Admas Media - አድማስ ሚዲያ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


ይህ Admas Media -አድማስ ሚዲያ - ኦፈሽአል ቴሌግራም ነው።
የሚወዱትን Admas Media -አድማስ ሚዲያ ማህበራዊ ገፅ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ።
This is Admas Media - አድማስ ሚዲያ Official Telegram Channel
መልዕክት መቀበያ እና ለማንኛውም አይነት ጥያቄ @Admas_media_bot
እንዲሁም ለማስታውቂያ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter








Advertisment ማስታወቂያ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።☕️ Get a free cup of coffee from Telega.io! Inform your subscribers that they can buy ads on your Telegram channel. We'll give you a $2 coffee reward and a +5 catalog rating, as well as the opportunity to receive referral rewards for 2 years from those advertisers who buy placements through your link.

Text of ad post: Enjoy our content? Advertise on this channel and reach a highly engaged audience! 👉🏻

It's easy with Telega.io. As the leading platform for native ads and integrations on Telegram, it provides user-friendly and efficient tools for quick and automated ad launches.


ሰበር መረጃ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከመጪው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እራሳቸውን አገለሉ።

Biden pulls out of the presidential elections.




Advertisment/ማስታውቂያ

በልዩ ቅናሽ ታብሌት‼️

🧨ለትምህርት,ለስራ,ለጌም,ለመዘናኝ እንዲሁም እንደ ስልክ ሚገለገሉበት

🎈እስክሪን መጠን 10"
🎈android :12
🎈Storage: 512 GB
🎈Ram:8 GB
🔋10000 mAh የባትሪ ሀይል (48 hours)
📷 3 camera
👉🏿ሁለት ሲምካርድ የሚቀበል, 3g/4g/5G LTE ኔትወርክ የሚሰራ

🏃‍♂️🏃🏃ውስን ፍሪ ስለሆነ ቀድመው ይውስዱ (Buy now few pieces left)

ይምጡና ይጎብኙን ‼️ ተደስተው ይመለሳሉ‼️

 🏢 አድራሻችን
              ሀዋሳ
ከቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ወደ ሎጊታ በሚወስድው መንገድ ላይ 
ከሲዳማ ክልል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ወይም ከሃዋሳ ህዝብ ላይበራሪ ፌት ለፌት
👉👉ከአሜ ፔንሲዮን በር ለይ
        አዶናይት ኦንላይን ሾፕ🏃‍♂️🏃‍♀️

ስልክ ☎️ 📞📲 09 73 64 57 79
        ☎️ 📞 📲 09 33 06 19 03

💬 ለትእዛዝ, አስተያየትና ጥያቄ ለመፃፍ
@Adonayet2018

ተጨማሪ እቃዎችን ለማየትና ለመሸመት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/Adonayet_high_techhawassa

❌❌ ማሳሰብያ: ሱቃችን ሲመጡ ትክክለኛ የኛ ሱቅ ስም አዶናይ  እና ከአሜ ፔንሲዮን በር ለይ መሆኑን ያረጋግጡ‼️


ኤለን መስክ  ከግድያ ሙከራ ማምለጡን ገለጸ

የቴስላና የኤክስ ኩባንያ  ባለቤት የሆነዉ ቢሊየነሩ  መስክ በሁለት የተለያዩ አጋጣሚዎች ሁለት ሰዎች ሊገድሉኝ ሞክረዋል ብሏል።  ሰዎቹ ቴክሳስ ከሚገኘው ከቴስላ ዋና መስሪያ ቤት በ20 ደቂቃ ርቀት ላይ ከእነ ጦር መሳሪያቸው ተይዘዋ ሲል አሜሪካዊው ቢሊየነር በማህበራዊ ሚዲያው ላይ አጋርቷል። ቢሊየነሩ   ይህንን  የተናገረዉ ዶናልድ ትራምፕ ከግድያ ሙከራ  ከተረፉ በኋላ ነወ፡፡


የቦሊቪያ ፖሊስ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መሪን በቁጥጥር ስር አዋለ

በዋና ከተማዋ ላ ፓዝ የሚገኘው ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግስት በወታደሮች ከተወረረ ከሰዓታት በኋላ የቦሊቪያ ፖሊስ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን መሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ይፋ አድርጓል።

የታጠቁ ወታደሮች ቁልፍ የመንግስት ህንፃዎች በሚገኙበት ሙሪሎ አደባባይ ላይ ቆመው ታይተዋል። የአማፂው ወታደራዊ መሪ ጄኔራል ሁዋን ሆሴ ዙኒጋ “ዲሞክራሲን እንደገና ማዋቀር” እንደሚፈልጉ እና ምንም እንኳን ፕሬዝዳንት ሉዊስ አርሴን ቢያከብሩ፣ የመንግስት ለውጥ እንደሚመጣ የተናገሩ ሲሆን አሁን በእስር ላይ ይገኛሉ።

ፕሬዝዳንት አርሴ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን አውግዘዋል፣ ህዝቡም "እንዲደራጅ ጥሪ አቅርበዋል። ከፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግስት ውስጥ ለሀገሪቱ ህዝብ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልእክት "የቦሊቪያውያንን ህይወት ለማጥፋት የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት እንደገና መፍቀድ አንችልም" ብለዋል።

አርሴ አዲስ ወታደራዊ አዛዦችን እየሾሙ መሆኑን አስታውቀው ጄኔራል ዙኒጋ የቦሊቪያ የቀድሞ መሪ ኢቮ ሞራሌስን በግልፅ በመተቸት ከስልጣናቸው መባረራቸውን አረጋግጧል። ሞራሌስ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን በማውገዝ በጄኔራል ዙኒጋ እና “በግብረ አበሮቻቸው” ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሰረትባቸው አሳስበዋል።

ሞራሌስ ደጋፊዎቻቸው በተለይም በሀገሪቱ የኮክ አብቃይ ንቅናቄ ውስጥ የሚገኙት ገበሬዎች የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራው እንዲያበቃ ወደ አደባባይ በመውጣት እንዲጠይቁ ጥሪ አቅርበዋል። ጄኔራል ዙኒጋ በወታደሮች ከተወሰዱ በኋላ ከሙሪሎ አደባባይ በመሆን “ይህችን የትውልድ አገር ወደ ነበረችበት እንመለሳለን። "ሀገርን ያፈረሱ ወንበዴዎችና ልሂቃን ናቸው ሀገርን ተቆጣጠረው ያሉትም ብለዋል።


በጎንደር እገታ❗️

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ተሽከርካሪን የሚይዙ በሹፊሮች እገታ፤ እንዲሁም ግድያ እየደረሰባቸዉ መሆኑ በተደጋጋሚ እየተዘገበ መሆኑ ይታወቃል። በአማራ ክልል ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች የሚገኙ ሹፌሮች በየመንገዱ እየታገቱ ከአቅማቸው በላይ ገንዘብ እንደሚጠየቁ፣ እንደሚደበደቡና እንደሚገደሉ እማኞችን ጠቅሷ ዶቼቬሌ ዘግቧል።


አይኤስ የተሰኘው የሽብር ቡድን  በሩሲያ በቤተክርስቲያን እና ምኩራብ ላይ በፈፀመው ጥቃት ቢያንስ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል

በሩሲያ ሰሜን ካውካሰስ ሪፐብሊክ ዳግስታን ውስጥ በፖሊስ መኮንኖች፣ አብያተ ክርስቲያናት እና ምኩራቦች ላይ በደረሰ ጥቃት የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል።

በጴንጤቆስጤ የሩሲያ ኦርቶዶክስ በዓል ላይ ታጣቂዎች በደርቤንት እና ማካችካላ ከተሞች ላይ ጥቃት አድርሰዋል።

ከሟቾቹ መካከል ቢያንስ 15 የፖሊስ አባላት፣ ቄስ እና የጥበቃ ሰራተኛ ይገኙበታል።

ከአጥቂዎቹ መካከል ስድስቱ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ፖሊስ ሌሎችን እያደነ ይገኛል።

የአጥቂዎቹ ማንነት ባይታወቅም በዳጌስታን ከዚህ ቀደም ተከታታይ ጥቃቶች ሲደርሱ ቆይቷል።

በእሁዱ ጥቃት ሁለት አብያተ ክርስቲያናት እና ሁለት ምኩራቦች ኢላማ ተደርገዋል። የዳግስታን ትልቋ ከተማ በሆነችው በማካችካላ አንድ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቄስ ተገድለዋል።

15 ፖሊሶች በጥቃቱ መገደላቸውን የዳግስታን ሪፐብሊክ መሪ ሰርጌ ሜሊኮቭ ተናግረዋል።

በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተለጠፉት ምስሎች እንዳሳዩት የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች  ወደ ስፍራው ከመድረሳቸው በፊት ጥቁር ልብስ የለበሱ ሰዎች በፖሊስ ተሽከርካሪ ላይ ሲተኩሱ ያሳያል።


የኢትዮጵያ አየር መንገደ በዓለም ላይ ምርጡ የአየር መንገድ ነው - አምባሳደር ቲቦር ናዥ 

የኢትዮጵያ አየር መንገደ በዓለም ላይ ምርጡ የአየር መንገድ ነው ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ አምባሳደር ቲቦር ናዥ ገለፁ፡፡

አምባሳደር ቲቦር ናዥ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ በአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲው ላስመረቃቸው 800 ተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

አምባሳደሩ በመልእክታቸውም፤ የኢትዮጵያ አየር መንገደን ብዙ ጊዜ መጎብኘታቸውን ጠቅሰው፤ በነበራቸው ተሞክሮም የአየር መንገዱ የሙያ ልህቀት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ለእኔ የኢትዮጵያ አየር መንገደ በዓለም ላይ ምርጡ የአየር መንገድ ነው ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡


ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክክ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ ጀመረ

የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው በዚህ መመሪያ ዉስጥ የእህልና ጥሬጥሬ ፣ የግብርና ምርቶች እና የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች ይገኙበታል ።

በዚህ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ  እቃዎችን ለመወሰን በወጣው  መመሪያ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ማድረግ የወጪ ጫናውን በማርገብ ረገድ ጠቀሜታ አለዉ ተብሏል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ከተደረጉት መካከል ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ ፣ ማዳበሪያ ፣ የእንስሳት መድሃኒት እንዲሁም በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርብ የካፒታል ዕቃዎች ተካተዉበታል።


ተመድ ሊባኖስን አስጠነቀቀ❗️

ሊባኖስ ሌላኛዋ ጋዛ እንዳትሆን የተመድ ዋና ጸኃፊ አስጠነቀቁ። የተባበሩት መንግስት ድርጅት(ተመድ) ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በእስራኤል እና ሄዝቦላ ያለው ውጥት መካረር እንዳስጨነቃቸው በትናንትናው እለት ተናግረዋል። ሊባኖስ ሌላኛዋ ጋዛ እንዳትሆን የተመድ ዋና ጸኃፊ አስጠነቀቁ። የተባበሩት መንግስት ድርጅት(ተመድ) ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በእስራኤል እና ሄዝቦላ ያለው ውጥት መካረር እንዳስጨነቃቸው በትናንትናው እለት ተናግረዋል። "አንድ ችኩል እርምጃ ወይም የተሳሳተ ስሌት ከምናስበው በላይ ድንበር ተሻጋሪ አስከፊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል" ሲሉ ጉተሬዝ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። "ግልጽ እንሁን። የቀጣናው ህዝብ እና የዓለም ህዝብ ሌባኖስ ሌላኛዋ ጋዛ እንድትሆን አይፈልግም።" በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላ ባለፈው ጥር ወር የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለሀማሰ አጋርነት ለማሳየት ወደ እስራኤል በርካታ ሚሳይሎችን አስወንጭፏል፤ በዚህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ከቤታቸው ተፈናቅለዋል።


"መምህራኑ በዶርም ለመኖር ተገደዋል"ከመቀሌ የተሰማ

በቤት ኪራይ ውድነት የተቸገሩ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፤ በተማሪዎች ዶርም “በጊዜያዊነት” እየኖሩ ነው ተባለ።

ትግራይ ክልል በሚገኘው መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩ የተወሰኑ መምህራን “ቤት ተከራይቶ መኖር እንደከበዳቸው” ለተቋሙ ማመልከታቸውን ተከትሎ፤ በተማሪዎች ማደሪያ ዶርም “በጊዜያዊነት” እንዲቆዩ ተፈቅዶላቸው እየኖሩ መሆኑን ገለጹ።

የዩኒቨርስቲው መምህራን በክልሉ በነበረው ጦርነት ሳቢያ የ17 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መሆኑ፤ በአስር ሺህዎች የሚቆጠር ውዝፍ የቤት ኪራይ እንዲከማችባችው አድርጓል። 

የዩኒቨርሲቲው መምህራን “የቤት ኪራይ መክፈል አቅቶናል” የሚሉ ማመልከቻዎችን ለተቋሙ ማስገባት የጀመሩት ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ቢሆንም፤ ካለፈው ሶስት ወር ወዲህ ግን በርካታ መምህራን ተመሳሳይ ጥያቄዎች ለተቋሙ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ቢሮ ማቅረባቸው ተነግሯል።

መምህራኑ ለዩኒቨርሲቲው ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተገደዱት፤ በጦርነት ወቅት ሳይከፍሉ የቀሩትን “ውዝፍ የቤት ኪራይ” አሁን እንዲያመጡ እየተጠየቁ በመሆኑ እና በክልሉ ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት ነው ብለዋል።


በትግራይ ክልል ወረርሽኝ በሆነ መልኩ በተከሰተ ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፍ በሽታ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ

በደቡብ ምስራቅ ትግራይ በተለይም ህንጣሎ ዋጀራት በተሰኘዉ ወረዳ ከእንስሳት ወደ ሰዉ በሚተላለፍ በሽታ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴንሽን እና የጤና ማስተዋወቅ ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሚካኤል ሃጎስ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በሽታዉ ጦርነቱ ካስከተለዉ ቀዉስ መካከል አንዱ ነዉ ብለዋል። በበሽታዉ ከተያዘ እንሰሳ ጋር በሚኖር ንክኪ እና ስጋዉን በመብላት በሚተላለፈዉ በሽታው በወረዳዉ በወረርሽኝ መልክ መከሰቱን ተናግረዋል።

በዚህ በሽታ ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ ሰዎች መጠቃታቸዉን የተናገሩት አቶ ሚካኤል ፤ እስከሞት ሊያደርስ እንደሚችልም ገልጸዋል። በዚህ በሽታ የተነሳ የአራት ሰዎች ህይወት ሲቀጠፍ በርካቶች በአዲ ጉደም ሆስፒታል እንዲሁም ከፍ ባለ አስጊ ሁኔታ ዉስጥ ያሉት ደግሞ በዓይደር ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ክትትል ላይ ናቸዉ ብለዉናል።

በሽታዉ በሁሉም የትግራይ ዞኖች ይታይ ነበር ያሉት አቶ ሚካኤል አሁን ግን በወረርሽኝ መልክ በደቡብ ምስራቅ ትግራይ አንድ ወረዳ ላይ መከሰቱን አስረድተዋል።

አንትራክስ የተሰሰነዉ በሽታ በባክቴሪያ የሚመጣ ሲሆን የተጠቃዉ ሰዉ ፤ ከእንስሳት ጋር በሚኖረዉ ንክኪ የቆዳ ላይ ህመም ፣ በበሽታዉ የተጠቃ እና ያልተመረመረ ከብትን የተመገቡ ሰዎች ደግሞ ከአንጀት ጋር የተታያዘ ከፍተኛ ህመምን እንዲሁም የእንሰሳዉ ቆዳ በፋብሪካዎች ከተቀነባበረ ደግሞ በሳንባ ላይ ከፍተኛ ህመምን የሚያስከትል እና በ 24 ሰዓታት ዉስጥ ሊገድል የሚችል ነዉ ብለዉናል።

በአሁኑ ወቅትም በትግራይ ከእንስሳቱ ጋር በሚኖር ንክኪ በቆዳ ላይ የሚከሰተዉ የበሽታ አይነት በስፋት መታየቱን ጠቅሰዉ ያልተመረመረ ስጋን የተመገቡ ሰዎችም በበሽታዉ መጠቃታቸዉን አክለዋል። በሽታዉ ከሰዉ ወደሰዉ አይተላለፍም የተባለ ሲሆን ከእንስሳት ጋር የሚኖር ንክኪን ግን መገደብ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ከ 20 አመታት በፊትም በሽታዉ ተከስቶ ነበር የተባለ ሲሆን በወቅቱ በቁጥጥር ስር የነበረ ቢሆንም ከጦርነቱ በኋላ በተፈጠረዉ የጤና አገልግሎት ስርዓት መጓደል የተከሰተ መሆኑን አመላክተዋል።

በበሽታዉ የተያዙ ሰዎች በቆዳ ላይ የማሳከክ እና አብጦ የመፈንዳት እንዲሁም የእንስሳት ስጋን ተመግበዉ የታመሙትን ሰዎች ደግሞ እንደማንኛዉም የሆድ ህመም የቁርጠት እና የህመም ምልክት ያለዉ ሲሆን በአንጀት ላይ ግን ቁስለትን የሚያስከትል መሆኑንም ተናግረዋል።

በሽታው በቶሎ የህክምና ክትትል ከተደረገለት የሚድን እንደሆነም በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴንሽን እና የጤና ማስተዋወቅ ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሚካኤል ሃጎስ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።


የ4 አመቱ ህፃን በንብ መንጋ ተነድፎ ህይወቱ አለፈ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሸካ ዞን የማሻ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ፍቅረአለም በቀለ ለክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን በስልክ እንደገለፁት ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት በወረዳዉ ኡዋ ቀበሌ ልዩ ስፍራ ይጎ ቁጥር አንድ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ የአራት አመቱ ህፃን በንብ መንጋ ተነድፎ ህይወቱ ማለፋን ተናግረዋል።

እንደ ፖሊስ አዛዡ ገለፃ በዕለቱ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ከባድ ዝናብ ምክንያት በመኖሪያ ቤት አከባቢ ዘመናዊ የንብ እርባታ ቀፎ በንፋስ በመዉደቁ ምክንያት ንቦቹ ከቀፎዉ ዉጥተዉ በመጫወት ላይ የነበሩ ሶስት ህፃናትን ለመዉረር ሲሉ ሁለቱ ሮጠዉ ሲያመልጡ የአራት አመቱ ህፃን ማምለጥ ባለመቻሉ በንቦች መንጋ ተነድፎ ህይወቱ እንደላፈ አስረድተዋል።

በመጨረሻም መሰል የንብ መንጋ አደጋ በሌሎች አከባቢዎች እንዳይከሰት ንብ የማነብ ስራ የሚያከናዉኑ ግለሰቦች ዘመናዊ ቀፎዎችን በንፋስ እንዳይወድቁ እና ከለላ አጥር ማበጀት እንደሚኖርባቸዉ ረዳት ኢንስፔክተር ፍቅርአለም በቀለ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽ


በአየር ትርዒት የተጋጩት ጄቶች❗️

በፖርቹጋል የአየር ትርዒት ላይ በተፈጠረ ግጭት የስፔን ዜግነት ያለው ፓይለት ህይወቱ ማለፉን የፖርቹጋል አየር ሀይል አስታውቋል፡፡ እንደ አየር ሀይሉ መረጃ፤ ከፖርቹጋል መዲና ሊዝበን ከተማ በ178 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምተገኘው የቤጃ ከተማ ላይ እየተካሄደ በነበረው የአየር ትርዒት ላይ አውሮፕላኖች ተጋጭተው አደጋ ተከስቷል፡ በግጭቱ አንደኛው አውሮፕላን ከቤጃ አየር ማረፊያ ክልል ውጭ ሲከሰከስ ሌላኛው አውሮፕላን ደግሞ በአየር ማረፊያው አቅራቢያ መከስከሱ ተገልጿል፡፡በአደጋው አንድ ፓይለት ህይወቱ ሲያልፍ ሌላኛው ፖርቹጋላዊ ፓይለት ክፉኛ ተጎድቶ ወደ ቤጃ ሆስፒታል መግባቱ ነው የተገለፀው፡፡ የፖርቹጋል አየር ሀይል በተፈጠረው ክስተት ማዘኑን ገልፆ በአደጋው ሕይዎቱን ላጣው አብራሪ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡


ቻይና መንኮራኩሯ ማንም ሞክሮ በማያውቀው የጨረቃ ክፍል ማረፉን አስታወቀች

ቻይና ቻንግ 6 የተበለው መንኮራኩሯ እሑድ ጥዋት ማንም ሞክሮ በማያውቀው በደቡብ ዋልታ-አይትከን ማረፉን የሀገሪቱ ብሔራዊ የጠፈር አስተዳደር (ሲኤንኤ) አስታውቋል።

የዛሬ ወር ገደማ ጉዞ የጀመረው መንኮራኩር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ውድ ድንጋይ እና አፈርን ለመሰብሰብ ያለመ ሲሆን በደቡብ ዋልታ ላይ ካለው ግዙፍ ጉድጓድ ውስጥ የተወሰኑትን የጨረቃን ጥንታዊ አለቶች ማውጣት እንደሚችል ተነግሯል።

መንኮራኮሩ ምቹ የሆነ ቦታ ለማረፍ በሚያደርገው ጥረት መሰናክሎችን በመለየት መንቀሳቀስ የሚያስችለው ቴክኖሎጂ እና እንደጨለማው ሁኔታ የሚቀያየር ብርሃን የተገጠመለት መሆኑን ተዘግቧል።
Credit: Xinhua


ልዩ መረጃ‼️

እስክንድር ነጋ ከመንግስት ሰዎች የሰላም ድርድር ሂደት መጀመሩ ታውቋል

  እስክንድር ነጋ የፋኖ ታጣቂዎችን ወክሎ ከመንግስት ድርድር መጀመሩ ተገልጿል። በ3ኛ ወገን አመቻችነት እስክንድር ነጋ ከመንግስት ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ የድርድር ሂደት መጀመሩ ተጠቁሟል።

መንግስት ከእስክንድር ጋር እያደረገ ያለው ድርድር የሚሳከ ከሆነ ከእስክንድር ቡድን ጋር ከሸዋ የሻለቃ መከታው ቡድን፣ ከወሎ የምሬ ወዳጆ እና የኮ/ል ፈንታሁን ቡድኖች፣ ከጎጃም የማስረሻ ሰጤ እና የማንችሎት ቡድኖች፤ ከጎንደር በሻለቃ ሀብተ ወልድ የሚመራ ቡድን ወደ በድርድርሩ  እንዲሳቱፉ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

ከሰላም ውጪ ሌላ አማራጭ መንገድ የለም! ሰላም ለኢትዮጵያ

20 last posts shown.