ሪቫን ትባላለች።ጣሊያን ውስጥ ከተዋወኳቸው ቆንጆና የደስ ደስ ያላቸው ሴቶች ውስጥ አንደኛዋ ነች።የተዋወቅነው "ግሮስማ" የተባለ ታዋቂና ዝነኛ ሆቴል ውስጥ ነው።አስተናጋጅ ነበረች።እዛ ትልቅ ሆቴል ውስጥ አስተናጋጅ ሆኖ መስራት እራሱ የማይገኝ ዕድል እንደሆነ ተሰማኝ።"Benvenuto" አለችኝ።እንኳን ደህና መጣህ ማለት ነው።እኔም መልሼ "Grazie" አልኳት።የእውነት ለመናገር የጣሊያኖች ቋንቋ እጅግ በጣም ከባድ ነው።ያዝናናል፤ረጋ ያደርጋል፤ግን ደግሞ ለመያዝና ለመልመድ ይከብዳል።ቋንቋቸውን፤ባህላቸውን፤አኗኗራቸውን፤ሁሉም ነገራቸውን በደምብ ለማወቅና ለመረዳት ጊዜ ያስፈልጋል።
ሪቫና ፈገግ አለች።ጣሊያነኛ እንደማላውቅ ገብቷታል።በጣም እንደጨነቀኝም ተረድታለች።በዚህ ሰአት ነው እንግዲህ ነገሮች ሁሉ የሚገርሙ የሆኑት።ለካስ አማርኛ ትችላለች።"ምንድን የምትፈልገው?" አለችኝ።በጣም ደነገጥኩ፤ተነሳው፤ተቀመጥኩ።እጅግ በጣም ደስ አለኝ።ምክንያቱም ጣሊያን ከገባው ለመጀመሪያ ጊዜ አማርኛ የምታወራ ጣሊያናዊት ቆንጆ ሴት አገኘው።ይሄ ፈፅሞ ከማልጠብቃቸው ክስተቶች ውስጥ አንዱ ነበር።በቃ በውስጤ ሪቫና የኔ ናት አልኩ።ከምርም የእኔ እንደሆነችና ለኔ እንደምትሆን ያክል ተሰማኝ።
ከዛም ሁለት አደገኛና አስካሪ መጠጦችን አዘዝኩኝ።አብራኝ ለጥቂት ደቂቃዎች እንድታሳልፍም ጠየኳት።ግን እንቢ አለች።ለምን? ስላት "ከአንተ ጋር የማሳልፋት እያንዳንዷ ደቂቃ ብዙ ሺ ዶላሮችን ታስመልጠኛለች" አለችኝ።ኢትዮጵያ ውስጥ እያለው ብዙ ቢዝነሶች ስለነበሩኝ የገንዘብ ችግር አልነበረብኝም ነበር።በዛ ሰአት አንድ የቢዝነስ አማካሪ ስለነበረኝ እንዴት ገንዘቤን መያዝና መቆጣጠር እንዳለብኝ በደምብ አስተምሮኝ ነበር። ከዛ ቶሎ ብዬ "ግሮስማ" ውስጥ ከምታገኚው ዶላር የበለጠ እኔ እከፍልሻለሁ" አልኳት።የእውነት ለመናገር ራሴን ማሳየት አልፈለኩም ነበር።ነገር ግን ጣሊያን ያለው ሁኔታ ትንሽ ከበድ ስለሚል አንዳንድ ነገሮችን ለመማር የግድ ታስፈልገኝ ነበር።ከእነሱ ጋር ለመግባባት እነሱን መሆን ባያስፈልግም እነሱን መረዳት ግን ያስፈልጋል።ምክንያቱም ይሄ ከኢትዮጵያ የመጣሁበትን ምክንያት የሚፈታልኝ የመጀመሪያው ቴክኒክ ነው።
ከወደዳችሁት ይቀጥላል...
📓፦ሴልቫኒያ(ማስወሻዬ ላይ የፃፍኳት)
✍️፦Bemni Alex