ሱቡሉ ሰላም سُبُلُ السَلامْ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


በቻናሉ የሱና ፅሁፎች፣ ግጥሞች፣ የተለያዩ ድምፆች፣ ቪድዬዎች፣ ጠቃሚ ፎቶዎች ይገኙበታል። እርምት አስተያየት ጥቆማ እዚህ ቡት ላይ ያስቀምጡ👉 t.me//subul_bot
«تَوَفَّنِي مُسْلِمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ»
“ሙስሊም ሆኘ ግደለኝ። በመልካሞቹም አስጠጋኝ” [ዩሱፍ፡101]

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


‏• - قالَ شيخُ الإسلامِ ابنُ تيميَّةَ
• - عليه رحمات رب البرية - :

• - من صار إلى قولٍ مقلدًا لقائله لم يكن له أن ينكر على من صار إلى القول الآخر مقلدًا لقائله ؛ لكن إن كان مع أحدهما حجة شرعية وجب الانقياد للحجج الشرعية إذا ظهرت ، ولا يجوز لأحد أن يرجح قولاً على قول بغير دليل ولا يتعصب لقول على قول ولا قائل على قائل بغير حجة ؛ بل من كان مقلدا لزم حكم التقليد ؛ فلم يرجح ؛ ولم يزيف ؛ ولم يصوب ؛ ولم يخطئ : ومن كان عنده من العلم والبيان ما يقوله سمع ذلك منه فقبل ما تبين أنه حق ورد ما تبين أنه باطل ووقف ما لم يتبين فيه أحد الأمرين ، والله تعالىٰ قد فاوت بين الناس في قوى الأذهان كما فاوت بينهم في قوى الأبدان ، وهذه المسألة ونحوها فيها من أغوار الفقه وحقائقه ما لا يعرفه إلا من عرف أقاويل العلماء ومآخذهم فأما من لم يعرف إلا قول عالم واحد وحجته دون قول العالم الآخر وحجته فإنه من العوام المقلدين ؛ لا من العلماء الذين يرجحون ويزيفون ، والله تعالىٰ يهدينا وإخواننا لما يحبه ويرضاه : وبالله التوفيق ، والله أعلم .

📜【 مجموع الفتاوىٰ (٢٣٣/٣٥) 】
‏༄༅‏༄༅‏༄༅❁✿❁ ‏༄༅‏༄༅‏༄


ደካም ተፈርቶ ሌት እያንቀላፉ፣
ረሃብ ተፈርቶ ቀን እየለፉ፣
ወቅት አባክነው እየተንጓፈፉ፣
በየገበያው እየጎረፉ፣
ሕልም በማየት፣
ቋምጦ በመመኘት፣
ሻሉን በማጣፋት፣
ኮሮጆ በመጎተት፣
ከአሕሉ ሳይጎነበሱ፣
ሶብረው ሳይታገሱ፣
በዝናብ ሳይበሰብሱ፣
መስኣላ ሳይምሱ፣
ኩቱብ ሳያተራምሱ፣
ጅስምን ሳያሳሱ፣
ሬት ሳይቀምሱ፣
ችጋር ሳይልሱ፣
ሌት ሳይነቁ፣
ቀን ሳይጠባበቁ፣
እንዴት ይመጣል?!
በየት ይገባል!
ያ ዓሊሙ
ያ ሰመድ በያለንበቱ፣
አግራልን ዒልሙን ከማጀቱ።

(ሸይኽ ዐብዱረሕማን-ኒዟም-ወሎ)


ወደ ወሎ ነው


አሏህ በዚህ አይቀጣም
~~~~~~~~~~~~~
ኢብኑ ዑመር [ረዲየሏሁ ዓንሁማ] እንዳስተላለፉት የአሏህ መልዕክተኛ [ﷺ] ሰዕድ ኢብኑ ዑባዳን ለመጠየቅ ሄዱ። ዐብዱረሕማን ኢብኑ ዐውፍ፣ ሰዕድ ኢብኑ አቢወቃስ እና ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ አብረዋቸው ነበሩ። የአሏህ መልዕክተኛ [ﷺ] አለቀሱ። ሰዎች የአሏህን መልዕክተኛ [ﷺ] ማልቀስ ሲያዩ እነርሱም አለቀሱ። መልዕክተኛውም [ﷺ] እንዲህ አሉ፦
«ታደምጣላችሁን?! አሏህ በዓይኖች እንባና በልብ ሐዘን አይቀጣም። የሚቀጣውም የሚምረውም በዚህች ነው» አሉና ወደ ምላሳቸው አመለከቱ። [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይህን ሐዲስ ያላዩ ሰዎች “ለቅሶ” ልንደርስ ሂደን ስናለቅስ ማውገዝን ፈልገው ፊታቸውን ያጨማዳሉ። እንደው ለታመመና ለሟች ማልቀስን ኩነኔ አድርገው ይወስዳሉ። ከ“ወንድነት” ጋ የሚጋጭ እንደሆነም ያስባሉ። ይሄ ስህተት ነው። ለሟች ማልቀስ አይከለክልም። በአግባቡ እንባ ማፍሰስ፣ ማልቀስ የሚከለክል ነገር የለም። የሚከለከለው ሙሾ ማውረድና እየጮኹ ማልቀስ፣ ሌሎችንም ማስለቀስ ነው። ነቢዩ [ﷺ] በዚህም ሐዲስና በሌሎችም እንደመጣው ጣዕረ-ሞት ላይ ያለን ሲያዩ፣ ለሟችም ያለቅሱ ነበር። የልጃቸው ኢብራሂም ሞት ጊዜ፣ የሴት ልጃቸው ልጅ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ሲጠጣቸው የተከሰተው ይታወቃል (ዓይናቸው እንባ አፍሷል)፣ እንባ ማፍሰስንም ከእዝነት ቆጥረውታል (ከልብ ከሆነ ነው)፣ የአሏህንም እዝነት ያስገኛል። በሌላ በኩል እየጮኹ ከሶብር ጋ በሚጋጭና የአሏህን ውሳኔ ማጥላላት በሚመስል መልኩ ማልቀስ፣ ኮሌታ መቅደድ፣ ደረት መደብደብ፣ ጉንጭ መቧጠጥ ክልክል ነው። እንደዚሁም ሙሾ ማውረድ በጥብቅ ተከልክሏል፣ “አርጋጅ” እያንጎራጎረች፣ የሟችን ጥሩ ጎን እያነሳች የምታስለቅስን ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃት ተናግረዋል (ወንድ ቢሆንም ያው ነው!)
ሌላ ሟች በቤተሰቡ ከልክ ያለፈ ለቅሶ ወይም እሪታ እንደሚቀጣ የሚያመለክት ሐዲስ መጧል ነገር ግን ይሄ ሙሾ እንዲያወርዱለት፣ እንዲያስለቅሱለት፣ እነርሱም እየጮኹ ከልክ በላይ እንዲያለቅሱለት ተናዞ የሞተ እንደሆን ነው። አንዲት ንጹህ ነፍስ የሌላውን ሀጢያት አትሸከምም።
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
https://t.me/AbubilalIbnuseid


እታለም እንቢ በይ!
~~~~~~~~~~
ጉዳችን ፈጠጠና
ግርማችን ተነነ፣
ሐይባችን ተገፎ
ክብር ኮሰመነ፣
እኛ ሟሽሸንና
ሞገሳችን መነመነ፣
አጥራችን ተጥሶ
ጠላት መረቀነ።

(አንተዬ)
የምንሰማው ያማል፣
የምናየው ይቀፋል፣
ቆሽት አሳርሮ ልብ ይሰባብራል፣
ጅስም አከሳስቶ ወዘና ያነጣል፣
እየሰረሰረ እንቅልፍም ይነሳል፣
ቅስም እየሰበረ አንገትም ያስደፋል፣
ምቾትም ከልክሎ ዳኢም ይገግባል፣
ላይበርድ እየተፋጀ ህመምን ይዘራል።

(ስማኝ...እህ ብለህ)
በትልቅ ሰው ስም የተሰየመችው፣
ከዶዬ ተብላ የተለቀበችው፣
ከእስላም ቤት የፈለቀችው፣
በጡሃራ ማህፀን የተረማመደችው፣
ደግ! የደግ ልጅ የተከበረችው፣
ጥንፍፍ የጥንፍፍ ልጅ የተንኳለለችው፣
ንጥር! አተኩሮ ያየን ልብ ምትመታው፣
ሙስሊሟ እህቴ ጉፍታ ያጣፋችው፣
ያቺ ሳቂታዋ
የኔዋ የኔዋ
ሒጃብ አጥላቂዋ፣
“ከኛ ናት” “የኔ ናት” እያልኩኝ!
ያ መናጢ ወሰደብህ አሉኝ፣
ተቀማህም አሉኝ፣
አዎ! ነጠቀኝ እርግጥም ነጠቀኝ፣
ኢስቲንጃ የሌለው ከፈራ ፈጀራ፣
ከሃዲ አስተባባይ በተውሒድ ያልተገራ፣
እንጨት የሚሳለም ለስዕል የሚሰግድ፣
ካ'ንድም፣ ለሶስት አምላክ ከቶም የሚያረግድ፣
ኸምር አተራማሽ ቅርሻት የሚተፋ ነቢን
የሚያጥላላ፣
ስብዕናው የወረደ፣ የዘቀጠ የሆነ ተላላ።

(ይኼው ነው)
ወራት ተቆጠሩ አመታት አለፉ
የ“ከዶ” ሰውነት በየከኒሳው ይለፋሉ ሳያርፉ፣
ያ ሱጁድ የተደፋ ግንባር ረክሶ፣
ያ ዚክር ያደረገ ምላስ ኮስሶ፣
ሂጃብም ተገፉ ቀልብም ተነጅሶ፣
“ላ ኢላሃ ኢለላህ” ተረስቶ የሁሉ ምስሶ፣
ለቅርፃቅርፅ ስዕል ተዋረደው ይደፋሉ፣
ድንጋይ ይስማሉ እንጨት ይሳለማሉ!
ቅርቤ ብትሆንም የቁም ሟች ናት ለኔ!
አይሽ ተበላሸ! ኧረ ዋ ኔ! ዋ ኔ!
አፅናን ያ አላህ! ጠብቀን ያ ሰመድ!
ግደለን በኢስላም በሙስጦፋ መንገድ!

የምንሰማው ያማል፣
የምናየው ይቀፋል፣
ቆሽት አሳርሮ ልብ ይሰባብራል፣
ጅስም አከሳስቶ ወዘና ያነጣል፣
እየሰረሰረ እንቅልፍም ይነሳል፣
ቅስም እየሰበረ አንገትም ያስደፋል፣
ምቾትም ከልክሎ ዳኢም ይገግባል፣
ላይበርድ እየተፋጀ ህመምን ይዘራል።

(እስቲ እንተወው!)
የሄደውስ ሄዷል፣
የመጣውም መጧል፣
የፈሰሰ ውሃ በ'ፍኝ አይታፈስም፣
እንቁላል ተሰብሮ ከቶም አይጠገንም።

(ያለሽው እህቴ)
ማር በሚተፋ ምላሱ አይደልሽሽ
አይሸንግልሽ!
ጤፍ በሚቆላ ምላሱ
ከቶ አያታልሽ፣
ዋ! እንዳትሆኚ የሳት ራት!
ዋ! ላንቺ! ዋ! መንጠራራት!

(እቴዋ)
ሂሳብ አለ፣
ሲራጥ አለ፣
ላስተባባይ ጀሃነም አለ፣
ኧረ ብዙ ጉድ፣ ስንት ጭንቅ አለ!
ተይ ብዬሻለሁ! ተይ ተመከሪ!
ዲንሽን ጠብቂ፣ ነኝ ላንቺ መካሪ!
ኢስብሪ፣
ሶብሪ፣
ነገ እንዳትጠወልጊ፣
እጅሽን አ'ዘርጊ!
ፈራሽ ነው ገላሽ፣
በስባሽ ነው መልክሽ!
የከዶዬ እጣ አንቺን አያግኝሽ!
ገምና በሌላው ይማር!
ንቂ! እታለም ጎርፉ አይውሰድሽ።

(እቴዋ)
የአላህ ተቀናቃኝ የነቢ ጠላት፣
የኢብሊስ ጁንድ
የተሳለ ኢስላምን ለማጥፋት፣
የሸይጧን ጓደኛ፣ ካፊር አይሆንሽም!
ሌባ ላመሉ ነው!
ገባሁልሽ ቢልም፣ ላንቺ አይበጅሽም።

(እስቲ ልጠይቅሽ)
ከተማ ተትቶ ውርማ ይገባል ወይ?
ፋኖስ ሳይያዝ ጨለማ ይዘለቃል ወይ?
እቱ ወንድ አልጠፋም! ጫካውን ተከልከይ!
ሙሽርክን ከሃዲ ኢስቲንጃ የሌለው!
ቁረጪ እታለም! እንቢ በይ! እንቢ በይ!

(ዐብዱልከሪም ሰዒድ)
@Ibnuseid99
23.1.13
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
@AbubilalIbnuseid


Forward from: Unknown
ጥሩ ከሆነ ሸር አድረጉት


ያንን ጉድ ፍልሚያ የታደመውን
ትርምስ ፍላጻውን፣ የሰይፉን ፉጨት
የታዘበውን
የጀግኖችን ጽናት የርሶን ገላ
መቁሰል የተመለከተውን
ባጎቶትም ጀብዱ የተደመመውን
እሱ ሚሳሳልሁ አንቱም 'ሚወዱትን
ሞገስ የደፋውን ጀበሉ ኡሁድን
ያንን የተረገጡትን ከምርጦቹ ጋራ
(ውዴዋ...!)
አይተነው እንሙት ያገርሁን ተራራ።

አሏሁሙ ሶሊ ዓላ ሙሐመድ [ﷺ]
ዐብዱልከሪም ሰዒድ
የጁሙዕ ሌሊት ነው ሶላት ዓለ ነቢ እናብዛ!
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
https://t.me/AbubilalIbnuseid


ሚዛኑ ይስተካከል
~~~~~~~~~~
«በዚህ ዘመን አብዛኛው ሰው ዑለማን የሚለይበት (የሚገምትበት) ሚዛን ተዛብቷል። ደራሽ (መሳጭ) የሆነን ተግሳጽ ያስተላለፈን፣ ታዳሚ በበዛበት ሙሐደራ ያደረገን፣ ተውቦ የጁሙዕ (ዕለት) ኹጥባ (ምክር) ያስተላለፈን በፈትዋ (ብይን) ጉዳይ የሚመለሱበት ዓሊም (አዋቂ)ና ከርሱ እውቀት የሚወሰድ አድርገው ይወስዳሉ። ይኼ አስከፊ አደጋ ነው፣ መዘዙም የሚንሰራፋ፣ ጉዳቱም ተዛማች ነው። በጥብቅ የሚወገዝ እንደሆነው ሁሉ። ደግሞም እውቀትን ባለቤቱ ወዳልሆነው ማስጠጋት ነው የሚሆነው።!
“(አንድ) ጉዳይ ባለቤቱ ወዳልሆነው ከተጠጋ ቂያማን ተጠባበቅ”»

ሸይኽ ዐብዱሰላም በርጂስ
[عوائق الطلب (ص: ٣٣)]
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
https://t.me/AbubilalIbnuseid


ግርም ከሚሉኝ አባባሎች “ኡስታዜን አትንኩ!” የሚለው አንዱ ነው። ግልፅ ግልጡን የአንድ ኡስታዝን ስም ጠቅሰው (ከየትኛውም ወገን ይሁን!) እርሱን አትንኩት የሚሉ ሰዎች አይዋጡኝም (ፕሮፋይልም የሚያደርጉ እንዳሉ ሆነው) እኔ ከዚህ ምረዳው የፈለገውን ይናገር፣ ይጻፍ በቃ አትንኩንት አትንኩት! የሚለውን ነው። ይሄ ደግሞ ግልፅ ወገንተኝነት ነው። መዘዝም አለው። መልካም ሲሰራ “በርታ” “አብሽር” ማለት ሌላ ነገር ነው። ወዳጄ! በህይወት ያለ ሰው ምሉዕ እምነት አይጣልበትም፣ ሊንሸራተት ይችላል። አንተ ስታወድሰው “አትንኩት” እያልክ ደጀን ስትሆንለት የነበረው አቋሙንና እይታው ሊዘወር ይችላል፣ ያለበትና የቆመበት ስህተት ከሆነም ሲመከር እንኳ እንዳይሰማ “እሱን አትንኩት” እያልክ ነፍሲያና ሸይጧንን በርሱ ላይ አብሽሩ ማለት ነው የሚሆነው። ራስህን ወደ አንድ ኡስታዝ ወይም ሸይኽ... ሙልጭ አድርገህ አስጠግተህ ሲወጣ ለመምከርም፣ ለማውገዝም አቅም ያሳጣል (አይቼዋለሁ)
በቃ አንዳዶቹ እርሱን “የነካ”፣ እርምት የሰጠውን ሁሉ (እርምት የሰጠ ሁሉ ትክክል ነውም አይባልም) ስህተት ላይ የወደቀ አድርገው ሲቆጥሩ እናያለን (እኔንም አንድ ሰሞን ተጠናውቶኝ ነበር!) ቆይ! እርሱ ልክ እንደኛ ሰው አይደለ እንዴ? ሰው ደግሞ ፍጹም አይደለማ? መቼም አዎ ነው መልሱ።
ለማንኛውም ከመልዕክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ውጭ ለግለሰብ ምሉዕ ወገንተኝነት ተቀባይነት የለውም።
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
https://t.me/AbubilalIbnuseid


መሸቃው
~~~~~
መሸቃው ሲመጣ ነው
ሰው 'ሚፈተነው፣
ሰፈር ሲወጡ ነው
ጠባይ የሚታየው፣
ገብሱ ከ'ንክርዳዱ ሲታሽ ነው
ሚለየው፣
ጎርፉ ሲያዳርስ ነው ወዳጅ 'ሚታወቀው።
ቅልጥም ስትነጭማ ሁሉም
ይጋረሃል፣
ኪስህ ከደለበ ማርሻል ያጅበሃል፣
ሸርተት ያለ ጊዜ ጓድ ይነጠራል
ወበቅ ይነፈሳል!
ችግሬን አከብረው! ጓዴን አሳይቶ
ዋሾን ገልጦልኛል።

ዐብዱልከሪም ሰዒድ
20/1/13
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
https://t.me/AbubilalIbnuseid


የዊትርን ነገር አደራ
~~~~~~~~~~~
የዊትር ሰላት ጠንካራ፣ የፅና ሱና ነው! (ሀነፊዬች ዋጂብ ነው ይላሉ)። የዊትር ሰላት ቀላሉ (ትንሹ) ረከዕ አንድ ነው፣ ወቅቱ ከዒሻእ ሰላት በኋላ የሚጀምር ሲሆን የሚገባደደው ፈጅሩ አሷዲቅ ሲወጣ (ጎህ ሲቀድ) ነው። ጎህ ሳይቀድ እንቃነለሁ ብሎ የተማመነ፣ የመንቃት ልምድ ያለው ሰው የሌሊቱ መጨረሻ ላይ መስገዱ ለሱ በላጭ ነው። አልቆምም፣ እንቅልፍ ይጥለኛል ብሎ የፈራ ሰግዶ መተኛቱ ለሱ በላጭ ነው። የዊትር ሰላትን ያስለመደ ሰው በህመም ወይም በእቅልፍ ምክንያት ያመለጠው እንደሆነ ቀን ላይ (ሸፍዕ በማድረግ) ቀዷ ያወጣል።
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
https://t.me/AbubilalIbnuseid


Forward from: قناة العلامة محمد سعيد رسلان
Video is unavailable for watching
Show in Telegram


እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ
~~~~~~~~
አየን ‘ሲያጌጡ’ እየገዙ ሲቀዳዱ
ልታይ ልታይ ሲሉ ከምዕራቡ
ሲቀዱ
ትንቢት ሲረጋገጥ ሲፈፀምም አየን
የኛው ዘመን ሆኖ ጉዳጉዱን ታዘብን
(ታዘብን)
አሳሳች ተዘንባይ ለብሰው ያለበሱ
ጸጉር 'ሚቆልሉ ከራስ የተጣሉ
በቁም የበሰበሱ!
የስልጣኔን ጫፍ የወጡ መስሏቸው
ዝንብ ማስተናገድ ምንም
አይገዳቸው! (ተውኳቸው)

(እህቴዋ)
ድህነት የተባለን ያን ክፉ ደዌ
ያን ጨካኝ ገዳይ
ስንቱን የረታውን ስንቱን የመታውን
ያለገላጋይ
አዋርደሽ ቀጣሽው ድል አደረግሽው
እጅ አልሰጥ ብልሽ ሰፋፍተሽ ለበስሽው!
ድንቅ ነሽ ድንቅ ነሽ
ከወዴት ተከሰትሽ?
ብቅ ያልሽ ጊዜ ሁሉንም አስደመምሽ
እኔንም ነካካኝ
እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ?!

ዐብዱልከሪም ሰዒድ
17/1/13
(ፎቶው ላይ ኒቃቧን እንዴት ሰፍታ አንደለበሰች ላስተዋለ አንጀት ይበላል፣ እያላችሁ የምትገላለጡ፣ ልታይ ልታይ ባዮች ሞት ሳይመጣ ተመከሩበት!)
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
https://t.me/AbubilalIbnuseid


Forward from: 🇮ዲን መመካከር ነው-الدين النصيحة🇮
ይደመጥ ይደመጥ ይደመጥ ..
🔊ተከታታይ የሙሐደራ ግብዣ ቁ.29
በአነስተኛ ሳይዝ የቀረበ
7.5Mb ብቻ .. Amr file
በአሏህ ፍቃድ ህይወታችንን ይቀይራል ብዬ ያሰብኩት ሙሐደራ ነው .. በጀነሀም ካልተመከርን በምን እንመከር???
@Ibnyahya7


ክፍል_ 3⃣1⃣

🖋📚 ተከታታይ ጽሁፍ፦ የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን ወሳኝ የህይወት ታሪክና ገድል የሚዳስሰው "#ኢብኑ_ተይሚያ_የሱናው_አንበሳ" የተሰኘው መጽሀፍ

[ለ] ከአሕመዲያ ሱፊዮች ጋር ክርክር
ከክ/ል 30የቀጠለ፦

ሪፋዒያዎቹ ብዙ ሆነው ተገኝተዋል። እራሳቸውንና አካላቸውን እያወዛወዙ የተለያዩ ሸይጧናዊ ትእይንቶቻቸውን ማሳየት ጀመሩ። እጅግ ሰፊ ህዝብ ነው የታደመው። ሌላው ሸይኻቸው ዳግም እርቅ ቢወርድ እንደሚሻልና ካለፈው ጥፋት ተውበት ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ ከቢድዐዎቻቸው ተመልሰው ሸሪዐውን ለመከተል ፍቃደኛ እንደሆኑ ተናገረ። ሌላኛው ተነሳና አንገታቸው ላይ ስለሚለብሱት ሰንሰለት ሲከላከል ኢብኑ ተይሚያ ጠንካራ መልስ ሰጡት።

ሪፋዒዩ ሸይኽ፦ የአራቱንም መዝሀብ ቃዲዎች እንድትሰበስብልን እንፈልጋለን። እኛ ሻፊዒዮች ነን።

ኢብኑ ተይሚያ፦ ይሄ በየትኛውም ዓሊም ዘንድ አግባብ አይደለም። እንዲያውም ሁሉም ከዚህ አይነቱ ዒባዳ ይከለክላሉ። እንደ ቢድዐ ነው የሚቆጥሩት። ይሄው ሸይኽ ከማሉዲን ኢብኑ ዘምለካኒ አለ። የሻፍዕያ ሙፍቲ ነው።
“ከማሉዲን! በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ትላለህ?!”

ከማሉዲን ዘምለካኒ፦ ቢድዐ ነው አይወደድም። እንዲያውም የተጠላ ነው።

ሪፋዒዩ፦ “እኛ ዟሂር የሆነውን ሸሪዐ የሚከተሉ ሰዎች የማይቋቋሙት ሁኔታዎችና ማንም የማይገታቸው ስውር ነገሮች አሉን” አለ እየጮኸ።

ኢብኑ ተይሚያ፦ ዟሂር፣ ስውር... የለም! ሁሉም ወደ አላህ ኪታብና ወደ መልዕክተኛው ﷺ ሱንና መመለስ አለበት እንጂ ወደ ሸይኾች ወደ ሱፍዮች፣ ወደ ንጉሶች፣ ወደ አሚሮች፣ ወደ ዑለማዎች፣ ወደ ዳኞች ወይም ወደ ማንም ሊመለስ አይገባም። ይልቁንም ሁሉም ፍጡር አላህንና መልእክተኛውን ﷺ መታዘዝ ግዴታቸው ነው። አምባረቁበት።

ሪፋዒዩ፦ “እኛ ከራማዎች እና እሳት ውስጥ መግባትን የመሰሉ ማንም ጋር የሌሉ ነገሮች አሉን። ስለዚህ ለኛ እጅ መስጠት ይገባል” ብሎ ጮኸ።

ኢብኑ ተይሚያ፦ እኔ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የሚገኝ እያንዳንዱን ሪፋዒ እወራረዳለሁ! የትኛውንም እነሱ በእሳት ላይ የሚሰሩትን ለመስራት ዝግጁ ነኝ። የተቃጠለ ተሸናፊ ነው። ባይሆን በቅድሚያ አካላችንን በኮምጣጤና በሙቅ ውሃ ከታጠብን በኋላ ነው! (በቁጣ ተናገሩ።)

ሪፋዒዩ፦ እሳት ውስጥ መግባት እንደሚችል ተናገረ።

ኢብኑ ተይሚያ፦ “ተነስ” አሉት ደጋግው።

ሪፋዒዩ፦ ቀሚሱን ሊያወልቅ እጁን አነሳ።

ኢብኑ ተይሚያ፦ በጭራሽ! በቅድሚያ በሙቅ ውሃና በኮምጣጤ መታጠብ አለብህ!

ሪፋዒዩ፦ “አሚሩን የሚወድ እንጨት ያቅርብ” እያለ እንዳልሰማ ሆኖ ቀጠለ።

ኢብኑ ተይሚያ፦ ይሄ ነገር ማራዘም፣ ሰውንም መበተን ነው። አላማችንም አይሳካም። ጧፍ ይቃጠልና ከታጠብን በኋላ እኔም እናንተም ጣታችንን እናስገባ። ጣቱ የተቃጠለ የአላህ እርግማን በሱ ላይ ይሁን።

ሪፋዒዩ፦ ፊቱ ተለዋወጠ፣ ተዋረደ።

ኢብኑ ተይሚያ፦ ከዚህም ጋር እሳት ገብታችሁ በሰላም ብትወጡም፣ በአየር ላይ ብትበሩም፣ በውሃ ላይ ብትራመዱም፣ የፈለጋችሁትን ብትሰሩም ሸሪዐን ለመፃረርና ለማፍረስ የምትሰሩትን ስራ ልክ አያደርግላችሁም። ምክንያቱም ትልቁ ደጃልም ሰማይን ”አዝንቢ” ሲላት ታዘንባለች። ምድርን “አብቅይ” ሲላት ታበቅላለች። ፍርስራሽ ምድርን “የተቀበረ ሀብትሽን አውጪ” ሲላት ወጥቶ ይከተለዋል። አንድን ሰው ገድሎ ለሁለት ከፍሎ ከጣለው በኋላ “ተነስ” ሲለው ይነሳል። ይህ ሁሉ ከመሆኑም ጋር ግን ቀጣፊ፣ ውሸታምና እርጉም ነው። የአላህ እርግማን በሱ ላይ የሆነ።

ይህን ማለታቸው በታዳሚው ልቦና ላይ ትልቅ ተፅእኖ አሳድሯል። መሻይኾቻቸው እርቅ ፍለጋ አሚሩን መማፀን ቀጥለዋል። ኢብኑ ተይሚያ ግን ሰዎቹ በእሳት ሊያሳዩ የተጎረሩትን ነገር ያሳዩ ዘንድ ደጋግመው እየወተወቱ ነው። በሃገር ያሉ መሻይኾቻቸው እንዳለ ተገኝተዋል። በጣም ብዙ ናቸው። አደባባዩ በህዝብ ጩኸት እየተናጠ ነው። ህዝቡ እንዲህ እያለ ያስተጋባል፦

{فَوَقَعَ الْحَقُّ وَبَطَلَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ (١١٨) فَغُلِبُوا هُنَالِكَ وَانقَلَبُوا صَاغِرِينَ (١١٩)}
“እውነቱ ተገለፅ! ይሰሩት የነበሩትም (ድግምት) ከንቱ ሆነ!! እዚያ ጋ ተሸነፉ!! ወራዶችም ኾነው ተመለሱ!!” [አልአዕራፍ፡ 118-119]

ሪፋዒዮቹ፦ እጅጉን ተሸማቀቁ። ትላንት ሲያረግድላቸው የነበረው ህዝብ ፊት ተዋርደው እየተሳለቀባቸው ነው። አለመቻላቸውና አጭበርባሪነታቸው ሲደግፏቸው ለነበሩት አሚሮች ጭምር ይፋ ሲሆን ጊዜ አፈገፈጉ። ስላለፈው ሁሉ ተውበት ጠየቁ።

አሚሩ፦ ከነሱ ምን ትፈልጋለህ?

ኢብኑ ተይሚያ፦ ቁርኣንና ሱንናን መከተል። ከመፃረርም መመለስ። ለምሳሌ ቁርኣንና ሐዲሥን መከተል በነሱ ላይ ግዴታ እንዳልሆነ ከማመን መመለስ። ለማንም ከቁርኣንና ከሱንና የመውጣት መብት እንደሌለው እንዲታመን።

ሪፋዒዮቹ፦ በቃ ቁርኣንና ሱንናን አጥበቀን ይዘናል። አንገታችን ላይ ከምናጠልቀው ሰንሰለት ውጭ በኛ ላይ የምትቃወመው ነገር አለህን? ይሄው እናወጣለን!

ኢብኑ ተይሚያ፦ እነዚህም ይሁኑ ሌላ ባጠቃላይ ሁሉም ሙስሊም ለአላህና ለመልእክተኛው ﷺ ትእዛዝ ታዛዥ የመሆን ግዴታ አለበት።

አሚሩ፦ ምንድን ነው ከቁርኣንና ከሱንና የሚጠበቅባቸው?

ኢብኑ ተይሚያ፦ ከቁርኣንና የሱንና ህግ ብዙ ነውና በዚህ መድረክ ላይ መዘርዘር አይቻልም። ነገር ግን የተፈለገው ባጠቃላይ ለዚህ ተገዥ እንዲሆኑ ነው። ከዚህ የወጣ አንገቱ ይቀላ።

አሚሩ፦ በጣቱ ወደ ህዝቡ እያመላከተ አፅንኦት ሰጠው። አላማው ህጉ ሁሉንም ህዝብ የሚመለከት ነው ለማለት ነው።

የሰዎች ሞራል የተነቃቃበት ትልቅ ጉባኤ ነበር። አማካሪዎች፣ ዑለማዎች፣ አሚሮች፣ ባሉበት ከቁርኣንና ከሱንና ያፈነገጠ በሰይፍ አንገቱ ሊቀላ ተወሰነ። “ይቀጥላል!”
___
📖ኢብኑ ተይሚያ የሱናው አንበሳ ከገፅ 88 እስከ 91
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
~~~ #በአላህ_ፍቃድ_ይቀጥላል~~~
✍️ዐብዱልከሪም ሰዒድ
📆[እሑድ] #ሶፈር 9 1442 ሂ. #መስከረም 17 2012 ዓል #Sep 27 2020 GC.
📕ዝግጅት፦ ሙሐመድ አሕመድ ሙነወር
📝#ሼር በማድረግ ሌሎችን ያስነብቡ!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📣የቴሌግራም ቻናላችንን ጆይን ያድርጉ፦ https://t.me/AbubilalIbnuseid


ወዳጆች!
በሶሻል ሚዲያ በተለይ #Facebook ላይ የሁለቱ ሐረሞች ስራ አስኪያጅና ፕሬዝዳንት ክቡር ሸይኽ ዐብዱረሕማን አስ-ሱደይስ በጠና እንደታመሙና እንደደከሙ፣ እንደሞቱም የሚናፈሰው ወሬ ቅጥፈት ነው። ዛሬ በመካ መስጂደል ሐረም የዒሻ ሰላት እደሚመሩ ተገልጿል።


አመስግን፣ ይጨመርልሃል!
~~~~~~~~~~~~~~
ኢብኑ ከሲር [ረሂመሁሏህ] እንዲህ ይላሉ፦
«(አሏህ) አጠቃላይ (በሰጣችሁ) ጸጋዎቹ ሁሉ እንድታመሰግኑት ቢጠይቃችሁ፣ ቢያዛችሁ ኖሮ (ምስጋና) ማድረስ አትችሉም፤ ታክታችሁ፣ ድክማችሁ ትተውት ነበር። ቢቀጣችሁ ደግሞ በደለኛ ሳይሆን ይቀጣችሁም ነበር። ነገር ግን እሱ (አሏህ) መሓሪ አዛኝ ነው፤ ብዙውን ይቅር ይላል። በጥቂቷ (ስራችሁ) ይመነዳል»

وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ اللَّهَ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
«የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና» [ነሕል፡ 18]
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
https://t.me/AbubilalIbnuseid


ወደ ሰዎች ችግርህን ስታቀርብ በከፊልም ቢሆን ሊቀርፉልህና ረሃብህን ሊያስታግሱልህ ይችላሉ፣
ወደ አሏህ ስታሰሙት ግን ህመምህ ይወገዳል፣ ስብራትህ ይጠገናል፣ ህይወትህ ይቃናል፣ የርሱን ውዴታን ትጎናጸፋለህ። ምክንያቱም ሲጨቀጭቁት ይወዳል፣ አይሰለችም፣ ካዝናው አይነጥፍም።

«‘ጭንቀቴንና ሐዘኔንና የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ’ አላቸው፡፡» [ዩሱፍ፡ 86]
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
https://t.me/AbubilalIbnuseid


ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ [ረሂመሁሏህ] እንደሚሉት ሙእሚን በርሱና በአሏህ መካከል የሚቀር ወንጀል፣ ሃጢያት ከፈጸመ በአስር ምክንያቶች ከቅጣት ሊድን እንደሚችል ይናገራሉ። ከአስሮቹ ምክንያቶች አንዱ ሰውየው በህይወት እያለም ሆነ ከሞተ በኋላ ኢስቲግፋር የሚያደርጉለት፣ ምህረት የሚጠይቅሉት፣ የመልካም ስራቸውን ምንዳ በስጦታ የሚያበረክቱለት ወንድሞች ያሉት እንደሆነ ወንጀለኛ ቢሆን እንኳ አሏህ ይቅር ብሎት፣ ከጀሃነም ነጃ ይለዋል። ሷሊሆችን፣ ደጋጎችን መጎዳኘት፤ እነርሱን መወዳጀት ብዙ ጥቅሞች አሉት። ዱንያ ላይ ወደ መልካም ይጎትቱናል፣ ከመጥፎ ይከለክሉናል። ቀድመናቸው ብንሻገር ጨርሶ አይረሱንም፣ ምህረት ይጠይቁልናል፣ በዱዓቸው ያስታውሱናል። ይሄ መታደል ነው። ተስካር ወይም ሰደቃ በልቶ የሚበተን ወዳጅ አይጠቅመንም፤ ስለዚህ ደጋጎችን ለራሳችን ስንል እንጎዳኝ፣ ሷሊሆችን እንወዳጅ።
•┈┈•◈◉✹❒🔸❒✹◉◈•┈┈•
©ሱቡሉ ሰላም-سبل السلام
https://t.me/AbubilalIbnuseid


Forward from: ? قناة السنه السلفية?
قال الشيخ صالح الفوزان:

فعذاب القبر قد ينقطع عن الميت المؤمن العاصي
إن كان يُعذَّب في قبره، بسبب دعاء أو صدقة.

شرح العقيدة الواسطية 144.

20 last posts shown.

1 674

subscribers
Channel statistics