"አምላክ" አይደለሁም ያለበት ቦታ!
አንዱ ነብይ ነኝ ብሎ ተነሳ፣ ህዝቡ ግን አላመነበትም። ስለዚህ ሰበሰባቸውና ዛሬ እኔ ነብይ መሆኔ በአደባባይ አረጋግጥላችዃለው አላቸው።
በል ማስረጃህን አቅርብ ሲሉት።
እሱ: እኔ በአሁን ሰአት በአዕምሮአቹ የምታስቡትን አውቃለው አላቸው።
ህዝቡ ማጉረምረም ጀመር ፣ በል ንገረንና እንመንህ አሉት።
እሱ፦ አሁን በዚህ ሰአት እያሰባቹ ያላችሁት ይህ ሰው ቀጣፊ ነው እያላቹ ነው አላቸው ይባላል።
እኛ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ኢየሱስ "እኔ አምላክ ነኝ" የሚል ስለራሱ የተናገረበት ንግግር መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የለም ብለን ስንጠይቅ መልሱ እንደሌለ የሚያውቁ ሰዎች የሚሰጡን ምላሽ፦
① አምላክነቱን ሊገልፅ አልመጣም ይላሉ
ሰው የሆነው ለእኛ ብሎ እስከሆነ ድረስ ፣ አምላክነቱን ለመግለፅ ምንድ ነው የሚያስፈራው? ምን እንዳይሆን ነው ሚስጢሩን የደበቀበት ምክንያት? ሞት ከሆነ እንደ እናንተ አስተምህሮ አልቀረለትም። ከግዜው በፊት እንዳይገሉት ፈርቶ ነው እንዳይባል "አምላክ ነው" ያለ ግዜው ቢገሉትም መነሳት ይችላል። ይህ ምላሽ አሳማኝ አይደለም።
② ነብያቶች ሲመጡ ነብይነታቸውን እንደሚገልፁ ሁሉ አምላክነቱን መግለፁ እና ማብራራቱ የሚጠበቅና ተገቢ ነው። ነብያቶቹን ግልፅ አድርጎ ራሱ ሲመጣ ግን "ተደብቆ " ለምን መጣ?
③ሌላኛው አምላክነቱን በግልፅ ለምን አልተናገረም? ተብለው ሲጠየቁ። "አምላክ አይደለሁም" ያለበትን ቦታ አምጡ አይደለሁም ካላለ ነው ማለት ነው የሚል አሲቂኝ መከራከሪያ ያመጣሉ።
እንዲያማ ከሆነ "አብርሀምም አምላክ አይደለሁም" ብሎ ቃል በቃል ስላልተናገረ አምላክ ነው ማለት ነው? ይሄ እጅና እግር የሌለው ሙግት ነው።
እናም እባካችሁ እንደ ሀሰተኛው "ነብይ ነኝ" ባይ የራሳችሁን መልስ ሳይሆን መሠረታዊ ሙግቱን ተከትላችሁ መልስ ስጡ!
https://t.me/Abuyusra3