ጡቶችዋ የድንግልናን ወተት ማመንጨት በጀመሩ ጊዜ በክንዷ ደግፋ የምታጠባው ሕፃን፣ ፀሐይን እያወጣ ዝናምን እያዘነበ ፍጥረቱን የሚመግብ አምላክ መሆኑን ታውቅ ነበር።
በእርሷ ማኅጸን በዝምታ ያደረው ጽንስ፣ በሰማይ ኃይላት "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እየተባለ የመድረኩ መሠረት እስኪናወጽ ድረስ በታላቅ ድምፅ የሚመሰገን መሆኑ አልተሰወራትም።(ኢሳ 6፥4) ስለዚህም ራሷን ወደ ሆዷ ዘንበል በማድረግ የመላእክቱን ቅዳሴ ታደምጥ ነበር።
ድንግል ወደ እርሷ ማኅጸን የገባው "የሚሳነው ነገር የሌለ የልዑል ልጅ" እንደ ሆነ ብታውቅም ሁሉን አልጋ በአልጋ እንዲያደርግላት ግን አልተማጸነችውም። የልጇን ሁሉን ቻይነት ወልደው በሚያሳድጉ ሁሉ ከሚደርሰው የእናትነት ጭንቅ ማምለጫ አላደረገችውም። ከጡቶቿ ወተት ፈልጎ እንደ ሕፃናት ሲያለቅስ "አምላክ አይደል አይርበውም" ብላ ቸል አላለችም።
ክፉው ሄሮድስ ሊገድለው በፈለገ ጊዜ "የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናቱ" እመቤታችን ድል ነሺነቱ ወዴት አለ? አላለችም። ስለ ሄሮድስ ሠራዊት አስጨናቂነት ጉንጮቿ እስኪቃጠሉ ድረስ አነባች፣ የበኩር ልጇንም አንዴ በጀባዋ አንዴ በጎንዋ እያዘለች የግብጽን ተራሮች እንደ ወፍ ዞረች እንጂ።
በእነዚያ የረሃብ ጊዜያት ድንግል ከሃሊ ልጇ ከሰማይ መና እንዲያዘንምላት ወይም ድንጋዩን ዳቦ እንዲያደርግላት ጠይቃ አልተፈታተነችውም። እስራኤላውያን በበረሃ ጉዟቸው ወቅት የሚከተላቸው (ይዘው የሚጓዙት) ዓለት ነበራቸው። እነርሱም በተጠሙ ጊዜ የሚጠጣ የሚያገኙት ከዚያ ዓለት ከሚፈልቀው ውኃ ነበር።
ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ታሪክ በማስታወስ በበረሃ ውኃ ያፈልቅላቸው የነበረው ዓለት በምሥጢር የክርስቶስ ምሳሌ መሆኑን ሲናገር "ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ" ይላል።(1ኛ ቆሮ 10፥3) እመቤታችን የማይቋረጥ የሕይወት ውኃ የሚፈልቅበትን ይህን መንፈሳዊ ዓለት ይዛ ስትሰደድ አንድ ቀን ስለ ጥሟ አላማረረችውም።
ራሱን በፈቃዱ ባዶ ላደረገው አምላኳ ከሁሉ ይልቅ በሥጋ ባዶ መሆንን በደስታ ለመቀበል የተዘጋጀ ቆራጥ ኅሊና ነበራት። ስለዚህም በልጇ ምክንያት ከደረሰባት መከራ በአንዱ እንኳን አላማረረችም።
@Deaconchernet