اَلـسَـــلامُ عَــلَــيْـكُم وَرَحْـمَــةُ اَلـلـهِ وَبَــرَكـاتُـهُ
بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في الخير !!!
👑ለውዷ እህቴ ለውዱ ወንድሜ🌹
👑 ሙሸሪት & ሙሸራው 🛍
ለውዷ እህቴ👑
ቢስሚላህ ብየ ልጀምርላችሁ
ደስታዬን በግጥም ልተርክላችሁ
አልሀምዱሊላሂ ምስጋና ይድረሰው
ሀራምን ከልክሎ ሀላል ለፈቀደው
ለአለማቱ ጌታ ከአርሽ በላይ ላለው
ባረከሏህ ብዬ በጣም ልባርክልሽ
እጅግ ደስ ብሎኛል ኒካህ በማሰርሽ
ትዳርም መስርተሽ ኢማንሽም ሞላ
ምን ያስደስትሻል ታዳ ከዚህ ሌላ
የኛማ ሙሽራ በጣም ተውባለች
ከጅልባቧ በላይ ኒቃብ ደርባለች
ሙሽሪት አደራ ብዬ የምነግርሽ
ሀቁን ጠብቂለት ለውዱ ባልሽ
በሚያዝሽ ሰአት መርሀባ ብለሽ
ለችግሩ ሁሉ መፍትሄ ሁነሽ
በደስታውም ጊዜ አብረሽ ተደስተሽ
እንድህ ነው ቃልኪዳን እንድህ ነው ጋብቻ
ለውዱ ወንድሜ 🌹
ሙሽራው ልገርህ አድምጥ በጥሞና
ውዷ ባለቤትህ ስጦታህ ነችና
ተንከባክበህ ያዛት
የረሱል አደራ አማናህ ናትና
ሀቋን ጠብቅላት በምትችለው አቅም
እሷም በአቅምህ እንጂ በብዙ አትጠይቅም
ባረከሏህ ለኩም ይድመቅ ትዳራችሁ
በደስታ በፍቅር ትኑሩ ቤታችሁ
በደጋሜ ለውዷ እህቴ ለውዱ ወንድሜ መብሩክ
ደስታችሁ ደስታየ ነው
መብሩክ መብሩክ አልኩኝ ይመር ኒካሀቹ ይመር ትዳራቹ
በሸሪዓው መንገድ ይድመቅ ትዳራቹ
ፍቅር ይስፈን ሁሌ በቤት በኑሮቹ
ሁሉን ቻይ የሆነው የአለማት ጌታ
ሰርጉን መብሩክ ያርገው ለሁሉ አስተማሪ
አላህን ከማመፅ ከጭፈራ እርቆ
ሰርጋቹ በሱና ታየ አሸብርቆ
አላህምዱሊላህ እንኳን ደስ አላቹ
የፍቅር የደስታ ይሁን ትዳራቹ
ለኡማው ጠቃሚ አላህን ፈሪ
ሷሊህ ልጅ ይስጣቹ የአለማቱ ጌታ
ውዷ እህቴ የዛሬዋ ሙሽሪት
ውዱ ወንድሜ የዛሬው ሙሸራ
ይድመቅ ትዳራቹ ከሀላልህ ጋራ
አላህ አይለያቹ ፍቅራቹ ይበርታ
ቤታቹህ ትሙላ ሁልጊዜ በደስታ
አቦ እንዴት ያምራል ሰርግማ በሱና
አላህን ሳያምፁ በረሱል ጎዳና
ጭፈራና ዘፈን ሳይኖር ሀራም ነገር
የአላህ ቃል ሲወራ ሀዲሱ ሲነገር
መቀላቀል ሳይኖር ወንዱ ከሴቱ ጋር
ደምቆ ታየ ሰርጉ በሀላል በቁምጋር ነገር
እንግዲህ ፁሁፌን ቋጨሁት እዚህ
ለውዷ እህቴ ብየ መልካም ትዳር
ለውዱ ወንድሜ ብየ መልካም ትዳር
ቤታችሁ ትሙላ በሙሀባ ፍቅር🛍
በይ ተንከባከቢው ሀቁን ጠብቂለት
በደስታም በሀዘን ከጎኑ ቁሚለት
ከሷሊሆች ሁኝ ለትዳርሽ ብቁ
አላህን በመፍራት ሀቅ ከሚጠብቁ
ለባል ታዛዥ መሆን ኢባዳ ነውና
ፍቅርሽን መገቢው በንፁህ ልቦና
ትልቅ ደረጃ አለው ትዳር በእስልምና
ወሚን አያቲሂ ...... ብሏል ረበና
እናም እህት አለም ኢማንሽ ይሙላና
ትዳርሽን ያዥ ጠበቅ በይና ።
የእህትነት ምክሬን ለወንድሜ
ስማኝ አደራ እህቴን አታስከፋብኝ
በደስታም በሀዘን ከጎኗ ሆነህ
እንድታጫውታት አቅፈህ በክንድህ
ሚስትህ እኮ ላንተ ሁለ ነገርህ ናት
የፍቅርህ ምርኮኛ የተለየች ከእናት
ከምነግርህ በላይ በስፋት ብታውቅም
ሀቋን ጠብቅላት በምትችለው አቅም
ኸይሩኩም ሊአህሊህ ብለዋል ነብዩ
ምርጥ ባል ሁንላት የምጊዜም ልዩ።
🌹ተመኘሁላችሁ🌹
የሁል ጌዜ ደስታ የነፍስን እርካታ
የቀልብ ሰኪና ፍቅር ሳቅ ጨዋታ
መተሳሰብና መቻቻል ውደታ
ደስ በሚል ሂወት ባማረ ፈገግታ
ውደታ አሸብርቆ በጧትም በማታ
በፍቅራችሁ ፅኑ እስከ ዘለቄታ
አላህ ያዋዳችሁ የአለማቱ ጌታ
መልካም ልጅ ይስጣችሁ ለድኑ ጠቃሚ
እንኳን ደሰ አላችሁ በነብዩ ሱና ሆነ ጋብቻችሁ
ተዛዝናችሁ ኑሩ
ሁሌም ተዋዳችሁ
በኢማን አጊጡ
ሞቅ ይበል ቤታችሁ
መ ብ ሩ ክ !!!
بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في الخير !!!
👑ለውዷ እህቴ ለውዱ ወንድሜ🌹
👑 ሙሸሪት & ሙሸራው 🛍
ለውዷ እህቴ👑
ቢስሚላህ ብየ ልጀምርላችሁ
ደስታዬን በግጥም ልተርክላችሁ
አልሀምዱሊላሂ ምስጋና ይድረሰው
ሀራምን ከልክሎ ሀላል ለፈቀደው
ለአለማቱ ጌታ ከአርሽ በላይ ላለው
ባረከሏህ ብዬ በጣም ልባርክልሽ
እጅግ ደስ ብሎኛል ኒካህ በማሰርሽ
ትዳርም መስርተሽ ኢማንሽም ሞላ
ምን ያስደስትሻል ታዳ ከዚህ ሌላ
የኛማ ሙሽራ በጣም ተውባለች
ከጅልባቧ በላይ ኒቃብ ደርባለች
ሙሽሪት አደራ ብዬ የምነግርሽ
ሀቁን ጠብቂለት ለውዱ ባልሽ
በሚያዝሽ ሰአት መርሀባ ብለሽ
ለችግሩ ሁሉ መፍትሄ ሁነሽ
በደስታውም ጊዜ አብረሽ ተደስተሽ
እንድህ ነው ቃልኪዳን እንድህ ነው ጋብቻ
ለውዱ ወንድሜ 🌹
ሙሽራው ልገርህ አድምጥ በጥሞና
ውዷ ባለቤትህ ስጦታህ ነችና
ተንከባክበህ ያዛት
የረሱል አደራ አማናህ ናትና
ሀቋን ጠብቅላት በምትችለው አቅም
እሷም በአቅምህ እንጂ በብዙ አትጠይቅም
ባረከሏህ ለኩም ይድመቅ ትዳራችሁ
በደስታ በፍቅር ትኑሩ ቤታችሁ
በደጋሜ ለውዷ እህቴ ለውዱ ወንድሜ መብሩክ
ደስታችሁ ደስታየ ነው
መብሩክ መብሩክ አልኩኝ ይመር ኒካሀቹ ይመር ትዳራቹ
በሸሪዓው መንገድ ይድመቅ ትዳራቹ
ፍቅር ይስፈን ሁሌ በቤት በኑሮቹ
ሁሉን ቻይ የሆነው የአለማት ጌታ
ሰርጉን መብሩክ ያርገው ለሁሉ አስተማሪ
አላህን ከማመፅ ከጭፈራ እርቆ
ሰርጋቹ በሱና ታየ አሸብርቆ
አላህምዱሊላህ እንኳን ደስ አላቹ
የፍቅር የደስታ ይሁን ትዳራቹ
ለኡማው ጠቃሚ አላህን ፈሪ
ሷሊህ ልጅ ይስጣቹ የአለማቱ ጌታ
ውዷ እህቴ የዛሬዋ ሙሽሪት
ውዱ ወንድሜ የዛሬው ሙሸራ
ይድመቅ ትዳራቹ ከሀላልህ ጋራ
አላህ አይለያቹ ፍቅራቹ ይበርታ
ቤታቹህ ትሙላ ሁልጊዜ በደስታ
አቦ እንዴት ያምራል ሰርግማ በሱና
አላህን ሳያምፁ በረሱል ጎዳና
ጭፈራና ዘፈን ሳይኖር ሀራም ነገር
የአላህ ቃል ሲወራ ሀዲሱ ሲነገር
መቀላቀል ሳይኖር ወንዱ ከሴቱ ጋር
ደምቆ ታየ ሰርጉ በሀላል በቁምጋር ነገር
እንግዲህ ፁሁፌን ቋጨሁት እዚህ
ለውዷ እህቴ ብየ መልካም ትዳር
ለውዱ ወንድሜ ብየ መልካም ትዳር
ቤታችሁ ትሙላ በሙሀባ ፍቅር🛍
በይ ተንከባከቢው ሀቁን ጠብቂለት
በደስታም በሀዘን ከጎኑ ቁሚለት
ከሷሊሆች ሁኝ ለትዳርሽ ብቁ
አላህን በመፍራት ሀቅ ከሚጠብቁ
ለባል ታዛዥ መሆን ኢባዳ ነውና
ፍቅርሽን መገቢው በንፁህ ልቦና
ትልቅ ደረጃ አለው ትዳር በእስልምና
ወሚን አያቲሂ ...... ብሏል ረበና
እናም እህት አለም ኢማንሽ ይሙላና
ትዳርሽን ያዥ ጠበቅ በይና ።
የእህትነት ምክሬን ለወንድሜ
ስማኝ አደራ እህቴን አታስከፋብኝ
በደስታም በሀዘን ከጎኗ ሆነህ
እንድታጫውታት አቅፈህ በክንድህ
ሚስትህ እኮ ላንተ ሁለ ነገርህ ናት
የፍቅርህ ምርኮኛ የተለየች ከእናት
ከምነግርህ በላይ በስፋት ብታውቅም
ሀቋን ጠብቅላት በምትችለው አቅም
ኸይሩኩም ሊአህሊህ ብለዋል ነብዩ
ምርጥ ባል ሁንላት የምጊዜም ልዩ።
🌹ተመኘሁላችሁ🌹
የሁል ጌዜ ደስታ የነፍስን እርካታ
የቀልብ ሰኪና ፍቅር ሳቅ ጨዋታ
መተሳሰብና መቻቻል ውደታ
ደስ በሚል ሂወት ባማረ ፈገግታ
ውደታ አሸብርቆ በጧትም በማታ
በፍቅራችሁ ፅኑ እስከ ዘለቄታ
አላህ ያዋዳችሁ የአለማቱ ጌታ
መልካም ልጅ ይስጣችሁ ለድኑ ጠቃሚ
እንኳን ደሰ አላችሁ በነብዩ ሱና ሆነ ጋብቻችሁ
ተዛዝናችሁ ኑሩ
ሁሌም ተዋዳችሁ
በኢማን አጊጡ
ሞቅ ይበል ቤታችሁ
መ ብ ሩ ክ !!!