Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በእጅ የተፃፈ የፍቅር ደብዳቤ ለሴቶች የአእምሮ ጨዋታ ይሰጣቸዋል።እኔ ደብዳቤ ስጽፍ ቁልጭ አድርጌ አልጽፍም።ጥቂት ዐረፍተ ነገሮችን ሆን ብዬ እሰርዛለሁ፤እደልዛለሁ።ሄለን የተደለዙ ዐረፍተ ነገሮችን ለማንበብ ከመጓጓቷ የተነሳ ሁለት የራስጌ መብራት እና አንድ ትልቅ ጣፍ አስተባብራ እንደምትጠቀም አውቃለሁ።በመጀመሪያ ከልቡ የወጣው ቃል ምንድን ነው? በኋላ ለምን ሰረዘው? በሁለቱ ሐሳቦች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? እያለች መመራመሯ አይቀርም።አንዲት ሴት ከተሰረዘ ዐረፍተ ነገር ጀርባ ያለውን ሀሳብ ለማወቅ የምታደርገው ጥረት በጎረቤት መታጠቢያ ቤት ውስጥ ወንድን አጮልቆ እንደ ማየት ያለ ደስታ ይሰጣታል።"ብቻ ምን ልበልህ?" በእጅ የተፃፈ ደብዳቤ ብዙ ምትኋት አለው።
📘 ርዕስ፦መግባት እና መውጣት
✍️ደራሲ፦በእውቀቱ ስዩም
✈️ሼር ለማድረግ፦ t.me/Bemnet_Library/5075
📘 ርዕስ፦መግባት እና መውጣት
✍️ደራሲ፦በእውቀቱ ስዩም
✈️ሼር ለማድረግ፦ t.me/Bemnet_Library/5075