አቡ ዩስራ - ንጽጽራዊ አስተምህሮ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የአቡ ዩስራ ንጽጽራዊ ሀይማኖት ላይ ያተኮሩ የፁሁፍና የድምጽ ስራዎች ይቀርቡበታል።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


አጀንዳ መቀማት ስትራተጂ
 
①ቤተክርስቲያን ላይ ጂሃድ ታውጆብናል

—እስካሁን እንዲህ ያለ ሙስሊም አለገጠመኝም።

②አነበበ እንጂ አልፃፈም
— የልጁን ብልግና ለመሸፈን የሚደረግ ከንቱ ጥረት።

③መክስስ ከፈለጋችሁ ቁርኣንና ሐዲሳቹን ክሰሱ እንጂ ልጁ ምን አጠፋ

④ህግ ባለበት ሀገር ይገደል እያላችሁ ነው

—ህግ ባለበትም እኮ አንከሰስም እያላችሁ ነው።

⑤ጀነት ለመግባት ክርስቲያኖችን መግደል ያስፈልጋል
— ንፅፅርም ላይ እንዲህ ነው የምታስቸግሩን የማይገናኘውን በግድ ጠምዝዞ ማገናኘት።
  
⑥ከርስትናን የሚያጥላሉ መፅሀፍት ትፅፋላችሁ።

— በቤተክርስቲያን ደረጃ የሚታተሙ ልጁን  የሚያስንቁ ስድቦች እኮ ሞልተዋል።የመፅሀፍቱን ብዛት እንኳ ለውድድር አይቀርብም።

⑦እየሱስን አምላክ አይደለም ሰው ነው ትላላችሁ ።
—ታዲያ ተውና በየመንገዱ በየታክሲው እየሱስን ተቀበል አትበሉን።/The funniest argument  known/

⑧እኛም ___ ነን

— መቼ ከለከልናችሁ።

ይሄ ሁሉ አጀንዳ ለመቀማት ነው ትኩረታችን ልጁ በህግ እንዲዳኝ ነው ሌላው ገብስ ነው።


Forward from: የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ከብሮድካስት ባለስልጣን ፍቃድ አውጥቶ የሚሰራ ህጋዊ ሚዲያ ነው። ይህ ሚዲያ ከተራ ዩቲዩበር እንኳን የማይጠበቅ የበሬ ወለደ ትርክት ዩቲዩቡ ላይ ለጥፏል። ከሰሞኑ በነበሩ ጉዳዮች ቤተ ክርስቲያን ላይ ፍለጠው ቁረጠው ያለ ግለሰብም የለም። የብሮድካስት ባለስልጣን በዚህ አይነት ግጭት ቀስቃሽ ተግባር ላይ እርምጃ እንደሚወስድ እጠብቃለሁ። ዋናው ጉዳይ ግን ነውረኛ ተግባር የፈጸመውን ልጅ ለመከላከል የሚሄዱበት ርቀት ምክንያቱ ምንድን ነው? የሚለው ነው። የተወሰነውን ልንገራችሁ፦

ሚዲያውን ከመመስረት ጀምሮ በበላይ ጠባቂነት እየመሩ የሚገኙት ከሲኖዶሱ ሊቀጳጳሳት መካከል የሆኑት አቡነ ሄኖክ ናቸው። አቡነ ሄኖክ ደግሞ የምዕራብ አርሲ ሀገር ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩ ሰው ናቸው። ታዲያ ይህ ነውረኛ ግለሰብ (እፎይ) ከየት መጣ ብለው ከጠየቁ ደግሞ መልሱ "ከአርሲ" የሚል ነው። ነውሩን ለመከላከል በሚያደርጉት ግብታዊ ጥረት ሳቢያ ብልግናውን መዋቅራዊ እያደረጉት ነው፥ ያሳዝናል።

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
https://t.me/Yahyanuhe


ቀጣይ ተቃውሞ

እንዴት ብንደፈር ነው የሀይማኖት ጉባኤ መግለጫ አንዳንድ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን የሚወቅሰው ልጁ እኮ ያወራው በማስረጃ ነው ?😒


የናንተ ሲሳደቡ ለምን አላስቆማችሁም?

ቆይ እኔ የምለው የኛንም ወገኖች ሲሳደቡ ከሰን ፍርድ ቤት አቁመን ፣ እናንተም ስትሳደቡ ከሰን ፍርድ ቤት አቁመን እንዴት ይሆናል? እናንተ የት ሄዳቹ ነው እኛ ስናጠፋ ዝም የምትሉት? እኛ ህጋዊ መንገድ እንደተከተልንው ህጋዊ መንገድ ተከትላቹ የማትጠይቁን ፣ እኛ ዝም እንዳልንው እናንተም ዝም በሉ እንዴት ይባላል? መጀመሪያም ዝም እንድትሉ እምነታችሁ የሚያዛችሁ ከሆነ አሁንም ዝም በሉ።


Forward from: የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
በየሰንበት ትምህርት ቤቶች ሳይቀር መዋቅሩን ጠብቆ ስለ እስልምና ትምህርት ለመስጠት ፕሮፓዛል ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መግባቱን ሲያወሩ ሰማሁ። በእርግጥ አሁን ስድቡን ፎርማላይዝ ለማድረግ ካላሰቡ በቀር ድሮም በአቃቤ እምነት ዘርፍ እስልምናን የተመለከቱ ትምህርቶችን ይሰጣሉ። ይህ ተግባር የኦርቶዶክሱ ብቻ ሳይሆን የፕሮቴስታንቱም ኮሌጆች "Muslim christian relation" በሚል የዳቦ ስም እስከ ማስተርስ ዲግሪ ድረስ ይሰጡበታል። ለአብነት የኢቫንጀሊካል ቲዮሎጂካል ኮሌጅን (ETC) ኮርስ አውትላይን ብትመለከቱት ይህ ኮርስ ቁርኣንና ሐዲስ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰጥ በግልጽ ይዘረዝራል።

በሙስሊሙስ በኩል ሌላውን እንተወውና የሚመጡ ትችቶችንና ጥያቄዎችን መልስ መስጠት የሚያስችል መዋቅራዊ ድጋፍ/ስራ አለ ወይ? ከተባለ፥ ጠላትም ወዳጅም ይወቀው "የለም" ነው። የንጽጽር ወንድሞች በግል ተነሳሽነት ከሚያደርጉት ትግል ውጭ የሚጠቀስ ምንም ነገር የለም። በአባት ተቋሙም በኩል ከጥቂት ሰዎች የግል ተቆርቋሪነትና ፍላጎት ውጭ ካሪክለምን ያማከለና ነገን የተመለከተ ይህ ነው የሚባል መዋቅራዊ ስራ የለም።

በሌላው እምነት በኩል የሚሰራው ስራ አንገብግቧቸው ያላቸውን ጊዜና ጉልበት ሁሉ ሰጥተው ይህንን ታሪካዊ ስራ መስመር አስምረው ለማለፍ የለፉ ጥቂት ወንድሞች ግን ጉዳያቸው ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘቱ ሳይሳካላቸው ቀርቷል። በሌላው በኩል የሚሰራውንና መጭውን ፈተናችንን ላየ ግን ዛሬ ችላ ላልነው ድክመታችን ሁሉ አላህ እድሉን በሰጠን መጠን ነገ እሱ ፊት ምን ብለን እንደምንመልስ አላህ ይወቅ። በዚህ በኩል ያለው ጉዳይ አስጨንቆት የሚታገል አዲስ ትውልድ ከመጣ ቢያንስ መስመሩን ገር በማድረግ እናግዘው..!

© የሕያ ኢብኑ ኑህ


⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe


ሙስሊሞች ለምን የንፅፅራዊ ሃይማኖቶች ጥናት አስፈለጋቸው?

አሁን አሁን «ሙስሊሞች ለምንድነው የአይሁድና የክርስትና እምነት አስተምህሮዎችን ርዕሰ ጉዳያቸው አድርገው የሚያስተምሩት?»፤ «ለምን የሌላው እምነት ይነካሉ?»፤ «ለምንስ የራሳቸው እምነት ብቻ አያስተምሩም?»፤ «በኢየሱስ ማንነት እና ምንነት ላይ ከመናገርም ሆነ ከመፃፍ ለምን አይታቀቡም…?» የሚሉ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ሲነሱ ይስተዋላል፡፡
እውን ሙስሊሞች የንፅፅራዊ ሃይማኖት ጥናትን እንደ አንድ አጀንዳ መያዛቸው ጠብ አጫሪነት ነው ወይስ በተጨባጭ ምክኒያትና አመክንዬ ላይ የተመሰረተ? ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦች ሙስሊሞች ለምን የንፅፅራዊ ሃይማኖት ጥናት እንደሚያጠኑና ምንም ዓይነት የትንኮሳ ዓላማ (በተለይ ኦርቶዶክስን) እንደሌላቸው በአጭሩ ያስረዳሉ፡፡

1. ሙስሊሞች ምንም እንኳን በዒሳ (ኢየሱስ) ላይ በወረደው ኢንጂል (ወንጌል) እና በሙሳ ላይ በወረደው ተውራት (ኦሪት) የሚያምኑ ቢሆንም ቁርኣን ግን ከእነዚህ መፅሐፎች በኋላ የወረደ እንደመሆኑ በነዚህ መፅሐፍት ላይ የተፈፀሙትን የመበረዝና የመቀየር ስራዎች እንዲሁም የመፅሐፎቹ ተከታይ ነን የሚሉትን ክርስቲያኖች እና አይሁዶችን ሰፊ ትኩረት በመስጠት ይተቻል፡፡ «የመፅሐፉ ባለቤቶች ሆይ!» በሚል የሚጀምሩ በርካታ ክርስቲያንና አይሁድን የሚያናግሩ አናቅፅ በቁርኣን ውስጥ እናገኛለን፡፡ ሥላሴ፣ የኢየሱስ ጌትነት፣ የኢየሱስ መሰቀል አለመሰቀልና ሌሎችም በርካታ ክርስቲያኖች የነእሱ አጀንዳ ብቻ የሚመስሏቸው በርካታ ጉዳዮች ቁርኣን በሰፊው ዳሷቸዋል፡፡ በመሆኑም አንድ ሙስሊም ስለነዚህ ጉዳዮች ሲያወራ ቁርኣን ትኩረት ስለሰጠው አንድ የኢስላም አጀንዳ እንጂ ከቁርኣን ጋር ግንኙነት ስለሌለው የሌላ እምነት አጀንዳ ብቻ ስለሆነ ነገር እያወራ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ክርስቲያን ወንድሞቻችን ይህን ጉዳይ ለመረዳት ወንጌል በወቅቱ የነበሩትን አይሁዶች የተቸበትን ሁኔታ ቢያገናዝቡ ጠቃሚ ይመስለናል፡፡ ፈጣሪ አዲስ ኪዳን ውስጥ ከፊል አይሁዶችን “የአመንዝራ ልጆች” ብሎ በመጥራቱ እንደማይወቀስ ሁሉ በቁርኣንም መፅሐፍ ቅዱስን የበረዙ ወይም ኢየሱስን ፈጣሪ ነው ያሉ ክርስቲያኖችን በመተቸቱ ሊወቀስ አይችልም፡፡

2. ምንም እንኳን ከላይ የጠቀስነው ጉዳይ ለአንድ ሙስሊም ንፅፅራዊ ሃይማኖትን ለማጥናት መሰረታዊው እና በቂ ነጥብ ቢሆንም በአገራችን ለተሰሩት ንፅፅራዊ ስራዎች መንስኤ የሆነው ዋናው ጉዳይ ግን መጠነ ሰፊ የሆነው የሚሽነሪዎች ሃይማኖትን በስንዴና በዘይት የማስቀየር ስራ ነው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ካለባት የኢኮኖሚ ችግር አንፃር በርካታ በምዕራቡ ዓለም የሚረዱ መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶችን ለማስተናገድ የተገደደች ሲሆን እነዚሁ ድርጅቶች የሚሰጡት ዕርዳታ ብዙ ጊዜ በስብአዊነት ላይ ብቻ የተመረኮዘ ከመሆን ይልቅ አብሮ የፕሮቴስታንት እምነትን ከማስፋፋት ጋር የተያያዘ መሆኑን ከሙስሊሞች በላይ ብዙ አማኞቿን የተነጠቀችው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትረዳዋለች፡፡ ሚሽነሪዎች ለአንድ ችግረኛ ሙስሊም ስንዴና ዘይት ሰጥተው “ኢየሱስ ጌታ ነው!” ሲሉት እኛ ደግሞ እንደነሱ ኢኮኖሚያዊ አቅም ስለሌለን መርዳት ባንችል የቀረበለትን ኢየሱስን የመቀበል ጥያቄ መመለስ የሚያስችለው “እውን ኢየሱስ ፈጣሪ ነው?!” የሚል ሲዲ ወይም መጽሐፍ ብናቀርብለት ትንኮሳ ነውን?

3. ከላይ እንደጠቀስነው ዋነኛው ንፅፅራዊ ስራዎች የተሰሩበት ዐላማ የፕሮቴስታንቱን የማክፈር እንቅስቃሴ ለመቀነስ የታለሙ እንጂ በምንም መልክ የኦርቶዶክስ አማኞችን ያነጣጠሩ አልነበሩም፡፡ በነዚህ ስራዎች የተፈለገው ኦርቶዶክስን መተቸት ቢሆን ኖሮ ኦርቶዶክስ ከሌሎች የክርስቲያን አንጃዎች የሚለይባቸውን እንደ ታቦት፣ ቅዱሳን፣ ቅርፃቅርፆች የመሳሰሉ ጉዳዮችን በሰፊው መተቸት ይቻል ነበር፡፡ ነገር ግን የስራዎቹ ዓላማ ይህ አይደለም፡፡ እንደሚታወቀው በአገራችን የተሰሩት አብዛኞቹ የንፅፅር ስራዎች የዶ/ር ዛኪር እና የሸኽ አህመድ ዲዳትን ስራዎች ከመተርጐም ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ደግሞ ትምህርት የሰጡባቸው አገሮች ያሉት ክርስቲያኖች ፕሮቴስታንት አልያም ካቶሊክ እንጂ በፍፁም ኦርቶዶክስ አይደሉም፡፡

4. በሌሎች የክርስቲያን አንጃዎች የኦርቶዶክስን መሰረታዊ እምነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚተቹ በርካታ መፅሐፍት የተሰሩ መሆኑ እየታወቀ ሙስሊሙ በሰራቸው ኦርቶዶክስን ለይቶ በማይመለከቱ መፅሐፎችና ሲዲዎች ምክንያት ረብሻ ለማስነሳት መሞከሩ ከበስተጀርባው ፖለቲካዊ ዓላማ ሊኖረው እንደሚችል ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባል፡፡

5. ሙስሊሙ የሚሰራቸው ስራዎች አሁን በክርስቲያኖች እየተፃፈ እንዳለው በስድብና በማንቋሸሽ ላይ የተመሰረቱ ሳይሆን ምክንያታዊና ትህትና የተሞላበት አቀራረብ ነው፡፡ በመሰረቱ አንድ ሙስሊም እንደ ዒሳ (ኢየሱስ) እና መርየም የተከበሩ ሰዎችን ቢሰድብ ከእምነቱ እንደሚወጣ (እንደካደ እንደሚቆጠር) መታወቅ አለበት፡፡

6. በቁጥር 3 እንደተጠቀሰው በአገራችን የተሰሩት አብዛኞቹ ንፅፅራዊ ስራዎች የዶ/ር ዛኪርና የሸኽ አህመድ ዲዳት ስራዎች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች የሰጧቸው ትምህርቶች ወይም ያደረጓቸው ክርክሮች በአብዛኛው የተደረጉት እንደ ደቡብ አፍሪካ፣ ኖርዌይ፣ አሜሪካና ህንድ … የመሳሰሉ ሙስሊሞች በጣም አናሳ ወይም የሉም የሚባልበት አገሮች ሲሆን የትኛውም አገር ግን አንዳችም ችግር አልፈጠሩም፡፡ ተቃውሞ ካላቸው ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ አለመስማማታቸውን ከመግለፅ ባለፈ ሃይማኖታችንን አንቋሸሽክ ብሎ ጠብ የፈጠረ ሰው አለመኖሩን ሲዲዎቹ ይመሰክራሉ፡፡

7. የተሰሩት ሰራዎች ሚሽነሪዎችን የመከላከል ዓላማ እንጂ ኦርቶዶክስ ላይ ያነጣጠሩ አለመሆናቸውን የሚያረጋግጥልን ሌላው ነጥብ አገራችን ላይ የንፅፅራዊ ሃይማኖት ትምህርት በመስጠት ላይ ያሉ ሙስሊም ግለሰቦች ለትምህርት የተንቀሳቀሱባቸውን ክልሎች ብናጤን በአጠቃላይ የሚሽነሪ እንቅስቃሴ የሚበዛባቸው የደቡብና ከፊል የኦሮሚያ ክልሎች ብቻ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ኦርቶዶክስ ወደሚበዛባቸው የትግራይ ወይም የአማራ ክልል ሄዶ ንፅፅራዊ ትምህር ሰጥቶ የሚያውቅ ሰው የለም፡፡

8. አንዳንድ ግለሰቦችና ሚዲያዎች የንፅፅራዊ ሃይማኖት ጥናት ፅሁፎችን አገራችን ላይ መጀመሪያ የሰሩት ሙስሊሞች እንደሆኑ በመጥቀስ በክርስቲያኑ ወገን አሁን እየተፃፉ ላሉት ፈር የለቀቁ ተሳዳቢ ፅሁፎች ሙስሊሙን ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን ከብዙ አስርት ዐመታት በፊት ጀምሮ የሙስሊሙን እምነት የሚያንቋሽሹና የትችትን ሥርዓት ያልጠበቁ እንደ “ተዐምረ ማርያም”፣ “አፍሪቃና እስልምና” እና “ሙሐጀባ”… የመሳሰሉ መፅሐፍት መኖራቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

9. በሙስሊሙ በኩል ከክርስትና ጋር ግንኙነት ያላቸው መፅሐፍት ወይም ሲዲ ሲሰሩ የማስታወቂያ ፖስተሮች የሚለጠፉት መስጅዶች አካባቢ ብቻ እንጂ እንደሌሎቹ እምነቶች በየአደባባዩና መንገደ ላይ አለመሆኑ አሁንም በነዚህ ስራዎች ዓላማ የተደረገው ሙስሊሙ ራሱን ከሰባኪዎች ሊከላክልበት የሚችል ነገር ማስጨበጥ እንጂ ክርስቲያኑን መተንኮስ እንዳልሆነ በግልፅ ያሳያል፡፡

© ከ 9 አመት በፊት የተዘጋጀ ፅሁፍ


Forward from: የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
"እስልምና የሰይጣን ሀይማኖት ነው" "ሙስሊሙ ሁሉ አሸባሪ ነው" ወዘተ በሚሉና መሠል እስልምናን እንዲሁም ሙስሊሞችን በከፍተኛ የጥላቻ ቃላት በመወረፍ የሚታወቁት ሰባኪ ፍራንክሊን ግራሀም ዛሬ ሀገራችን ናቸው። አዲስ አበባ ሲገቡ በመንግስት ደረጃ ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸውም "ሰበካቸውን" አቅርበዋል። ይህንን ጉዳይ በዋናነት ኃላፊነት ወስዶ ፕሮግራሙን ያሰናዳው ደግሞ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስሉ ነው። በእርግጥም ካውንስሉ ይህንን ሁሉ ነውራቸውን እያወቀ ነው የጋበዛቸው? በዚህ መልኩ የሚታወቁ የጥላቻን መምህር የጋበዘውስ ምን እንዲያስተምሩለት ነው? ይህ ሲርየስሊ የሚታይ በጣም አደገኛ ነገር ነው..!

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Yahyanuhe


ما لم يأخذه العدو بالحرب لن يأخذه بالتهديدات والحيل.

أبو عبيدة


እንኳን ለ 1,446ኛው የተከበረው የረመዷን ወር ፆም አላህ በሰላም በጤና አደረሳችሁ። አላህ ወሩን ተቀባይነት ያለው የዒባዳ፣ የዚክር፣ የዱዓና የቂርኣት  ያድርግልን።


© Copy


ጥያቄ: —
ቁርኣን በሱራ 2:7 ላይ  ያላመኑትን ሰዎች አይን ሸፍኖ፣ጆሮና ልብ ላይ  አትሞ ለምንድ ነው በእኔ አላመናችሁም ብሎ የሚቀጣቸው? ይሄ  ከኣምላክ የማይጥበቅ የፍትህ መዛባት ነው።


خَتَمَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ وَعَلَىٰ سَمۡعِهِمۡۖ وَعَلَىٰٓ أَبۡصَٰرِهِمۡ غِشَٰوَةࣱۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمࣱ

አላህ በልቦቻቸው ላይ በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል፤ በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አልለ፤ ለነሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡

መልስ:—

1) በመጀመሪያ የአንቀፁ  ሙሉ ሃሳብ ለማግኘት ከቁጥር 6 ጀምሮ መነበብ አለበት። ሰለዚህ " እነዚያ የካዱት ሰዎች ብታስፈራራቸውም ባታስፈራራቸውም በነርሱ ላይ እኩል ነው አያምኑም " ካለ በዃላ ነው ።እንደነዚህ አይነት ሰዎች በ"ክህደታቸው " ምክንያት ነው ይህ ቅጣት የሚጣልባቸው። [ቁርኣን 4:155]


2) አላህ ሱወ ምንግዜም ቅን የሆኑ ሰዎችን ያውቃል ይመራቸዋልም። ለሰው እንጂ ለአምላክ ይህ ቀላል ነገር ነው። ከኛ ውስጥ ማን መመራትን (ቅናቻን) እንደሚፈልግ። ማን መጥመምን እንደሚፈልግ አስቀድሞ ያውቃል። ከዚህም የተነሳ  አይደለም ምድር ላይ አቆይቶን ፣ ዛሬ ፈጥሮን ዛሬውኑ ፍርድ ቢሰጥ ፍርዱ ፍትሃዊ ነው።

3) አምላክ የሰውን ልጅ ሁለት ምርጫ ሰጥቶ የፈለገውን እንዲመርጥ ከነጥቅሙና ጉዳቱ ግልፅ አድርጓል [ ቁርኣን 76:3 እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲኾን መንገዱን መራነው፤ (ገለጽንለት) ] በዚህ ሒደት ውስጥ የነብያት ተልእኮ መልእክቱን ማደረስ ብቻ ነው። መመራት በአላህ ሱወ እጅ ያለ ጉዳይ ነው።እርሱ ቅኖቹን ዐዋቂ ነውና። [ቁርኣን 28:56 አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን ዐዋቂ ነው]

4.  ሰለዚህ ከላይ የተገለፁ ሰዎች [ ከሃዲዎች] ከክህደታቸው ከተመለሱ ወደ ቅኑ  መንገድ ይመራሉ ምክንያቱም ። አላህ ሱወ ለባሮቹ ክህደትን አይሻምና።[ቁርኣን 49:7]

እንዲህማ ባይሆን ትላንት የሌላ እምነት ተከታይ  የነበሩ ሰዎች በዚህ አንቀፅ እያሳበቡ ባልሰለሙ ነበር። ለእውነት ያደረጉት ጥረት ፍሬ እያፈራ በየግዜው ሰዎች ወደ እስልምና ይገባሉ።

ቁርኣን 8:38 ለነዚያ ለካዱት በላቸው፡- ቢከለከሉ ለእነሱ በእርግጥ ያለፈውን (ሥራ) ምሕረት ይደረግላቸዋል።


Forward from: ሒዳያ ንጽጽር /Hidaya Comparative/
ከትላንቱ በቀጠለው ስልጠናችን ከስቅለት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች የተመለከተው ስልጠና ተሰጥቷል። በኡስታዝ አቡ ዩስራ አማካኝነት የተሰጠው ይህ ስልጠና "The Non-Crucifixion Verse Q 4:157" በሚል ርዕስ የተሰጠ ሲሆን ከሰልጣኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል

https://t.me/Hidayaic8212


If you tell the truth, you don't have to remember anything.

©Mark Twain


ክርስቲያኖችና ሦስት ቁጥር ያላቸው ጠብ

"ልክ ስላሴ ለመረዳት እንደሚቸግረው ሁሉ ኢየሱስ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በምድር ሆድ ውስጥ ቆይቷል የሚለው ሌላኛው ስላሴ ነው"

ሁለቱም ለመረዳት የሚቸግሩ ናቸው።


Forward from: የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አማካኝነት የተዘጋጀውን ይህንን ስልጠና መውሰድ ለምትሹ ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ መመዝገብ ትችላላችሁ። እያንዳንዱ ስልጠና ለአንድ ቀን የሚሰጥ ሲሆን ከተመዘገባችሁ በኃላ በሚደወልላችሁ የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ስልክ ቁጥር አማካኝነት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በቴሌግራም ወይንም በዋትስአፕ ቀድመው መላክ ይኖርብዎታል።

- ለስልጠናው የምንፈልገው 15 ሰልጣኝ ብቻ ስለሆነ ስልጠናውን የመውሰድ እርግጠኛ እቅድ ከሌለዎት አይመዝገቡ።

https://bit.ly/4aK4Pq5


ታቦቴ ተፌዘበት ባሉበት አፋቸው ቁርኣንን እንኳን አቃጠለ ብለው ያዜማሉ።

የጥምቀት በዓል ተከትሎ በሃይማኖታዊ ስርዓቱ ላይ ያፌዙ ልጆች ነበሩ። አሁንም ድርስ እያፌዙ ያሉ አሉ።ልጆቹ አሁን እልህ ይዟቸው ፊታቸውን እየሸፈኑ ማሾፉን ቀጥለዋል።ልጆቹ ቢያገኙዋቸው ምን ሊያደርጉዋቸው እንደሚችሉ ሰሞኑን በተለያየ ቦታዎች ላይ እየተሰጡ ያሉ ኮመንቶች መመልከት በቂ ነው ። አለፍ ሲልም ቤተክርስትያኗም በግልፅ ይህን ድርጊት ብላ ባትገልፀውም ፣ከዚህ ድርጊት በዃላ በሃይማኖታዊ ስርኣቶቼ ላይ የሚቀልድ ከአሁን በዃላ አልታገሰም ብላ ገልፃለች።

ትላንት አንድ ግዜ ክርስቲያን ነኝ ሌላ ግዜ ሃይማኖት አልባ ነኝ ያለ ኢራቃዊ ሲውዲን ውስጥ በ 2023 በሙስሊሞች በአል ቀን ( ኢደል አደሐ) ቁርኣንን በአደባባይ በፖሊስ ተጠብቆ አቃጥሏል። ይህ ግለሰብ በዚህም ክስ ዛሬ ሀሙስ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ነበረው። የመጨረሻው ፍርድ ቀድሞ ወደ ጀሀነም ጀግኖች ሸኝተውታል።


Forward from: ሒዳያ ንጽጽር /Hidaya Comparative/
ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ከጉረባዕ ኢስላማዊ ድርጅት ጋር በመተባበር ላለፉት 6 ሳምንታት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል። በስልጠናው መሠረታዊ የንጽጽር አስተምህሮ የተዳሰሰ ሲሆን በቀጣይ በትብብር ስለሚሰሩ ስራዎችም ውይይትና ስምምነት ላይ ተደርሷል። ማዕከሉ ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰጣቸው ስልጠናዎችም በአላህ ፍቃድ ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል


ወንድማችን ኡስታዝ ወሒድ ዑመር አዲሱን መጽሀፉን (አልገደሉትም፣ አልሰቀሉትም) ሶስት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ እህቶች ወጭውን እንዲሸፍኑ በማስተባበር 100 መጽሀፍትን ለሒዳያ ላይብረሪ አስረክቦናል። በተጨማሪም በራሱ በኩል የእሱን መጽሀፍ የኦሮምኛ ትርጉም 100 ፍሬ የለገሰን ሲሆን ኡስታዝ ጀማል ደግሞ የአህመዲን ጀበልን "ክርስቶስ ማነው?" መጽሀፍ የኦሮምኛ ትርጉም ስራውን 100 ፍሬ አበርክቶልናል። እያንዳንዳቸው 100 መጽሀፍ በድምሩ 300 መጽሀፍትን ለግሰውናል። አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው፣ ከዚህ የበለጠ የሚተጉበትን ብርታትም ይወፍቃቸው።

© ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል


Forward from: የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
እስልምና ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎችንና በሀይማኖት ንጽጽር ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎችን ጥልቅ በሆነ መልኩ ስራዎችን ለመስራት እንዲያግዝ በማሰብ ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በስሩ የጥናትና ምርምር ዘርፍ አቋቁሟል።

በዚህ ዘርፍ ውስጥ የንጽጽር ዱዓቶችን ጨምሮ ተተኪ ወንድምና እህቶች ሰፊ ጊዜዎችን በመውሰድ ስራዎችን እንዲያጠኑ፣ በየቋንቋቸው የጥናት ውጤታቸውን እንዲያዘጋጁ በማመቻቸት ላይ ይገኛል።

ለስራውም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ አረብኛ እና እንግሊዝኛ የተጻፉ መጽሀፍትን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ሲሆን ለዚህ የሚያግዙ እናንተ ጋር የተቀመጡና ለተቋማችን ይጠቅማል የምትሏቸው መጽሀፍት ካሉ በሚከተለው ስልክ ቁጥር ለአስተባባሪዎች በመደወል መስጠት የምትችሉ ሲሆን ቢሮ መጥቶ መስጠት የሚችሉም ይበረታታሉ።

አድራሻ፦ ቤተል
ስልክ፦ 0910858830


ከዚህ በፊት አምላክ ተገርዟልን? ብለን ስንጠይቅ የሚሰድቡን ነበሩ ።አሁን ግን የግዝረቱ ቀንም ይከበራል።

"ጥር 6 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪት ሕግ የሆነውን ግዝረት የፈጸመበት ዕለት ጥር ስድስት ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ይከበራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋ ግዝረትን ተቀበለ፣ ለአባቶች የተሰጠውን ቃልኪዳን ይፈጽም ዘንድ›› ብሎ መስክሯል፡፡ (ሮሜ 15፥8)
መጽሐፈ ስንክሳር "

20 last posts shown.