አይኤስ የተሰኘው የሽብር ቡድን በሩሲያ በቤተክርስቲያን እና ምኩራብ ላይ በፈፀመው ጥቃት ቢያንስ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል ።
በሩሲያ ሰሜን ካውካሰስ ሪፐብሊክ ዳግስታን ውስጥ በፖሊስ መኮንኖች፣ አብያተ ክርስቲያናት እና ምኩራቦች ላይ በደረሰ ጥቃት የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል።
በጴንጤቆስጤ የሩሲያ ኦርቶዶክስ በዓል ላይ ታጣቂዎች በደርቤንት እና ማካችካላ ከተሞች ላይ ጥቃት አድርሰዋል።
ከሟቾቹ መካከል ቢያንስ 15 የፖሊስ አባላት፣ ቄስ እና የጥበቃ ሰራተኛ ይገኙበታል።
ከአጥቂዎቹ መካከል ስድስቱ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ፖሊስ ሌሎችን እያደነ ይገኛል።
የአጥቂዎቹ ማንነት ባይታወቅም በዳጌስታን ከዚህ ቀደም ተከታታይ ጥቃቶች ሲደርሱ ቆይቷል።
በእሁዱ ጥቃት ሁለት አብያተ ክርስቲያናት እና ሁለት ምኩራቦች ኢላማ ተደርገዋል። የዳግስታን ትልቋ ከተማ በሆነችው በማካችካላ አንድ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቄስ ተገድለዋል።
15 ፖሊሶች በጥቃቱ መገደላቸውን የዳግስታን ሪፐብሊክ መሪ ሰርጌ ሜሊኮቭ ተናግረዋል።
በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተለጠፉት ምስሎች እንዳሳዩት የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ወደ ስፍራው ከመድረሳቸው በፊት ጥቁር ልብስ የለበሱ ሰዎች በፖሊስ ተሽከርካሪ ላይ ሲተኩሱ ያሳያል።