አሏህ በዚህ አይቀጣም
~~~~~~~~~~~~~
ኢብኑ ዑመር [ረዲየሏሁ ዓንሁማ] እንዳስተላለፉት የአሏህ መልዕክተኛ [ﷺ] ሰዕድ ኢብኑ ዑባዳን ለመጠየቅ ሄዱ። ዐብዱረሕማን ኢብኑ ዐውፍ፣ ሰዕድ ኢብኑ አቢወቃስ እና ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ አብረዋቸው ነበሩ። የአሏህ መልዕክተኛ [ﷺ] አለቀሱ። ሰዎች የአሏህን መልዕክተኛ [ﷺ] ማልቀስ ሲያዩ እነርሱም አለቀሱ። መልዕክተኛውም [ﷺ] እንዲህ አሉ፦
«ታደምጣላችሁን?! አሏህ በዓይኖች እንባና በልብ ሐዘን አይቀጣም። የሚቀጣውም የሚምረውም በዚህች ነው» አሉና ወደ ምላሳቸው አመለከቱ። [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይህን ሐዲስ ያላዩ ሰዎች “ለቅሶ” ልንደርስ ሂደን ስናለቅስ ማውገዝን ፈልገው ፊታቸውን ያጨማዳሉ። እንደው ለታመመና ለሟች ማልቀስን ኩነኔ አድርገው ይወስዳሉ። ከ“ወንድነት” ጋ የሚጋጭ እንደሆነም ያስባሉ። ይሄ ስህተት ነው። ለሟች ማልቀስ አይከለክልም። በአግባቡ እንባ ማፍሰስ፣ ማልቀስ የሚከለክል ነገር የለም። የሚከለከለው ሙሾ ማውረድና እየጮኹ ማልቀስ፣ ሌሎችንም ማስለቀስ ነው። ነቢዩ [ﷺ] በዚህም ሐዲስና በሌሎችም እንደመጣው ጣዕረ-ሞት ላይ ያለን ሲያዩ፣ ለሟችም ያለቅሱ ነበር። የልጃቸው ኢብራሂም ሞት ጊዜ፣ የሴት ልጃቸው ልጅ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ሲጠጣቸው የተከሰተው ይታወቃል (ዓይናቸው እንባ አፍሷል)፣ እንባ ማፍሰስንም ከእዝነት ቆጥረውታል (ከልብ ከሆነ ነው)፣ የአሏህንም እዝነት ያስገኛል። በሌላ በኩል እየጮኹ ከሶብር ጋ በሚጋጭና የአሏህን ውሳኔ ማጥላላት በሚመስል መልኩ ማልቀስ፣ ኮሌታ መቅደድ፣ ደረት መደብደብ፣ ጉንጭ መቧጠጥ ክልክል ነው። እንደዚሁም ሙሾ ማውረድ በጥብቅ ተከልክሏል፣ “አርጋጅ” እያንጎራጎረች፣ የሟችን ጥሩ ጎን እያነሳች የምታስለቅስን ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃት ተናግረዋል (ወንድ ቢሆንም ያው ነው!)
ሌላ ሟች በቤተሰቡ ከልክ ያለፈ ለቅሶ ወይም እሪታ እንደሚቀጣ የሚያመለክት ሐዲስ መጧል ነገር ግን ይሄ ሙሾ እንዲያወርዱለት፣ እንዲያስለቅሱለት፣ እነርሱም እየጮኹ ከልክ በላይ እንዲያለቅሱለት ተናዞ የሞተ እንደሆን ነው። አንዲት ንጹህ ነፍስ የሌላውን ሀጢያት አትሸከምም።
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
https://t.me/AbubilalIbnuseid