ለፈተና የሚጠቅሙ ምክሮች
ውድና የተከበራችሁ የት/ቤቶቻቸን ወላጆች/አሳዳጊዎች
የትምህርት ዘመኑ የመጀመሪያ መንፈቀ-ዓመት የትምህርት መርኃግብር ተጠናቆ የ2017 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ መንፈቀ-ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ሐሙስ፣ ጥር 15/2017 መውሰድ ይጀምራሉ፡፡
እኛም ለዛሬው ሳምንታዊ መልዕክታችን ለፈተና የሚጠቅሙ አንዳንድ ጠቃሚ ነጥቦች ማስታወስ እንዲሆን መርጠናል፡፡
መረጃውን ከብርቲሽ ካውንስል ያገኘነው ሲሆን በመጠኑ አሻሽለን እንደሚከተለው አቅርበንላችኃል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ፈተና በጣም የተረጋጉ በሚባሉ ተማሪዎችም ላይ ሳይቀር ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል። ይሁንና የተወሰነ ዝግጅት በማድረግና የታሰበበት ፕሮግራም አውጥቶ ትምህርቱን በመከለስ ተማሪዎች የሚገባቸውን ውጤት ማግኘት ይችላሉ።
የፈተናው ቀን ከመድረሱ በፊትተማሪዎች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፦
ተማሪዎች አሁን ክለሳ የሚያደርጉበትን ፕሮግራም ስለማውጣት በቁም ነገር ማሰብ መጀመር ይኖርባቸዋል።
የሚከተሉትን ነገሮች ያድርጉ፦
➡️ ፈተናውን በተመለከተ አንዳንድ መረጃዎች ለማግኘት ይሞክሩ (ለምሳሌ ያህል ጥያቄዎቹ ምርጫ ናቸው ወይስ በተጻፉ ነገሮች ላይ የተመሠረቱ?)
➡️ክለሣ የሚያደርጉበትን ፕሮግራም ያዘጋጁ።
ለክለሣ የሚጠቅሙ አንዳንድ ሐሳቦች፦
ተማሪዎች የተማሩትን የሚከልሱበት ፕሮግራም ሲያወጡ ከቀኑ ውስጥ ይበልጥ ውጤታማ የሚሆኑበትን ጊዜ ይምረጡ። ለምሳሌ ያህል ጠዋት ላይ ቀለል የሚላቸውና ነቃ የሚሉ ከሆነ ሰፊ ጊዜ መድበው ከማጥናት ወደኋላ አይበሉ። ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ለማድረግም ጥረት ያድርጉ፦
➡️በአንድ የትምህርት ዓይነት ብዙ ነጥብ ለሚይዙ የፈተና ዓይነቶች ቅድሚያ ይስጡ፣
➡️ አእምሯቸውን ለማደስ አዘውትረው የተወሰነ እረፍት ያድርጉ፣
➡️ መጽሐፎችን በድምፅ የተቀዱ መመሪያዎችንና ለማጥናት የሚረዱ የተለያዩ ዝግጅቶችን ተጠቅመው ትምህርቱን ይከልሱ፣
➡️ ሲያጠኑ በያዙት ማስታወሻ ላይ ቁልፍ ነጥቦችን ያስምሩባቸው፣
➡️ ከእያንዳንዱ ርዕስ ጋር በተያያዘ የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ የሆነ ሰው ጥያቄዎች እንዲጠይቃቸው ያድርጉ፣
➡️ የጥያቄዎቹን ዓይነትና የሚመደበውን ሰዓት በተመለከተ ግንዛቤ ማግኘት እንዲችሉ የድሮ ፈተናዎችን ይሥሩ፣
➡️ ከቤተሰብ ጋር ዘና የሚሉበት ጊዜ ይመድቡ።
ለፈተና ቀን የሚጠቅሙ ሐሳቦች
እንግዲህ ተማሪዎች ጥናታቸውንና ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው ለቁርጥ ቀን ተዘጋጅተዋል። የመረበሽ ስሜት ቢሰማቸው ግራ እንዳይጋቡ፤ ይሄ ያለ ነገር እንደሆነ ሊረዱት ይገባል።ዘና ለማለትና በተቻለ መጠን ጥሩ ውጤት ለማምጣት ተማሪዎች የሚከተሉትን ጥቂት ተጨማሪ ምክሮች ተግባራዊ ያድርጉ፦
➡️ ለመረጋጋት ይሞክሩ እንዲሁም ደጋግመው በደንብ ይተንፍሱ፣
➡️ ፈተናውን መሥራት ከመጀመር በፊት የጥያቄ ወረቀቱን ከዳር እስከ ዳር ያንብቡ፣
➡️ የተመደበውን ጊዜ ይከፋፍሉ፣
ከባድ ጥያቄ ሲያጋጥም ወደሚቀጥለው ይለፉ፣
➡️ ጥያቄዎቹን በጥሞና ያንብቡ፣ ለእያንዳንዱ ጥያቄ ትክክለኛ መልስ መስጠታቸውን እርግጠኛ ይሁኑ፣
በተለይ ፈተናውን በጊዜ ሠርተው ከጨረሱ የጻፏቸውን መልሶች ተመልሰው ይመልከቱ።
በመጨረሻም ወላጆች ልጆቻችሁ የሚያደርጉትን የክለሳና የፈተና ዝግጅት ከላይ የቀረቡትን እና ሌሎችን ጠቃሚ ነጥቦች በማጋራት እና በመምከር ከሌላው ጊዜ በተሻለ ማገዝ እና ማበረታታት ተገቢ መሆኑን በድጋሚ በማስታወስ የዛሬውን ሳምንታዊ መልዕክት እናጠናቅቃለን፡፡