ቤተ ያሬድ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


የአብነት ትምህርት ለመማር
@lealem16 (+251934104451) ያናግሩን።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


በራሶት መንገድ ማስታወቂያ በመጨመር ማንኛውም ግሩፕና ቻናል ላይ በመልቀቅ ወይም ለግለ ሰብእ በመላክ መጋበዝ ይቻላል። በምንም መንገድ ቢኾን የእርሶን ሊንክ ነክቶ የገባውን ቻናሉ ይቆጥርሎታል።

መንፈሳዊ ቻናል ወይም ግሩፕ ያላችኹ ሰዎች ተጠቀሙበት የእኛም ጉባኤያችን ለሚፈልጉ ኹሉ ተደራሽ እንዲኾን አግዙን።


ትምህርት ቤታችንን በማገዝ በነጻ የፈለጉትን ይማሩ።

እንዴት ?

የሚሰጦትን ሊንክ ቢያንስ ለ፶ ወዳጆችዎ በመላክ ቻናላችንን እንዲቀላቀሉ በማድረግ።

ሊንኩን ለማግኘትና ዕድሉን ለመጠቀም
@lealem16 (+251934104451) ያናግሩን።


ክብር ይእቲ ወዕጣነ ሞገር
ዘመ/ር ያሬድ ዘርአ_ቡሩክ መምህረ ቅኔ ወትርጓሜ መጻሕፍት

መጋቢት ፳፰/፳፻፲፯ ዐ.ም

ግእዝ ክብር
●ኵሉ በግዕ ይትዐቀብ ለበሊዕ፤
●ወካልእ ውእቱ ዘቀራንዮ በግዕ፤
●እስመ ለሊሁ የዐቅብ ዐቃብያኒሁ በርትዕ፤
●ወእንዘ ሠዋዔ ይከውን ይቀርብ ለምሥዋዕ።

ግእዝ ዕጣነ ሞገር
●ሠራዔ ሕገጋት ክርስቶስ እመ ውስተ ወንጌል ትብል ይኤብስ ብእሲቶ እንተ ደኀረ፥
●ኒቆዲሞስ ዐርክ ዘበኀቤከ ነበረ፥
●በድኂረ ኦሪት ብእሲት ሕገጋቲከ ሰዐረ፥
●ወሚመ ትብልኑ ዘፈቀደ ገብረ።

ዐሠረ ነጋሢ
●ቤተ ክርስቲያን ድንግል ውስተ ከርሥኪ እግዚአ ኵሉ እስመ ተዐቍረ፥
●እምአእንስተ ዐለም ኵሎን ለሊሁ እስመ ኪያኪ አፍቀረ፥
●ብኪ እስመ ተፈወሰ ዘተሰብረ።

@beteyared21
@beteyared21
@beteyared21


✍️✍️ቅኔ ዘኒቆዲሞስ

✍️ጉባዔቃና

ለንጉሠ ነገሥት ክርስቶስ ሶበ አስተርአዮ ገሐደ
ኒቆዲሞስ ብእሴ ትህትና እምርሁቅ ሰገደ

ሁለተኛ

ይብል ክርስቶስ ኀዘነ ኒቆዲሞስ ጸንአ
ሞተወላዲሁ ስግደተ እስመበሌሊት ሰምአ

✍️ዘአምላኪየ

ኅዝንተልቡና ኦሪት ብእሲተ ዓመጻ ወድድቅ
እስመ ጠፍአ መልዕልተክሳዳ ኒቆዲሞስ ወርቅ
ወበእንቲአሃ ኀዘነት ወለተ አማኑኤል ጽድቅ

✍️ሚበዝሁ

በእንተ ኒቆዲሞስ ሊቅ አዝማደ ኒቆዲሞስ ጸርሑ እስመድኅረብዙህ ተሐውኮ
መንፈቀ ሌሊት ወጽአት ነፍሰ ኒቆዲሞስ አስተብርኮ
ወከዊኖቶ ዘርዕየ የዋሀ ልቡና ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ ባረኮ

ሁለተኛ

ምስጢረ ጥምቀት ሕሙም ዘበቀደሚ ፈድፈደ ወበዝሐ ሕማምከ
ስተይ ማየ በእንተ ኒቆዲሞስ ጥዒናከ
ዘኩሎ ነጸረ ብእሴ ጥበብ ክርስቶስ ከመሐዋርያት ይብለከ

ሶስተኛ

ወላዲተ ሙሴ ኦሪት በእንተ ኒቆዲሞስ ኮነት ሕመምተልቡና ሕምምተ
እስመ ኒቆዲሞስ ተርፈ በከመወጽአ ሌሊተ
ወፍጡነ ሰምዓት ወላዲተ ሙሴ ኦሪት ብሂለኒቆዲሞስ ስህተ

አራተኛ

ኒቆዲሞስ ይብል ወለተ ኢየሱስ ስግደተ ኢይትሌለይ ምስለህዝቡ
ወለተ ኢየሱስ ስግደት እስመቦአት ውስተ ልቡ
ወኩሎ ሰናየ ወበቀዳሚ ብዙኀ በእንቲአሃ ይነቡ

አምስተኛ

ኒቆዲሞስ ይብል ጠቢበ ጠቢባን ብሂል አስተብርኮሥጋ ጠቢበምንት
እስመ አስተብርኮ ጠቢብ ተሰወረ በሌሊት
ነሲኦ ብዙኀ ኒቆዲሞስሃ ንዋየ ዘውስተ መዝገቡ ኦሪት

✍️ዋዜማ

ጠበብተኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ እንዘበሌሊት ይትነሳእ ወያስተርኢ ገሐደ
ይትቃፀቡ ኀበኀበይብሉ ኒቆዲሞስ አብደ
ወለአረጋዊ ክርስቶስ ሶበቀዳሚ ሰገደ
አዝማደ ኒቆዲሞስ ይብሉ ድኅረተዋረደ
ኢኮነነ ምንተኒ ዘመደ


ሁለተኛ

ወለተ ኢየሱስ አስተብርኮ ከመቀዳማዊት ተጽህቀት እስመቤተሙሴ ወዮሳ
መጽአ መንፈቀሌሊት ኒቆዲሞስ ጽንሳ
ወባህቲታ ወለደት ወጠብለለቶ በልብሳ
ወእለ አስተርአዩ ዘንተ በእንተ ርዕሳ
ተጋብዑ ሰላሳ ወስሳ

ሶስተኛ

ኒቆዲሞስ በዓለዘቦ ወርቀ አስተብርኮ ብዙህ ዘኒቆዲሞስ አንቀጸ
ጥምቀተ ጽርሐተዋህዶ ዲበማይ ሐነጸ
ወንጉሠ ነገሠት ክርስቶስ ጽርሐተዋህዶ ሐወጸ
ወኩሉ ዘርዕየ ወአስተሐየጸ
እፎኑመ እፎኑ ደንገጸ

አራተኛ

በቀመረ ወርህ ኒቆዲሞስ ቀመረ ሌሊት ኦቀ ስግደተ ኒቆዲሞስ መርህ
እስመኮነ ቀመረሌሊት ኒቆዲሞስ ወርህ
ወቀመረ ፀሐይ ክርስቶስ ቀመረ መዓልት ብዙህ
እስመ ወርህ ምስጢር ወፀሐይ ብሩህ
ተዋሕዶ ዜናሁ ለኖህ

✍️ሥላሴ

ስግደት ወአስተብርኮ ሊቃውንተኤልያስ ይወጽኡ
ውስተ ቤተመቅደስ ኦሪት እስመ ዘኤልያስ ኦቀ
ኒቆዲሞስ ስርዓተ ማኅሌት በሌሊት ሐልቀ
ወእምቤተመቅደስ ኦሪት እግረ አማኑኤል ርህቀ
ለለአክሞሰሰ ወሰሐቀ
ኒቆዲሞስሂ ማኅሌት ለዘአምነ ህቀ
ይከውኖ ሰላመ ወጽድቀ

ሁለተኛ

ኒቆዲሞስ ሐራሴምድር ሚ ትጉህ ወሐረሳዊ
ዘርዐ ሃይማኖት ይዝራእ በዘልቡናሁ ፈቀደ
እስመሶረ አስተብርኮሥጋ በሌሊት ጸመደ
ወባዕለ ጸጋ ክርስቶስ ከመይኩኖ ዘመደ
ምስለ ኒቆዲሞስ ተወሐደ
ሃይማኖተ ዘርዐ አመ አፈድፈደ
ወሊተኒ ልቡናየ ነደ

ሶሰተኛ

ኒቆዲሞስ እስራኤላዊ ብሂለ እስራኤል ያዕቆብ
ከመ ይህስስ እክለ ምስጢረ ጥምቀት ህቡአ
ምድረግብጽ አስተብርኮሥጋ በሌሊት ቦአ
ኒቆዲሞስሂ ያዕቆብ ኀበ አማኑኤል መጽአ
ድኅረተሰወረ ወተኀብአ
እስመ አስተብርኮ ሲሳየ ወስግደተ ቅብአ
እምቀዳሚ የሐስስ እግዚአ

✍️ዘይዕዜ

ወለቱ ለአብ ህገኦሪት ሚ ህዝንት ወኀዘነይእቲ ጸንአ
ኒቆዲሞስ እስመበላዕሌሃ ኀፀየ ካልአ
ወዘመደ ሥጋ ብሉይ ተሰወረ ወተኀብአ
ወለተ ኢየሱስ ሐዲሰ እምድኅረ አምጽአ
ኒቆዲሞስ ሄር መምህረ አምልኮ እግዚአ
ወለተ ኢየሱስ ሐዲሰ እምድኅረ አምጽአ

ሁለተኛ

ለካህናት ስግደት ወአስተብርኮ ሊቀ ካህናት ክርስቶስ
እንዘ ትዔዝዞሙ እንከ
ኒቆዲሞስ ልቡናክልዔቱ በይነምንት ተሐውከ
ኢፈቀዱሂ ይስምኡ ስርዓተ ኦሪት ትዕዛዘከ
እስመ ህገ ኦሪት ጽኑእ ነገረቃልከ
ፍጡነ ሰምኡ ወተጋብኡ ኀቤከ
እስመ ህገ ኦሪት ጽኑእ ነገረቃልከ

✍️መወድስ

ዲበምድር አጽነነት ዕፀ አስተብርኮ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ጠበብተ ህሬ
በከመ ይቤ ክርስቶስ መገስጸቆሬ
አስመበዝሐ ባቲ ኒቆዲሞስ ፍሬ
ወተጽህቀት በፍሬሃ ዕፀ አስተብርኮ ለወልድ እግዚአከዊን መሐሬ
ወድኅረ አስተርአየ ፍሬዛቲ ዘበእስከደሬ
ቀንአ በፍሬሃ ምስጢረ ጥምቀት ወልደኖሬ
ወአስተዳለወ ካዕበ ብእሴአምልኮ ፈጣሬ
አዕጹቀዘይት ነቢያተ አምሳለ ዕፀድርስ ወፕፕሬ

ሁተኛ

ያስተፌስሖ ለወልድ መምህረ ርህራሄ ብሂለ ኢይረክብ ሰብአ ዘከመ ኒቆዲሞስ ሰብአጽድቅ
እሰመእንዘኩሉ ይጎይይ በጊዜምንዳቤ ወጻህቅ
ኢተፈልጠ ጊዜምንዳቤሁ ኒቆዲሞስ ሊቅ
ኢኀለየሂ ኒቆዲሞስ ጊዜምንዳቤሁ ለወልድ
ይጉየይ ወይርኃቅ
ወምስሌሁኒ ኒቆዲሞስ ዘበርህራሄሁ እውቅ
ምዕረ የኀዝን ወምዕረ ይስሕቅ
ወሶበነጸሮ ለወልድ ፍኖተ ደቂቅ
ኒቆዲሞስ አረጋዊ አስተብረከ እምርሑቅ

ሶስተኛ

ለምስጢረ ጥምቀት ወላድ ዘያደነግጻ ጻህቀልቡናሃ ፈድፈደ ወምንዳቤይእቲ ተመክዐበ
ብእሴ ጥበብ ክርስቶስ በከመነገረነ ካዕበ
ኒቆዲሞስ ወርኀወሊዶታ እስመዮም ቀርበ
ወብእሲሃ ህገኦሪት ጻህቀልቡናሃ ዘርዕየ ተሐውከ ወተአጽበ
ወይብል ዘአስተርአያ ብእሴ ከዊን ጠቢበ
ላህበ ገጸይእቲ አስተብርኮ ቅድመገጸይእቲ አንጠብጠበ
ወአዕይንቲሁ ለወልድ ከዊኖተዛቲ ሰሐበ
እስመ አሰሰለ ከዊኖታ ርኃበ ወጽጋበ

አራተኛ

ሶበ ጠየቆሙ ወልድ ምስጢረጥምቀት ለሐዋርያት አርድዕት ወኒቆዲሞስ ዘገዝፈ
እንዘይተርፉ ካዕበ ወእንዘይወድቁ እልፈ
አርድዕተ መዓልት ሐዋርያት
ኒቆዲሞስ መርድአ ሌሊት እፎኑ ሐለፈ
ወመርድአሌሊት ኒቆዲሞስ ዘበበጊዜሁ ያነበብ
አስተብርኮ ሥጋ መጽሐፈ
ጽውዐ ወርቀ ጴጥሮስ ሃይማኖተ እምኀበክርስቶስ ተወክፈ
አንብቦተ መጽሐፍ ልደተማይ እስመ አፈድፈደ ወአዝለፈ
ወግብረ ኒቆዲሞስ ሊቅ እስከነይሰማእ ጽንፈ
ኢኀደገ አንብቦተ ወምንተ ኢያዕረፈ

የጻድቁ የቅዱስ ኒቆዲሞስ በረከት እጥፍ ድርብ ይሁንልን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏


ሊ/ጉ አባ ገብረማርያም

@beteyared21
@beteyared21
@beteyared21


ለሁላችኹም መልሻለሁ። ከመልእክት መብዛት የተነሣ አይቼ የረሳሁት ካለ ወይም የምዝገባ ሒደቱ ያለምክንያት የተቋረጠበት ካለ ይጻፍልኝ።

@lealem16
+251934104451


ቅኔ መማር የምትፈልጉ ሁሌም ማታ ከ2:00--5:00 ቀጥታ በጉባኤው ገብቶ ለመከታተል ለትምህርቱ የማትመድቡ ከኾነ ወይም በግል በመደወል ቢያንስ በሳምንት 3 ቀን ውስጥ በእነዚያ ቀናት 1 1 ሰዓት አመቻችታችኹ የማትማሩ ከኾነ
ባትመዘገቡ ይሻላል፤ ከንቱ ድካም ነው።


የቤተ ያሬድ ንባብ ቤትና ቅኔ ቤት መርሐ ግብር


በየሳምንቱ ዐርብ ዐርብ በመድኀኔዐለም መቀኜት የሚቻል ሲኾን፣

እንደገና ሁሌም ክብር ይእቲ የሚወርደው በዚህ መኾኑ ይታወቃል።


👉👉ቅኔ ዘመጋቢት መድኃኔዓለም

👉ጉባዔ ቃና

ትቤ ወላድ ቀራንዮስ ከመኢይድክም ኃይልየ
በትዕምርተ መስቀል አአትብ አማኑኤልሃ ገጽየ

ሁለተኛ

አንከረ አብ ወመንፈስቅዱስ ተምአ
አሐዱ ህብስት እስመለኀምስ ተሠርአ

ሶስተኛ

አማኑኤል ይብል እንዘይትከዓው ደምየ
ሥጋየ ጠግዐ ዲበዕፀመስቀል አጽምየ

አራተኛ

ምንት ውእቱ ሕማመሥጋወልድ ስቅለት
ስቅለተ ሥጋ ሕማም እስመ አብጽሆ ለሞት

አምስተኛ

ባሕርየ መስቀል ለከ ወባሕርየ ክርስቶስ ሎቱ
ባሕርየ መስቀል ሕይወት ወባሕርየ ክርስቶስ ሕይወቱ

ስድስተኛ

መቃብረ ሙሴ ሕሙም እምድኅረ ሐመ ሕዳጠ
ሕሙም መቃብረሙሴ መድኃኒተ ውህጠ (መድኃኒት የተባለው ክርስቶስ ነው

ሰባተኛ

ይብል ወልድ ማዕምረ አፍዓሁ ወውስጡ
ለመስቀል እጓለመዋቲ ነፍስየ እሜጡ

ስምንተኛ

አማኑኤል ይብል በከመቀኖት መሳጢ
መስቀል ብእሴምንዳቤ ኪያየ ያነጢ

ዘጠነኛ

ይብል ወልድ ማዕምረ አፍኣ ወውስጣ
ለብእሲት ምድረ ቀራንዮ መኑመ አስፈጣ

👉👉ዘአምላኪየ

ውስተ ቤተመቅደስ ስቅለት አመተ ተፈተተ ናሁ
መስቀል ብእሴንስሓ ተወክፈ ሥጋሁ
ሎቱ ለወልድ አምጣነ መድኃኒት ለሊሁ

ሁለተኛ

ብእሴ ሃይማኖት መስቀል እንዘይኔጽር ቀዊሞ
ቀራንዮስ ብእሲተዓመጻ ተመጠወት ደሞ
ወዳግመሂ ተወክፈት ለአማኑኤል ሕማሞ

ሶስተኛ

ሶበ አማኑኤል ዖቀ ከመይመውት ባህቲቶ
ለመስቀል እጓለመዋቲ አውረሰ ንብረቶ
ወእጓለማውታ መስቀል አስተሐፈረ ጸላዕቶ

👉👉ሚበዝሁ

ኦ ገብርኤል በይነምንት አርመምከ ወኢተናገርከ በይነምንት
እንዘ ይወስዶ ለወልድ ውስተ ቤተ ሞቅሕ ስቅለት
በዓለ ጊዜ መስቀል በከመአዘዞ ፍጡነ በዓለዘመን ቀኖት

ሁለተኛ

ቅንዋት ህዝብ ካህነ ቀራንዮስ ወልድ እንዘ ይትናገር ቀዲሙ
ቅድመገጸ ካህን ወልድ አትህቱ ርእሰክሙ
ወሶበ ይቤ ስግዱ ታህተ እገሪሁ ስግዱ እስመ ቅዱሳን አንትሙ

ሶስተኛ

በበአፉሆሙ ይብሉ ቅንዋት ካህናት ለወልድ ፍቁራኒሁ
ከፈለነ ንብላዕ እምዕፀ ሕይወት ሥጋሁ
ወደሞ ክቡረ ወሀበነ ንስተይ እስመተስፋ ሕይወት ላዕሌሁ

አራተኛ

ነቅዐ ማየ ሕይወት ብዙህ አማኑኤል ኮነ
ጠለዕፀመስቀል ሠናይ
እስመ ሙሐዘ ማይ ኮነ አማኑኤል ነቅዐማይ
ወፍሬ በረከት ነሥአ ዕፀ ተዋሕዶ መስቀል። ወኩለታሁ ሲሳይ

አምስተኛ

ኢሳያስ ይብል ለሕማም ወግፍዕ አረጋውያን መንፈቆሙ
ብእሴ ሃይማኖት መስቀል ኀበ አማኑኤል ወሰዶሙ
ለሕማም ወግፍዕ አረጋውያን ዘበዝሁ
እስመ ተስፋ ሕይወት ቦሙ

ስድስተኛ

ኢይፈርህኑ እግዚአ ብእሴ ዓመጻ ኩይናት ለተመጥዎደም ሶበቀርበ
ብእሴ ዓመጻ ኩይናት እስመበደመሰብዕ ተሐጽበ
ወሚ ሐካይ ብእሴ ዓመጻ ኩይናት እስመኢነስሐ ካዕበ

ሰባተኛ

ካህነ ቀራንዮስ ወልድ ተገፍዖ ሥጋ ወንጌለ እንዘያነበብ በምልኡ
አዕጋረ ወልደአብ ህዝብ ቁሙ ወአጽምኡ
ወሶበ ቀዳሚ ይትነበብ ተገፍዖ ሥጋ ወንጌል ከመቀዳሚ ስምኡ

ስምንተኛ

ዘመደሥጋ ብሂል ዘመደ ሥጋወልድ መስቀል እስመሕማመወልድ አመሶጠ
ዘመደሥጋሁ መስቀል እስከነይመውት ኢተፈልጠ
ወዘመደሥጋ መስቀል ድኅረሞተ ወልድ ኀበአዝማዲሁ ተመይጠ

ዘጠነኛ

ቅንዋት ዘብርት ወንጌላውያን ይቤሉ ሶበወልደአብ ያንሶሱ
ብእሲተ ሕማም መስቀል ገሰሰት ጽንፈልብሱ
ወበጽንፈ ልብሱ ለወልድ ለብእሲተ ሕማም መስቀል ሕማማቲሃ ተግህሱ

👉ዋዜማ

ይብል አማኑኤል ድኅረማዕድየ በልዑ በዕፀ መስቀል እዴየ
ቅንዋት ሰማዕተዓመጻ ተንስኡ ላዕሌየ
ወዘበቀዳሚ መከሩ ከመይስተዩ ደምየ
ቅንዋት አሐው ምስለ ጸላዕትየ
ተማከሩ ይብልዑ ሥጋየ

ሁለተኛ

ብእሴ ኦሪት አማኑኤል መስቀል ርግብ እንዘትመጽእ ኀቤሁ
ቀርበ ከመይትወከፋ ሰፊሆ እዴሁ
ብዕሥራተ ሕይወትነ ለነ ከመይጠይቅ ለሊሁ
መስቀል ርግብ እስመ ተስፋሁ
ለዓለም ዘብዙህ ደዌሁ

👉ሥላሴ

በከመኢበዝኀ ኀዘነ አዕላፍ ተዋሕዶ
አሐዱ ህብስት እንዘ ይሰየጥ ሠላሳ
እምዮም ወእምይእዜሰ ኢተረክበ ስሳ
እስመ አሐዱ ህብስት ሕይወተ አዕላፍ ኃምሳ
ወእምቀራንዮስ እስከሱሳ
በረከተዘቦ ህብስት በበሐሰሳ
ኢረከበ ልብነ አቢሳ

👉ዘይዕዜ

ይቤለነ ሊቅ ዕፀመስቀል ብእሴዓመጻ ቀኖት እንዘያስተዋርድ ሰብአ
ቀኖት ብእሴዓመጻ በረከተ ኀጥአ
እስመኢያከብር ሄረ መምህረ ወእግዚአ
ብእሴዓመጻ ቀኖት እስከነአጥፍአ
ስመ ወላዲሁ እግዚእ ወበላዕለ እግዚእ ተንሥአ
ብእሴዓመጻ ቀኖት እስከነአጥፍአ

ሁለተኛ

ለዐቃቤ ሥራይ ወልድ ዘበባህቲቱ ሕሙማነ ሥጋ ቀኖት ወዕፀመስቀል እኁነ
ዐቃቤ ሕይወትነ ይቤልዎ
እስመወልድ ዐቃቤሥራይ መድኃኒተ ኮነ
ወነፍሰ ብዙኃን ይቤዙ የሐስስ ሕሙማነ
ዐቃቤሥራይ ወልድ እስመ ሕይወትነ
ዐቃቤሥራይ ወልድ ዘተፈነወ ኀቤነ

👉መወድስ

ብእሴ ትህትና ወጽድቅ መድኃኔዓለም
ዘበቀዳሚ ይፈቱ ነገረ ቅንዋት ሕጻናቲሁ
ቅንዋት ደቂቅ ሶበአልጸቁ ኀቤሁ
ተወክፎሙ ወተቀበሎሙ ሰፊሆ እዴሁ
ወቅድመ ሰዐልዎ አዝማደ ቅንዋት ደቂቅ ከመ ይባርኮሙ ናሁ
ቅንዋትሂ ደቂቀዘቦ ኢትዮጵያ ተስፋሁ
እንዘ ይብሉ ኆሳዕና ይዜምሩ በቅድሜሁ
ወዘመደ እሉ መስቀል እንዘ ይሰምእ ዜናሁ
ፈቀደ ቀሪቦቶ ከመይርዓይ ኩለታሁ

ሁለተኛ

ካህነ ትህትና ወጽድቅ መድኃኔዓለም ዘስብሐቲሁ እጹብ ወመንክር ቅዳሴሁ
ውስተ ቤተመቅደስ ስቅለት እንዘ ይወጽእ ለሊሁ
ቅንዋት ህዝበ ተዋሕዶ ሰዓሙ እዴሁ
እንዘይብሉ ይብጽሐነ በረከተ ቅድስት እዴከ
ወመንፈስ ቅዱስ ዘበላዕሌሁ
ኩይናትሂ ዘመደሥጋ ዘበእንቲአሁ
ይቀውም በገቦሁ ወይተሉ አዕጋሪሁ
ወካልዑኒ መስቀል እንዘይኔጽር ኪያሁ
መዓልተ ወሌሊተ ኢተፈልጠ እምኔሁ

ሶስተኛ

ካህነ ትህትና ወጽድቅ መድኃኔዓለም ሶበ እዴሁ አሐዘ ወገሠሠ ኩለታሁ
ሕሙመ ሥጋ ቀኖት ድኅረ ተፈወሰ ናሁ
ተንሥአ ቀዲሙ ወቆመ ቅድሜሁ
አምጣነ ዘኮነ መጻጉዐ ሕሙመ ሥጋ ቀኖት ሐይወ እምደዌሁ
ዕፀመስቀልሂ ዘመደሥጋ እንዘያንሶሱ ምስሌሁ
አንከረ ወተደመ አምጣነ የአምር ሕላዌሁ
ወሶበ እዴሁ አሐዘ ድኅረ ተንሥአ ለሊሁ
አንሶሰወ ቅድመገጹ እስመ ጸንዐ እገሪሁ

አራተኛ

ሐዋርያ ሰላም ወጽድቅ መድኃኔዓለም ሕማመ ጣቢታ ቀኖት ድኅረ አስተርአያ አዕይንቲሁ
ጣቢታ ቀኖት እምኀበሰከበት ናሁ
ትንሥኢ እንዘይብል
ለቀኖት ጣቢታ መጠዋ እዴሁ
ወጣቢታሂ ቀኖተሥጋ ፍጡነ ቆመት
ወአንሶሰወት ቅድሜሁ
ጣቢታሂ ቀኖተሥጋ ድኅረ ተንሥአት አዲሁ
መሐለት እንዘትብል ኢይትፈለጥ እምኔሁ
ወጣቢታሂ ቀኖት ከመ አሬዳኢሁ
ሐዋርያሁ ሐዋርያሁ ሐዋርያሁ ሐዋርያሁ

አምስተኛ

ይቤ መጽሐፍ መድኃኔዓለም ፈነወ ሰብአ ውስተቤተልሄም ገቦየ
ንጉሠ እስራኤል ኩይናት ከመ ተመነየ
ማየ ቤተልሔም ደመገቦየ
አምጣነፈተወ ከመይስተይ ማየ
ኢፈቀደሂ ከመእስተይ ሶበ አምጽዕዎ ሊተ ቅንዋት አሐውየ
ደመ ምስለማይ እስመአስተርአየ
ወማየ ዘፈተወ ይስተይ ኢሐለየ
ንጉሠ እስራኤል ኩይናት አምጣነ ሐረየ
ሞተ አሐውየ ቅንዋት ወመቅበርተ መስቀል ዘመድየ

👉አጭር መወድስ

ለእግዚአ ስብሐት ምስጢር ካህናተብዙህ ምናኔ
ይቤልዎ ኢየሐልቅኑ ዓመቲከ ቅኔ

ሁለተኛ

አምላከ ሊቃውንት ምስጢር መኮንነጽድቅ ወግርማ
አብርሆን ለአዕይትየ ትርጓሜ ወዜማ

ሶስተኛ

ትቤሎ ድንግል መጽሐፈ ሐተታ ፍጠኔ
ለእግዚአ ስብሐት ቃለ ትርጓሜ
ዘመንከ ዜማ ዘመንየ ቅኔ

የመድኃኔዓለም ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን ለዛሬ ዓመት በሰላም ያድርሰን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ሊ)ጉ አባ ገብረማርያም

@beteyared21
@beteyared21
@beteyared21


መወድስ
ዘመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
ለእመ ንጉሥ ይነግሥ ዘበበዘመኑ  እንዘ ስመ ስልጣን ይትዌለጥ  ወለእመ ጳጳስ ይትጰጰስ
ለለእለቱ የሀውር እንዘ ይበዝህ ተጽናስ
በሀገር ኢትዮጽያ  ወኢቆመ እስከነ ይእዜ ምንዳቤ ወባእስ
ወለምንት ተጰጰሰ ለእመ ኢያምጽአ ፍቅረ ወለምንትኑ  ዘይነግስ
ለሀገርነሂ ኢትዮጵያ ከመ ተሰይጠ ክርስቶስ
ለባእድ ከመ ይሲጣ ሀሎ ዘየሀሰስ
በዘሀላፊ ንዋይ ወበዘየሀልቅ ልብስ
ወረሀብ ይቀትለነ እንዘ  ቦ ዘይትሀረስ
እስከነ አባይ ይትዐቆር ወእስከነ ይማስን የብስ
ወረሀብ ይቀትለነ እንዘቦ ዘይትሀረስ

@beteyared21
@beteyared21
@beteyared21


ተመዝግቦ ለመማር
@lealem16
+251934104451 ያናግሩን።






ለመመዝገብ እያናገራችሁኝ ላላችሁ ለሁላችሁም እመልሳለሁ። በትዕግስት ጠብቁ ገና ቃለ መጠይቅም ስላለ አትቸኩሉ።

ተመዝግባችሁ ያላሳወቃችሁኝ ላናግራችሁ ስሞክርም ያስቀመጣችሁት ስልክ በቴለግራም የማይመጣ አለና ያላሳወቃችሁ አሳውቁኝ።
@lealem16
+251934104451


ንባብ #አልተስተካከል #ለሚላችኹ #መፍትሔ


#አንድ #ጊዜ #ወይም #ድጋሜ #አስተካክሉ #ተብላችኹ #አልተስተካከል #ለሚላችኹ፦

መሠረታዊ ችግሩን መለየትና ማስተካከል ነው።
ለምሳሌ፦
ለምዶባችኹ ከኾነ የታረመላችኹን ቃል እስከትይዙት ድረስ #መጀመሪያ #በተናጠል #ያንን #ቃል #ብቻ #ደጋግማችኹ #መጥራት
ከዚያ ሁሉንም ዕርማቶች በዚህ መልክ መዝለቅ።
በመቀጠል ከሙሉው ንባብ ውስጥ ስህተቶቻችኹ የት የት እንዳሉ ማስተዋል።
(ምዕራፍ ቁጥር የምንጽፍላችኹ ለዚያ ነው።)

በመጨረሻ ሙሉውን ንባብ ደጋግሞ ማጥናትና እንደገና ሪከርድ አድርጎ መላክ ወይም ላይብ ላይ ገብቶ ማሰማት ነው።


ከውዳሴ ሠሉስ "ለዘይሴስዮ" ብቻ አስቸገረቺው።

ይሄኛው ደግሞ ፍሥሓ ይባላል። በራሱ ጥረት ረከርድ እያዳመጠ ይሸመድድ፤ የያዘውን ለማሳረም ይሄን ጊዜ እየተጠባበቀ ነበር። ።

አሁን የማክሰኞውን ሙሉውን በቃሉ ብሎ በ17 ደቂቃ አለፈው። 😍😍😍


ከንባብ ቤት

ተማሪ ማኅቶት
(ጸሎተ ሙሴ ፩ ፪ ፫ )ን ሲማር፣ እርማቶቹ በጣት የሚቆጠሩ ናቼው።

ክለሣ እንዳይመስላችኹ መጀመሪያው ነው ። 🥰🥰🥰

18 last posts shown.