አንተ
አንተን በማወቄ ለማን ምስጋና ላቅርብ? ማንንስ ልረገም? ወይሰ ዝም ነው ምለው? አላውቅም። ምን አልባት እርግማኑንም ምስጋናውንም አንተ ላይ አዥጎደጉደው ይሆናል።
ለምን??
ስለገደልከኝ፣ ላልነሳ አፈር ስላላስከኝ።
ምስጋናውስ?!
እውነትን ባንተ ውሸት ውስጥ እንዳይ ስላደረከኝ፣ ማሳየት ብቻ አይደለም እንድቀበልም ነው ያደረከኝ።
ግን የቱ ይበልጣል? እርግማኑንም ምርቃቱንም ትንሽ ይበዛል ደሞም እርስ በእርሱ ይጣረሳል። መርቆ መርገም ምን ይባላል? መርቆስ መርገም ከየት የመጣ ነው ?? ሆሆሆ ላንተም ቢሆን ይከብድሃል
የተዋወቅንበት ጊዜ .....አይ አንተ እንድታውቀኝ ብዙ ጥሪያለው፣ እንድታየኝ፣ የሴትነት ጠሬኔ እንዲጠራህ እንዳበባ ፈንድቼ ልታይ ብያለው አንተ ሳታውቀኝ እኔ አውቅህ ነበር። ብትጠይቀኝ "ምንህ እንዳማረኝ አላውቅ may be ወንዳወንድነትህ" ብዬ አግበስብሼ አልፈው ነበር። እውነት እንነጋገር ከተባለ ግን ድርብ ጥርስህ ነበር ያስደነገጠኝ (ከየት እንደመጣ ባላውቅም ለድርብ ጥርስ ሟች ነኝ በተለይ ከቆንጆ የሚገመጥ ከንፈር በፈገግታ እሳት ሲገለጥ)፣ የጎርምስና ፂም ያልበቀለበት ከኔ ቆዳ እንኳ የለሰለሰ ጠይም ፊትህ....ጠይም ዓሳ መሳይ አልልህም ስለማይገባኝ (ዓሳ ጠይምነቱ የቱ ጋር እንደሆነ አላውቅም፣ ወይ የጠየመው አጋጥሞኝ አያውቅም)። ሁሉ ነገርህ ለስላሳ ነው። ሳቅህ፣ አይኖችህ፣ አይኖች በጸሐይ ጨረር ቡና ነፀብራቅ ሲረጩ፣ ጸጉርህ፣ ንግግርህ፣ አረማመድህ፣ ስምህ ሁሉ እንደ ወፍ ላባ ይለሰልሰኝ ነበር...እንደ ደመና አይነት ሰማያዊነቱ በሚዋጋ የጠራ ሰማይ የሚንጎማለለው ሃጣ በረዶ የመሰለው ደመና።
እንድታየኝ ያደረኩበት መንገድ ብነግርህ ምን ያደርግልሃል? ብቻ አየኸኝ። ዛሬ ድረስ ያስቀኛል የኔ በማላውቀው መፈንዳት ውስጥ የኔ መንደፋደፍ፣ ያንተ ማየት። አየህ አለማወቅ አንዳንዴ ጥሩ ነው። በልክ ነኝ ስህተት ብዙ እናያለን፣ እጃችንን ይዘው ከሚያስተምሩን ይልቅ በእውር ልባችን ወድቀን የምንነሳው ብዙ ያስተምረናል። አለማወቃችንን። እኔን ያንተ ለማድረግ ነገር ስትፈተፍት፣በማትውልበት ተጎልተህ ጊዜን ስትገድል በላወቀ፣ ባልገባው አግራሞትን በአይኔ ስዬ፣ ግራ መጋባት በድምጼ ሸፍኜ "ምነው?" እልሃለው የባጥ የቆጡን እንድታወራ። አንዳንዴ ግን አምላክ የማሰብ (የመምረጥ?) ችሎታን ሲሰጠን አብሮ ምላስ የምታድጥ እውነት ከጎሮሮአችን ቢተክል እላለው አለ አይደለ እሊናችን የሚያውቀውን ሀቅ ከምላሳችን አንሸራታ ከአፋችን የምታወጣ? አንዳንዴ ነው ታዲያ ሳናውቀው ሳናስበው።
"ጓደኛ አለችኝ በዚ ቀን ስለተጣላን ይሄ ቀን ሁሌ ይከፋኛል" አይኖችህ ይተክዛሉ የዓለምን ክፋትን እንዳዩ ሁሉ
አይኖቼ የሀዘን እንባን አቀርዝዘው "አይዞህ"ን ከንፈሮቼ ያጉተመትማሉ። አየህ አሁን ሳስበው በምንአልባት ውቅያኖስ ውስጥ፣ የኔን ብቸኝነት ባታይ ኖሮ፣ ልቤን የሰበረውን እኔ ሳላውቀው አንተ ባታውቀው ኖሮ.... .. (ኖሮ ብሎ ነገር ግን ደስ አይልም? እውነታውን ቢያንስ በአይነ ህሊናችን የመቀየር ስልጣን ይሰጠናል። ኖሮ ..ኖሮ.. ኖሮ ) ብቻ በመከፋት ፈንታ የልቤን ደስታ አይተሃት ቢሆን የሚያስከፋህም ቀን የኔም አይዞህ አይኖርም ነበር።
"ፍቅረኛ አለሽ?" በዚያ በሚያሰከፋህ ቀን ጠየከኝ
"ነበረኝ፣ግን ተጣላን" እንደተበደለ አማረርኩልህ፣ እንደተገፋ ትከሻህን መደገፊያ አድርጌ አነባሁኝ። አቤት ትከሻህ!!ግርማ ሞገስ ባንተ ትከሻ ነበር የሚለካው።
እውነቱን ልንገርህ?
ፍቅረኛ ነበረኝ ግን አልተጣላንም። የመጀመሪያ ፍቅረኛዬ በfacebook የተተዋወኩት። በጠዋት ቁር 4፣5 ሠፈር አቆራርጦ እኔን ለማየት የሚመጣ ሂጂ ከተባልኩበት ሸፍቼ ማርያም ማዶ ያለ ግም ሜዳ ላይ ቀን ሙሉ በወድሻለው፣ በልሳምሽ፣ በሰፊ ክንድ የማላውቀውን ፍቅር የምኮመኩም። አየህ መልክ የለውም ከጎሬዛ መለስ ያለ ነው (ግን ሴቶችዬ 'ከጎሬዛ መለስ ካለ ይበቀኛል' ስትሉ ከልባቹ ነው? አይመስለኝም) እንዳይደብረው ብዬ ከቀረብኩት ልጅ ፍቅርን አይቻት ነበር። እኔና እውነት ተግባብተን ነበር። ያኔ ግን film ላይ እንደምናየው 'በውበቷ ወንድን አንበርክካ' ብቻ የሆነ romantic scene ያለው መሪ ተዋናይ የሆንኩኝ ነው የመሰለኝ። ከዛ ያለፈ እውቀት የለኝማ። ክብሬን ሲጠብቅ እንኳ በአፍላነት በሾፍኳት የብልግና ተውኔት ተፈታተንኩት። የሚማርበት ኮለጅ ውስጥ የሚጎረብጥ ዴስክ ላይ ጭኔን ከፈትኩኝ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በፍቃዱ ማሩን ሊያዝረበርብ። ፍርሃቱ ይሁን ወይም ሌላ ምንም አላደረገኝም። የሱ ከዚህ እውቀት ንጹህ (ማርያምን አለማወቁን ለማስረዳት ልቅ ሆኜ ብነግርህ ደስ ይለኛል ግን የሱን ንጽህና ማጉደፍ ይሆናል ክብሩን መሬት መጎተት ይሆንብኛል) መሆን፣ እኔ በማያት ግን ባልተረዳዋት የውሸት መውተርተር፣መቃተት...hehe ከዛ በኋላም ግን ለኔ ያለው ክብር ለኔ ያለው ፍቅር አልቀነሰም ነበር። በጀንበር መጥለቅ ፊቱ ፈክቶ "የመጨረሻዬ ሁኚ፣ የኔ ሁኚ"
አንተ ይሄን ጥያቄ በጠየከኝ ሳምንት የሰው ልብ ሰብሬ ሸኘሁትኝ። ለክፋቴ ክፋት በቂ ምክንያት አልሰጠሁትም። ምንአልባት ያኔ ይሆናል ለኔ ቅጣት የሆንከው፣ አክኬ የማላድነው ቁስል፣ ነፍሴ ማቃጠያ ሲዎል። ታዲያ ያንስብኛል? በጊዜው ግን ልቤን በእንጥልጥል ቀጥ ያደረገው ሌላ romantic scene ካንተ ጋር የሌላ ቦታ ጓሮ ላይ በስስ ከንፈሮችህ ስትስመኝ ። ጥሩ ትወናዬን ጀመርኩኝ።
ይቀጥላል.....
✍🏾✍🏾ምንትዋብ
22/06/2017✍🏾✍🏾