የብርሸለቆ ማሠልጠኛ ማዕከልን ለማወክ የሞከረው ፅንፈኛ ቡድን ተደምስሷል።
የአማራ ፖሊስ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም
ባሳለፍነው አርብ ህዳር 27/2017 ዓ.ም የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤትን ለማወክ አስቦ የተንቀሳቀሰው የፅንፈኛ ቡድን መደምሰሱን እና ቀሪው ትጥቁን እያንጠባጠበ የትም መግባቱን የማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ኮሎኔል መኮነን መንግስቴ አሥታውቀዋል።
በአምስት አቅጣጫዎች ማለትም በጉልም፣ ክሊኒክ፣ ሰንሰል፣ ቀበሮ ሜዳና ቁጭ በሚባሉ መንደሮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱን ለማወክ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ከህብረተሰቡ በርካታ መረጃዎች ቀድመው እንደደረሷቸው ኮሎኔል መኮነን መንግስቴ ተናግረዋል።
ከህብረተሰቡ የደረሰው መረጃ ከቀድሞው ለየት ያለ በመሆኑ በአጭር ሰዓት ቅድመ ዝግጅት ግልፅ ኦሬንቴሽን በመሥጠት የማሠልጠኛው የሠራዊት አባላት ከማሠልጠኛው ውጪ ቦታ በመያዝና ወታደራዊ ጥበብ በመጠቀም ቆሞ መዋጋት በማይችለው ፅንፈኛ ቡድን ላይ በመጣባቸው አቅጣጫዎች ሁሉ አሥፈላጊውን እርምጃ መውሰድ መቻሉን ገልፀዋል። በማሠልጠኛው የሠራዊት አባላት ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን በመጠቆም።
በፅንፈኛው ላይ በተወሰደ እርምጃም 22 ፅንፈኛ ሲደመሰስ ጥቂት የማይባል ቁጥር ያለው ቁሥለኛ እንደሆነም አዛዡ ገልፀዋል። የአካባቢው ህብረተሰብ ቀድሞ ለማሠልጠኛ ማዕከሉ መረጃ በማድረሱና የሠላም ተባባሪ በመሆኑ ምስጋና ያቀረቡት ኮሎኔል መኮነን መንግስቴ በቀጣይም ከህብረተሰቡ ጋር ያለው መልካም ግንኙነት ይበልጥ እንደሚጠናከር ተናግረዋል።
የብርሸለቆ ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት በቀጣይ የሀገራቸውን ሠላም የሚያረጋግጡ የምልምል ወታደሮችን የሥልጠና ማሥጀመሪያ መርሃ ግብር አከናውኗል።
የማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ አዛዥ ኮሎኔል መኮነን መንግስቴ ሠልጣኝ ምልምል ወታደሮች በማሠልጠኛው የሚሠጣቸውን ሁሉ አቀፍ ሥልጠና በመልካም ዲስፕሊንና በሞራል ሠልጥነው በማጠናቀቅ ከነባሩ ሠራዊት ጋር በመቀላቀል ለሀገራቸው የሠላም ዘብ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል።