የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በመንግስት የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት በሚያስችለው ቁመና ላይ ለማድረስ የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያዎችን ለይቶ በመስራት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰ አስታወቁ።
የባንኩ ማኔጅመንትና ሰራተኛም ባንኩ ሀገራዊ አበርክቶን በተሟላ መልኩ እንዲወጣ ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ፕሬዚዳንቷ ጠይቀዋል።
በተለይ ጠንካራ የስራ ባህልን በመገንባት፣ የውስጥ አሰራሮችን መፈተሸና ለስራ አመቺ ማድረግ፣ የተሻሻሉ ፖሊሲዎችን እና መመሪያዎችን ማዘጋጀት፣ ለባንክ ስራ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ በውስጥ ኦዲት የሚሰጡ ግኝቶችን ፈጥኖ ማስተካከል፣ ራስን ለከፍተኛ ለውጥ ማዘጋጀት፣ ጥራት ያለው የብድር ስርዓት መዘርጋት፣ ባንኩ ለሀገራዊ ልማት የሚያበረክተውን ፋይዳ ተረድቶ በትጋት መስራት እንደሚገባ ነው ዶ/ር እመቤት የገለፁት። ፕሬዚዳንቷ ይህን ያስታወቁት የባንኩ የስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በተገመገመበት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ በግማሽ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በሰጡት ማጠቃለያ እንዳሉት ከዚህ በፊት የተሰጡ ብድሮችን ወደ ጤናማነት ማምጣትና አዲስ የሚሰጡ ብድሮች ደግሞ የተጠኑና ወቅታቸውን ጠብቀው ሊመለሱ በሚችሉ መልኩ ማድረግ ይገባል።
ሰብሳቢው አክለውም ባንኩ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ቢያልፍም በጥሩ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ባንኩ ከፊቱ የሚጠብቁትን ፈተኛዎች በብቃት ለመወጣት በላቀ ትጋት መስራት ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአብዛኛው የፋይናንስ መለኪያዎች ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፣ ከ13.3 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ማሰራጨቱ፣ ከ11.3 ቢሊዮን ብር በላይ ከብድር ተመላሽ ማድረጉ፣ ከ7.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ፣ በተለይም ከዲቢኢ ቦንድ የተሰበሰበ ሀብት 9.3 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን በአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ወቅት ተገልጿል፡፡