ለፈተና ለመዘጋጀት የሚጠቅሙ 9 ነጥቦች
ውድ እና የተከበራችሁ የት/ቤቶቻችን ወላጆች፡-
ከሰኞ ህዳር 16 ቀን 2017 ጀምሮ ትምህርት ዘመኑ የመጀመሪያው መንፈቀ-ዓመት አጋማሽ ፈተና መሰጠት ይጀምራል።ታዲያ በዚህ ወቀት ለተማሪዎች የፈተና ዝግጅት ጠቃሚ መሆናቸውን በባለሙያዎች የሚመከሩ 9 ጠቃሚ ነጥቦችን ልንነገራችሁ ወደናል፤መልካም ንባብ፡፡
1. ቁርስና ጠቃሚ ምግቦች
ሰውነታችን በአግባቡ ሥራውን እንዲሰራ ኃይል ያስፈልገዋል፤ አንጎላችን ደግሞ ትኩረት እንዲኖረውና የማስተዋል አቅማችን እንዲጨምር በቂ የሆነና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት ይፈልጋል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቁርሳቸውን ተመግበው ወደፈተና የሚገቡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ። የተመጣጠነ ምግብ ተመግበው ለፈተና የሚቀርቡት ደግሞ የበለጠ የማስታወስና የማስተዋል አቅም ይኖራቸዋል።
ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ፈተና ያለባቸው ተማሪዎች እንደ የገብስ ገንፎ፣ ዳቦ፣ ሩዝና ድንች ያሉ በካርቦሃይድሬት የበለጸጉ ምግቦችን በቁርስ ሰዓት ተመግበው ቢወጡ ይመከራል።
እርጎ፣ እንቁላል፣ አሳ፣ ጎመን፣ ቲማቲምና አቮካዶ ዓይነት ምግቦችም እጅጉን ጠቃሚ ናቸው።
2. በጠዋት ወደ ጥናት መግባት
ሁሌም ቢሆን ነገሮችን አስቀድሞ መጀመርን የመሰለ ነገር የለም። ለፈተናም ቢሆን ጥናት በጠዋት ተነስቶ መጀመር በፈተና ወቅት የተረጋጋ መንፈስ እንዲኖረን ይረዳል።
ጠዋት ላይ ጭንቅላታችን እረፍት አድርጎ በአዲስ መንፈስ ሁሉንም ነገር ስለሚጀምር፤ በዚህ ሰዓት ማጥናት ውጤታማ ያደርጋል። በተለይ ደግሞ የክለሳ ጥናቶችን ለከሰዓት ማሸጋገር ተገቢ አይደለም።
3. ከፋፍሎ ማጥናት
የክለሳ ጥናትን ከፋፍሎ ማካሄድን የመሰለ ነገር የለም። አንድ የትምህርት ዓይነት ላይ 10 ሰዓት ሙሉ ከማሳለፍ በየቀኑ አንድ ሰዓት በማጥናት በ10 ቀን መጨረስ ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል።
ያጠናነውን ነገር ለማስታወስና በቀላሉ ለመሸምደድ ጭንቅላታችን ጊዜ ይፈልጋል። ከፋፍሎ ማጥናት ደግሞ ለዚህ ፍቱን መድሃኒት ነው። ከፋፍሎ ማጥናት እጅግ ውጤታማው መንገድ እንደሆነም በመላው ዓለም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች ያለመክታሉ።
4. ራሳችሁን ቶሎ ቶሎ ፈትኑ
የሥነ አዕምሮ ጥናት ባለሙያዎች እንደሚሉት የማስታወስ ችሎታን ለማዳበርና በራስ መተማመናችንን ለመጨመር ራስን መፈተን ውጤታማ ያደርጋል።
ከዚህ በተጨማሪ እየተዘጋጀንበት ያለነውን ጉዳይ በደንብ እንድናውቀው ከማድረጉ በተጨማሪ የረሳናቸው አልያም የዘለልናቸው ርዕሶችን ለመለየት ይረዳናል።
5. መምህር መሆን
ከባዱን የክለሳና ራሳችሁን የመፈተን ሥራውን ካከናወናችሁ በኋላ ጓደኞቻችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ በጭንቅላታችሁ የሚመጣውን ነገር በሙሉ ንገሯቸው። ራሳችሁን በመምህር ቦታ አድርጋችሁ እውቀታችሁን ለማካፈል ሞክሩ።
ምን ያህል እንደምታስታውሱ ለማወቅ ከመርዳቱ በተጨማሪ ጓደኞቻችሁንም ትጠቅሟቸዋላችሁ።
6. ከተንቀሳቃሽ ስልኮች መራቅ
ስልኮች በጣም ብዙ ጥቅም አላቸው። ነገር ግን በጥናት ወቅት ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ነው የሚያመዝነው። በተለይ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ።
ብዙ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ብዙ ጊዜያቸውን ስልካቸው ላይ የሚያሳልፉ ተማሪዎች የትምህርት ውጤታቸው ሁሌም ቢሆን ዝቅ ያለ ነው።
7. ቋሚ እረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴ
ውጤታማ የክለሳ ጥናት ማለት እረፍት አልባ ጥናት ማለት አይደለም። በጥናታችን መሀል መሀል ላይ ጥሩ አየር ለማግኘትና ሰውነታችንን ለማፍታታት ወጣ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ የማስታወስ ችሎታችንን በደንብ ከፍ ያደርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን እና ጭንቅላታችን በእጅጉ የተሳሰሩ በመሆናቸው እንቅስቃሴ ስናደርግ የደም ዝውውራችን ይስተካከላል፤ ይህ ደግሞ በቂ ኦክስጅን ወደ ጭንቅላታችን እንዲሄድ ይረዳል።
አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ጭንቀትን መከላከልና በራስ መተማመንን መጨመር ከነዚህ መካከል ይጠቀሳሉ።
8. እንቅልፍ
ከፈተና በፊት ያለችውን ምሽት ጥሩ እንቅልፍ አግኝቶ ማሳለፍ ተገቢ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ነገር ግን ጥሩ እንቅልፍ ፈተናው ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን ከሳምንታት በፊት ገና ዋናው ጥናት ሲደረግና ክለሳ በሚደረግበት ወቅትም እጅግ ወሳኝ ነው።
በጠዋት ተነስቶ ውጤታማ የክለሳ ጥናት ካደረጉ በኋላ በጊዜ ተኝቶ ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ሰውነታችንና ጭንቅላታችን በደንብ ተግባብተው እንዲሰሩ ይረዳቸዋል። ሌሊቱን በሙሉ ለማጥናት ሙከራ አታድርጉ ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። ምክንያቱም ራሳችን ላይ ጫና እያሳደርን ስለሆነ።
9. መረጋጋትና በጎ በጎውን ማሰብ
ተማሪዎች እስካሁን የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ተግባራዊ ካደረጉ ምንም የሚያሳስባቸው ነገር ሊኖር አይገባም። ዘና ብለው ወደ ፈተና መግባት ብቻ ነው የሚቀራቸው፡፡ ምናልባት ጥሩ ያልሆነ አጋጣሚ ቢገጥማቸው እንኳን እሱን ረስተው ለቀጣዩ በጥሩ መንፈስ ለመዘጋጀት መሞከር ነው ፡፡
ምንጭ፡BBC NEWS አማርኛ
በመጠኑ ተስተካክሎ የተወሰደ
ውድ ወላጆቻችን፡-
በእያንዳንዱ የፈተና ጊዜ ልጆቻችሁን ማገዝ እና ማበራታታት እንዲሁም ሞራል መስጠት አትርሱ።
ውድ ተማሪዎቻችን ፡-
መልካም ፈተና!!!