ሊቀ ህሩያን መለስ ማዕከሉ በአሁኑ ወቅት ወደ 700 ገደማ የሚጠጉ የአዕምሮ ሕሙማንን ተቀብሎ መጠለያና ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል።
አርቲስት ዳዊት አባተ በበኩሉ፣ ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማንን ለማገዝ እያደረገ የሚገኘውን ጥረት በማድነቅ፣ አሁን ላይ ግን ሕሙማኑን ለመርዳት የሚያስችለው አቅም እያነሰው እንደመጣ ጠቅሷል። የአንድ ሕመምተኛ ቁርስ፣ ምሳ፣ ራት እና መድሃኒትን ጨምሮ አጠቃላይ ዕለታዊ ወጪ 200 ብር መሆኑን አውስቶ “እናንት ደጋግ ኢትዮጵያውያን፣ በምትችሉት አቅም ጌርጌሴኖን እርዱ!” በማለት ጥሪውን አቅርቧል።
እንዲሁም የሕንጻ ግንባታውን በተመለከተ፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ የጠየቀው አርቲስቱ፣ ማንኛውንም የግንባታ ግብዓቶችን ለጌርጌሴኖን መለገስ የሚፈልጉ ወገኖች ወደ ማዕከሉ በመምጣት መለገስ እንደሚችሉ ገልጿል። በተጨማሪም፣ ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ለሚሹ ወገኖች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000649044183፣ አቢሲኒያ ባንክ 1219 ወይም 1998፣ ኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ 1026600059494 እና በቴሌ ብር 500464 መጠቀም “ይቻላል” ሲል አርቲስት ዳዊት ተናግሯል።