የሆነ ቀን ንፁህ ነበርን፤የሆነ ቀን ውስጣችን ሰላም ነበር፤የሆነ ቀን ስለ ዓለም ምንም አናውቅም ነበር።አለማወቃችን ህይወታችንን በነፃነት እንድንኖር አግዞን ነበር።ግን ስናድግ እና ስንበስል ብዙ ነገሮችን ማወቅ ስንጀምር የሆነ ቦታ ላይ መታመም ጀመርን።ለካ አንዳንዴ ማወቅ ያሳምማል፤ለካ አንዳንዴ ማወቅ ያቆስላል፤ለካ አንዳንዴ ማወቅ ጥቅመ-ቢስ ነው።አንድቀን ከሚጠቅሙን ነገሮች ይልቅ የማይጠቅሙንን ነገሮች ስላወቅን ተጎዳን።
✍️ Bemni Alex
✍️ Bemni Alex