ከመጽሐፍ ገጽ 📚😍


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Books


"There is no friend as loyal as a book"
Ernest Hemingway
unlimited quotes💭
Daily book recommendation 📚
Music to vibe to 🎶
Deep dives into the epic novels📖
Short stories🖋 and thoughts🤔
We forever live between the pages💖

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Books
Statistics
Posts filter


አንተ (ክፍል ሁለት)

የኔና ያንተ ፍቅር ዝንተ ዓለም የሚኖር፣ ከዓለም መጨረሻ እንኳ ተርፎ በሕዋው ላይ ብቻውን የሚንሳፈፍ። የቱን ነግሬ የቱን ልተውልህ፣ እውነት የመሰለኝን ፍቅር ባንተ አይቻለው። ፈንድቄ ተፍነክንኬ ትንሿ ሰፈራችን በሳቄ አውኪያለው። ከቤትህ ደብቀህ አስገብተህ ወንድነትህን አሳይተኸኛል። ጉልበትህን ተደግፌ የሚጣፍጥ እንቁላል ፍርፍር፣ የፍቅር ፍርፍር ከጅህ ጎረስኩኝ? ግን ከዛ የዘለለ ምን ነበረን ? አልጋ ላይ መራወጥ (እሱም የጥድፊያ ሰው ሳይመጣ)፣ የማይገባንን የነጭ ፍቅር መመልከት (አሁን ድረስ የሱ አይነት ፊልም እንደሚያበሳጨኝ ታውቃለህ?) በቃ የልባችንን ማውራት የለ፣ ስለወደፊት ማሰብ የለ።


"የመጀመሪያዬ ነሽ"አልከኝ። እንዳልሆንኩኝ አውቅ ነበር በፈረንጂኛ ልበለውና 'you know exactly what you do, you know it well, too well'

'እንዴት አወቅሽ?'

እንዴት ልበልህ የዛኔ ሴትነት የለገሰችኝ ስድስተኛ ስሜት ይስለኝ ነበር ። ግን እናቴ የአዋቂ ነገሮች ቁጭ አድርጋ ሳታስረዳኝ በፊት አውቀው ነበር።

አየህ በልጅነቴ አፌ ሳይፈታ በፍርሃት ዲዳ ሆኜ ሁሉን አይ ነበር አስተውል ነበር። ባልተረዳሁት  ሕመም  አቃስት ነበር። በሽታ መሆኑን እንኳ ሳላውቅ  ባህሪሄ ነው አመሌ ነው በሚል እሰቃይ ነበር? ይሄንን እንኳ አላውቅም ። በማላውቀው ቅዠት ግን እንቅልፍ ባይኔ ዛይዞር አድራለው። (የአክስቴ ልጅ እጆች ጭኖቼ ውስጥ፣ የአንድ ተከራይ ** አቅፎኝ እግሮቼ መሃል፣ በአፉካዶና ዳቦ የተጠረዘዘ ቦርጯን ላይዬ ላዬ ጥላ ከንፈሬን የምትመጥ ጠባቂ ጎረቤት...) ታውቃለህ ሁሏም ሴት በዚውስጥ የምታልፍ ነበር የሚስለኝ፣ የሆነ የሕይወት አንዱ አካል። መጥፎነቱ አይታየኝም ነበር (አሁን ላይ እንዲ ነው ብልህ አታምነኝም እኔም ጠባሳዬን መንካት አልፈልግም) መጥፎ ባልመሰለኝ ግን ለእናቴ እንኳ መንገር በፈራሁት ክብሬን፣ ልጅነቴን፣ ነፃነቴን ነው ያጣሁት። ደሞ ብዛታቸው እነዚህ ጠባሳዎቼ። አንዱ ባንዱ ሲደረብ ግማሹ በጊዜ ሲፈዝ፣ ሊጠፋ ሲል ግን አተኩረው ካዩት መልሶ አይኑን የሚያፈጥ። ዲዳ ያደረገኝ፣ መጥፎ ያልሆነው በሽታዬ ይሄ ነው። እኔንም ወደ መርዝነት የቀየረኝ መርዝ ... አየህ እኔ መጥፎ ነው ብዬ አለማሰቤ አልገደለኝም እንጂ


ልረግምህ ተነስቼ ሌላ ፈተፈትኩኝ አይደል ?

ሕይወትም ያው ነች። ሌላን መፈትፈት፣ የሕልም ኑሮ ማሳደድ፣ ወይ ደንዞ ድንጋይ መሆን ቢቀመጡብን እንኳ የማይከብደን፣ ለሌላው መኖር መሞት። manual አልተሰጠንማ ቀድመን የምናጠናው script የለማ። ሕይወት የተቀመረ አይደለም፣ እኛ ነን ለመቀመር ምንሞክረው። ለሱም ደሞ ፎርሙላውን አናውቀውም። በቃ

ስማኝ ሁሉ ነገሬ ነበርክ፣ በጥቂት ፍትጊያዎች፣ የፍቅር ልፊያዎች እኔ በመሰለኝ እስትንፋሴ ሆንክ። ደውለህ ዘፈን ትጋብዘኛለህ፣ ማን አድርጎት ያውቃል ? ፍቅር አንድ። ስስምህ አንገትህ ስር በትንሹ ... በጆሮዬ የሚያንቃጭለው ማቃተትህ ነው። የደምስርህ መራወጥ መወጠር ነው። ፍቅር ሁለት። እጅህ ፀጉሬ ውስጥ ሲርመሰመስ፣ ስታወራ (ምን እንደምታወራ አላውቅም ግን በተመስጦ እሰማህ ነበር) በለስላሳ ሰመመን ፣ የራሴን አለም ካንተ ጋር በሃያና ሠላሳ አይነት እየገነባሁኝ ነበር። ፍቅር ሶስት።'የኔ **** እንደዚህማ አያደርግም' ማለት ጀምሬ ነበር። አዋጅ አውጄ። ፍቅር አራት። ለረጅም ሰዓት ታየኝ ነበር ያለቃላት። በዓይን ማውራትን ያሰለመድከኝ አንተ ነህ።

ፍቅር አምስት። አጠገብህ አስቀምጠኸኝ የራስህ ስራ ላይ ትመሰጥ ነበር።

ፍቅር ስድስት

ፍቅር ሰባት። ውሃ ቀቅዬ ቅጠል ጨምሬ ብሰጥህ ይጣፍጣል ብለህ እጄን ሳምከኝ "እጅሽ ይባረክ"

ፍቅር ስምንት...አስቆጠርከኝ። አለም ለኔ ጎዶሎ ሳትሆን ሞልታ የተርፈረፈች ነበረች።


ስንት ጊዜ አብረን ቆየን 4 ወር። የዛኔ እንደሌሎቹ 4 ወር አራት ቀን ሆነብኝ። እኔንጃ አሁን ሳስበው ግን በጣም ትንሽ ጊዜ ነው። ሁሉም ጅማሬ እንዳለው፣ ፍፃሜም አለው፣ ፍፃሜ ባይሆን እንኳ ወደፍጻሜው የሚያንደረድር እንቅፋት አይጠፋም።

'እሷን እንዳትዪና እንዳልስቅ ከመጀመሪያውም ነግሬሽ ነበር በኔ እሷ መሃል ምንም እንደሌለ'

አይ አንተ። እኔም ነግሬ ነበር ቀልቤ እንደማይሳሳት እይታዬ እንደማይዋሽ። አሁን የት እዳለን ማየት ቀላል ነው። መደለንን ባንተ ሀ አልኩኝ ።
'በምንም የለም' ማስተባበያህ
አይንህ ለሷ ሲስቅ እያየው ቀንተሽ ነው ተባልኩኝ..
አጠገብህ ልቀመጥ ስመጣ መውጣት ...
አሞኛል ብለህ መተኛት
"ቤትህ ልምጣ?" "የለሁም።" "እሺ ደውልልኝ" እዛች ጠቅጠቅ ስልኬ ላይ ማማተር፣ ፊት መንሳት፣ ቃላት ማጠር... አይ ጊዜ ግን

አነባሁ፣ ኡኡኡኡኡ አልኩኝ ። ለሚያውቀኝ ለሚያውቅህ፣ ጉድ እስኪባል። ያንተስ መልስ "ከሷ ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም" የዛኔ ገረመኝ ? በጣም ። አንድ እውነትን አየሁኝ። ባንተ መወደስ የተሸፈነው አስቀያሚነቴን። የአለም ቆንጆ እንደሆንኩኝ ባይሰማኝም፣ ያንተ ሙገሳ በራስ አለመተማመኔን አጥፍቶት ነበር። ታዲያ አንተ ያንን ስትል በራስ አለመተማመኔ በአስር እጥፍ ተመለሰ። ሊዚህ ላመስግንህ ወይስ ልርገምህ ?


hey loves😍


Day 19 of GONE WITH THE WIND ❤️

This is the longest time i have spent with the book and we nearly 30% and let me already tell you this now, you should put this is on you TBR rn, start reading it now! I sewar you won't regret it ❤️


ለዚህ የድል ቀናችን እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን

the proud of Africa Adwa🤎


አንተ

አንተን በማወቄ ለማን ምስጋና ላቅርብ? ማንንስ ልረገም? ወይሰ ዝም ነው ምለው? አላውቅም። ምን አልባት እርግማኑንም ምስጋናውንም አንተ ላይ አዥጎደጉደው ይሆናል።
ለምን??

ስለገደልከኝ፣ ላልነሳ አፈር ስላላስከኝ።

ምስጋናውስ?!

እውነትን ባንተ ውሸት ውስጥ እንዳይ ስላደረከኝ፣ ማሳየት ብቻ አይደለም እንድቀበልም ነው ያደረከኝ።

ግን የቱ ይበልጣል? እርግማኑንም ምርቃቱንም ትንሽ ይበዛል ደሞም እርስ በእርሱ ይጣረሳል። መርቆ መርገም ምን ይባላል? መርቆስ መርገም ከየት የመጣ ነው ?? ሆሆሆ ላንተም ቢሆን ይከብድሃል

የተዋወቅንበት ጊዜ .....አይ አንተ እንድታውቀኝ ብዙ ጥሪያለው፣ እንድታየኝ፣ የሴትነት ጠሬኔ እንዲጠራህ እንዳበባ ፈንድቼ ልታይ ብያለው አንተ ሳታውቀኝ እኔ አውቅህ ነበር። ብትጠይቀኝ "ምንህ እንዳማረኝ አላውቅ may be ወንዳወንድነትህ" ብዬ አግበስብሼ አልፈው ነበር። እውነት እንነጋገር ከተባለ ግን ድርብ ጥርስህ ነበር ያስደነገጠኝ (ከየት እንደመጣ ባላውቅም ለድርብ ጥርስ ሟች ነኝ በተለይ ከቆንጆ የሚገመጥ ከንፈር በፈገግታ እሳት ሲገለጥ)፣ የጎርምስና ፂም ያልበቀለበት ከኔ ቆዳ እንኳ የለሰለሰ ጠይም ፊትህ....ጠይም ዓሳ መሳይ አልልህም ስለማይገባኝ (ዓሳ ጠይምነቱ የቱ ጋር እንደሆነ አላውቅም፣ ወይ የጠየመው አጋጥሞኝ አያውቅም)። ሁሉ ነገርህ ለስላሳ ነው። ሳቅህ፣ አይኖችህ፣ አይኖች በጸሐይ ጨረር ቡና ነፀብራቅ ሲረጩ፣ ጸጉርህ፣ ንግግርህ፣ አረማመድህ፣ ስምህ ሁሉ እንደ ወፍ ላባ ይለሰልሰኝ ነበር...እንደ ደመና አይነት ሰማያዊነቱ በሚዋጋ የጠራ ሰማይ የሚንጎማለለው ሃጣ በረዶ የመሰለው ደመና።

እንድታየኝ ያደረኩበት መንገድ ብነግርህ ምን ያደርግልሃል? ብቻ አየኸኝ። ዛሬ ድረስ ያስቀኛል የኔ በማላውቀው መፈንዳት ውስጥ የኔ መንደፋደፍ፣ ያንተ ማየት። አየህ አለማወቅ አንዳንዴ ጥሩ ነው። በልክ ነኝ ስህተት ብዙ እናያለን፣ እጃችንን ይዘው ከሚያስተምሩን ይልቅ በእውር ልባችን ወድቀን የምንነሳው ብዙ ያስተምረናል። አለማወቃችንን። እኔን ያንተ ለማድረግ ነገር ስትፈተፍት፣በማትውልበት ተጎልተህ ጊዜን ስትገድል በላወቀ፣ ባልገባው አግራሞትን በአይኔ ስዬ፣ ግራ መጋባት በድምጼ ሸፍኜ "ምነው?" እልሃለው የባጥ የቆጡን እንድታወራ። አንዳንዴ ግን አምላክ የማሰብ (የመምረጥ?) ችሎታን ሲሰጠን አብሮ ምላስ የምታድጥ እውነት ከጎሮሮአችን ቢተክል እላለው አለ አይደለ እሊናችን የሚያውቀውን ሀቅ ከምላሳችን አንሸራታ ከአፋችን የምታወጣ? አንዳንዴ ነው ታዲያ ሳናውቀው ሳናስበው።

"ጓደኛ አለችኝ በዚ ቀን ስለተጣላን ይሄ ቀን ሁሌ ይከፋኛል" አይኖችህ ይተክዛሉ የዓለምን ክፋትን እንዳዩ ሁሉ

አይኖቼ የሀዘን እንባን አቀርዝዘው "አይዞህ"ን ከንፈሮቼ ያጉተመትማሉ። አየህ አሁን ሳስበው በምንአልባት ውቅያኖስ ውስጥ፣ የኔን ብቸኝነት ባታይ ኖሮ፣ ልቤን የሰበረውን እኔ ሳላውቀው አንተ ባታውቀው ኖሮ.... .. (ኖሮ ብሎ ነገር ግን ደስ አይልም? እውነታውን ቢያንስ በአይነ ህሊናችን የመቀየር ስልጣን ይሰጠናል። ኖሮ ..ኖሮ.. ኖሮ ) ብቻ በመከፋት ፈንታ የልቤን ደስታ አይተሃት ቢሆን የሚያስከፋህም ቀን የኔም አይዞህ አይኖርም ነበር።

"ፍቅረኛ አለሽ?" በዚያ በሚያሰከፋህ ቀን ጠየከኝ

"ነበረኝ፣ግን ተጣላን" እንደተበደለ አማረርኩልህ፣ እንደተገፋ ትከሻህን መደገፊያ አድርጌ አነባሁኝ። አቤት ትከሻህ!!ግርማ ሞገስ ባንተ ትከሻ ነበር የሚለካው።

እውነቱን ልንገርህ?
ፍቅረኛ ነበረኝ ግን አልተጣላንም። የመጀመሪያ ፍቅረኛዬ በfacebook የተተዋወኩት። በጠዋት ቁር 4፣5 ሠፈር አቆራርጦ እኔን ለማየት የሚመጣ ሂጂ ከተባልኩበት ሸፍቼ ማርያም ማዶ ያለ ግም ሜዳ ላይ ቀን ሙሉ በወድሻለው፣ በልሳምሽ፣ በሰፊ ክንድ የማላውቀውን ፍቅር የምኮመኩም። አየህ መልክ የለውም ከጎሬዛ መለስ ያለ ነው (ግን ሴቶችዬ 'ከጎሬዛ መለስ ካለ ይበቀኛል' ስትሉ ከልባቹ ነው? አይመስለኝም) እንዳይደብረው ብዬ ከቀረብኩት ልጅ ፍቅርን አይቻት ነበር። እኔና እውነት ተግባብተን ነበር። ያኔ ግን film ላይ እንደምናየው 'በውበቷ ወንድን አንበርክካ' ብቻ የሆነ romantic scene ያለው መሪ ተዋናይ የሆንኩኝ ነው የመሰለኝ። ከዛ ያለፈ እውቀት የለኝማ። ክብሬን ሲጠብቅ እንኳ በአፍላነት በሾፍኳት የብልግና ተውኔት ተፈታተንኩት። የሚማርበት ኮለጅ ውስጥ የሚጎረብጥ ዴስክ ላይ ጭኔን ከፈትኩኝ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በፍቃዱ ማሩን ሊያዝረበርብ። ፍርሃቱ ይሁን ወይም ሌላ ምንም አላደረገኝም። የሱ ከዚህ እውቀት ንጹህ (ማርያምን አለማወቁን ለማስረዳት ልቅ ሆኜ ብነግርህ ደስ ይለኛል ግን የሱን ንጽህና ማጉደፍ ይሆናል ክብሩን መሬት መጎተት ይሆንብኛል) መሆን፣ እኔ በማያት ግን ባልተረዳዋት የውሸት መውተርተር፣መቃተት...hehe ከዛ በኋላም ግን ለኔ ያለው ክብር ለኔ ያለው ፍቅር አልቀነሰም ነበር። በጀንበር መጥለቅ ፊቱ ፈክቶ "የመጨረሻዬ ሁኚ፣ የኔ ሁኚ"

አንተ ይሄን ጥያቄ በጠየከኝ ሳምንት የሰው ልብ ሰብሬ ሸኘሁትኝ። ለክፋቴ ክፋት በቂ ምክንያት አልሰጠሁትም። ምንአልባት ያኔ ይሆናል ለኔ ቅጣት የሆንከው፣ አክኬ የማላድነው ቁስል፣ ነፍሴ ማቃጠያ ሲዎል። ታዲያ ያንስብኛል? በጊዜው ግን ልቤን በእንጥልጥል ቀጥ ያደረገው ሌላ romantic scene ካንተ ጋር የሌላ ቦታ ጓሮ ላይ በስስ ከንፈሮችህ ስትስመኝ ። ጥሩ ትወናዬን ጀመርኩኝ።

ይቀጥላል.....

✍🏾✍🏾ምንትዋብ
22/06/2017✍🏾✍🏾




I haven't forgot about Gone with the wind and to tell you the truth it is an absolute perfect novel, since i am reading it with my phone it is a bit harder to show it off እንጂ ቀን በቀን እንደተጣድኩበት ነው። we are now at 23%. I will keep you up with the progesss since እሱ ብቻ ስላለ ቶሎ ምጨርስ ይመስለኛል


አለንጋና ምስር

   ከየት መጀመር እንዳልብኝ አላውቅም። አዳም ሁሌም እንዳስደመመኝ ነው። ለገጸባህሪያቱ ቀርበን እነሱን ሆነን፣ የንሱን ሃሳብ አስበን፣ ከሃዘናቸው ሃዘንን፣ ከድስታቸው ሃሴትን፣ በነሱ ጫማ ቆመን እንድሄድ፣ በነሱ ዓይን አለምን ሒዎትን እንድናይ ያደርገናል። እንዳያልቅብኝ ሰስቼ የማንበው፣ የተደበቁ ትንንሽ አለላዎች እንዳያመልጡኝ ደግሜ የማነበው፣ ደግሜ አንብቤ መቶ አዲስ ነገሮችን የማገኝበት ነው። ውድ ከሆኑት መጽሓፍቱ አለንጋና ምስር እነሆ ። በቃ እንደዛ ብዬ ብጨርስ ደስ የለኛል ግን ትንሽ ለበል።  (spoiler alert)

1)የድንች መስዕዋት፡ ትንሽ ያስፈራኝ  ቢኖር ይሄ ታሪክ ነው። ምን አልባትም የድንች ቅዱስ መጽሐፍ መኖሩ፣ ወይም የድንቾቹ የሞት አጠባበቅ…. ለሞት ያላቸው ፍቅር? የሰው አምላካዊነት፣ ወይም ደሞ ሞትን ለፈሩ፣ መሰዕዋት መሆንን ለምን ብለው ለጠየቁ መነቀፋቸው መገለላቸው ከኔ እና እኔን ከመሰሉ አለም ላይ ከሚርምሰመሱ አመልካከት እና እምነት ጋር ተመሳስሎብኝ? It made me ask a question what if we are just potatoes under this earth and whoever and whatever is cultivating us just wants  us for surviving life among its kind? That is just what we are potatoes …. That have norms and rules, the obedient ones, that bids a time …a time for death? And that is our sole mission, the only responsibility is getting ready, just as death wants us to be…

2)ኦቾሎኒ፡  this for me is the most saddest story i have ever read. ታሪኩ በርግጥም አዛዛኝ  አይደልም፣ ይልቅስ እንደ ስማዖን ስንታችንን ነን ወርቅ እንደ መዳብ ቆርጥረን ያሽቀነጠርነው? ወርቅ መሆኑን እያወቅን?  ወደ ሌላ ያማተርነው፣ የበታችነት ሰሜታችን ሲሸነፍ፣ የራስ መተማመናችን እንደ እሳት ሲንበለበል፣ ከወርቅም የበለውጠው ፍቅርን እናጣለን.. ቆይቶ ሲገባን ያንገበግበናል።


3)አልንጋና ምስር፡ it is one of, the only story i treasured in my heart. It is family. it is the አለንጋ for me😊. አላውቅም እንዲ ነው እንዲያ ነው በዬ ማስረዳት አልችልም። እናትነትን፣ ለጅነት፣ ጨዋታው፣ ጥናቱ፣ የአባት ቁጣው የእናት ፍቅር በምስር። መዋደዳቸው እራሱ እውነት ነው። ከቤተሰብ ያየነውን ነው ምንወርሰው ። the way  the lay out of the bedroom is adopted by the son after he married the girl he was whooped for ( it was not because he loved her tho) is an absolute gem.

4)ሓመልማል፡ what is worse? losing someone you love or the regret that you were proud to give them the one thing their heart desired? ለሚወድን ሰው ብልጣብልጥ  የምንሆነው? በትለይ እኛ ሰቶች ስንወደድ ኩራት ፣ ስንፈቀር እንድንመለክ የምንቋምጥ? ከራሳችን ትንሽዬ ቆርጠን  መስጠት ሚይቅተን?  Maybe I am like her, I lost a love because I was selfish to give a little bit of me just because I was proud, I was drunk on being loved, what else  did I lose

ሌላውን እንገዲ ለናንተ ትውኩኝ። በታንቡት አትቆጩበትም አንዴም አስሬም።


I give it a good⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️


Last day of አለንጋና ምስር


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
Day 6 of አለንጋና ምስር

i now give you the evidence that cats do love books 😊❤️


Bravo! Now you are beginning to think for yourself instead of letting others think for you. That’s the beginning of wisdom.”
 
-Gone with the wind




❤️ በስመአብ reading this was heart warming


Day 5 of አለንጋና ምስር😊 ያው መብራት ጠፍቶ በባትሪ እየተጨናበስን ነው። እኔ ምለው 🕯️ሻማን ግን ማነው ያጠፋው? ቤት ውስጥ ብፈልግ ብፈልግ ከየት ይምጣ፣ ከጎረቤት እንኳ ኮብልሏል፣ ልገዛ ብወጣ በሻማ አቅም 🤭 አፌን አዚዞ መለሰኝ። ማስገባው ስለት የለኝ ሆሆሆ


"I used to think that the moments of greatest despair were those in which one feels most alone. But now I realize that the worst moments are those in which one feels the weight of everyone’s expectations and yet knows that one can never fulfill them. I am surrounded by people who think they understand me, who believe they can save me, but they cannot see that I am beyond salvation. The kind words, the looks of pity, the offers of help—they only deepen the wound, reminding me of a hope that I can no longer feel, of a future that no longer belongs to me."

— Fyodor Dostoevsky, The Idiot






the way you held yourself up, and the way you treat yourself is the key to show other what a value you have


Day 4 of አለንጋና ምስር

enjoying it more than i can tell you even without the dessert


With or without me, i want to see you live your life happily.

Together or not, i hope the universe takes care of you no matter what.

20 last posts shown.