታታት በፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ኩባንያዎች 50 በመቶ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲያቀርቡ በአዋጅ መፈቀዱን አስታውቀዋል።
ይህ እርምጃ ኩባንያዎች ምርታማነትን ለማሳደግ ብቻ ሳይሆን ለሸማቹ ማኅበረሰብም የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በቅርቡ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አዋጅ መውጣቱን አስታውሰው፤ አዋጁ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ ዞን እንዲሸጋገሩ የሚያደርግና በማክሮ ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
አዋጁ የኢንቨስትመንት ከባቢን የሚፈጥር፣ ከአፈጻጸም ጋር ተያይዞ የሀገር ገጽታን የሚያጎድፉ ድርጊቶችን የሚያስወግድ፣ የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራርና መናበብን የሚያጎለብት እንደሆነ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው ለውጭ ኩባንያዎች ዝግ በነበሩ ዘርፎች በችርቻሮም ሆነ በጅምላ ንግድ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው መመሪያ ለኢንቨስትመንት ዘርፉ ትልቅ ዕድል ነው ብለዋል።
For more upcoming news Join now‼️👇👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
የውስጥ መስመር👉 t.me/ayulaw