አሸባሪነት በተግባር፣ማንነት በገሀድ ሲጋለጥ
ፅንፈኛው የአማራን ህዝብ ሰላም በማሳጣት የጀመረውን የሽብር ተግባር በማጠናከር ወደለየለት የህዝብ ጠላትነት በይፋ በመሸጋገር ፀያፍ ተግባራትን መፈፀም ከጀመረ ወራቶችን አስቆጥሯል።
የወገኑን ንብረት ከመዝረፍአልፎ ማውደም ጀምሯል፣እየዘረፈ ወገኑን ለመውጋት ብርታት የሰጠውን የገበሬውን አዝመራ ማቃጠል "የበላበትን ወጭት ሰባሪ"የተባለለት እኩይ ሴራ ነው።
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ዙሪያ ቀበሌወች የፅንፈኛው ቡድን በአርሶ አደሩ የተሰበሰበ ሰብል ላይ የእሳት ቃጠሎ አካሄደ።
የፅንፈኛ ቡድኑ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መንቆረር ክ/ከተማ የቦ አርጀና ቀበሌ በተሰበሰበ የአርሶ አደር የስንዴ ክምር ላይ ጉዳት አድርሷል።
በተስፋ መቁረጥ ላይ የሚገኘው ቡድኑ የንፁህ አርሶ አደሮችን ዘጠኝ (9) የስንዴ ክምርና የተሰበሰበ የከብቶች ቀለብ የሆነ ገለባ ጭምር ታህሳስ 5ቀን 2017 ዓ.ም በክብሪት ጭሮ አውድሞ የሸሸ ሲሆን በስፍራው የመንግስት የፀጥታ መዋቅር ፍጥነው በመድረስ ከዚህ በላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ማድረግ መቻሉን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።