በጎንደር ከተማ የ9 አመት ህፃን ልጅን አግተው በጎርፍ በማስወሰድ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሉ ተከሳሾች እስራት ተቀጡ።
ነሀሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 አካባቢ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ቀጠና 03 ሽዋ በር አካባቢ ከአቶ ደርበው ታፈረው ግቢ ዶርም ተከራይተው እያለ ወይዘሮ አበባ ፈለቀ የተባለችው ግለሰብ ህፃን ኪብሮን ደርበውን ከግቢ ነይ ብር ልቀበል አብረን እንሂድ በማለት ወደ ቀሃ ወንዝ አቅጣጫ ይዛት በመሄድ ቀሃ ወንዝ አካባቢ ካለ ዋርካ ዛፍ አካባቢ ስትደርስ ባለቤቷ ለሆነው ሙሉጌታ አታሎ ሲሳይ በመስጠት ትመለሳለች።
ሙሉጌታ አታሎ የተባለው ግለሰብም ህፃኗን እንዳትጮህ አፏን በፎጣ በማፈን በመውሰድ ያዛቸው ውብስራ ከተባለ ተባባሪ ግለሰብ ጋር በመሆን ከምሽቱ 1፡30 ሰአት አካባቢ ዝናብ ሲመጣ ህፃኗን ይዘው ወደ ቃሃ ወንዝ አዲሱ ድልድይ በመሄድ ህፃን ኪብሮን ደርበውን ከሙላት ጎርፍ ወርውረው በመጣል ጎርፍ እንዲወስዳት አድርገዋል።
ግለሰቦቹም ህፃኗ በህይወት እንዳለች በማስመሰል ከቤተሰቦቿ 1000,000(አንድ ሚሊዮን ብር)በመጠየቅ ድርድር ጀመሩ።
ግለሰቦቹም ያዘኑና ስለ ጉዳዩ የማያውቁ በመምሰል ከህፃኗ ቤተሰቦች ጋር በመሆን ከህብረተሰቡ ህፃኗን ማስለቀቂያ ብር ሲለምኑ ውለው 800,000(ስምንት መቶ ሽህ ብር) መሰብሰቡን ካረጋገጡ በኋላ ስልክ በመደወል በ800,000 ብር ከወላጆች ጋር ድርድር ይጀምራሉ።
የሟች አባትም የልጄን ድምፅ ካለሳማችሁን ብሩን አልከፍልም በማለቱ እና ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ውለው ህፃን ልጅ በመጥለፍ እና በመግደል ወንጀል ተከሰው የፍርድ ሂደቱ ሲጠበቅ ቆይቷል፡፡
የጎንደር ከተማ ፖሊስም ከአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መርማሪ አካላት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ምርመራ በማስረጃ በማስደገፍ ለሚመለከተው የፍትህ አካል መዝገቡን ይልካል።
በመሆኑም መዝገቡ የደረሰው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 10 ቀን 2017 ለህብረተሰቡዓ.ም በዋለው ችሎት ወ/ሮ አበባ ዘለቀ አያሌውን የ21 ዓመት ፅኑ እስራት ሲወስንባት ዳጊ ደሳለኝ ሲሳይእና ያዛቸው ውብስራ ሃይሌ የተባሉ ወንጀለኞችን የእድሜ ልክ እስራት ቅጣት እንድቀጡ ወስኖባቸዋል።