አርሶ አምባ ቀበሌ❗️
ደሴ :ሐምሌ 5-11-2014
አርሶ አምባ በምትባል ቀበሌ በአርሶ አደሮች ሰብል ላይ ከብቶች መለቀቃቸውን ምክንያት በማድረግ የተጀመረው ይህ ጦርነት በትናንትናው ዕለት ወደ መንተኬ ሸረፋ ወደምትባል ቀበሌ ተስፋፍቷል።
የቀበሌው አስተዳዳሪ አቶ ካሳዬ ክብረት እንዳሉት በትናንትናው ዕለት ምሽት ላይ ከጅሌ ጥሙጋ ቀበሌዎች የመጡ ታጣቂዎች ከ400 በላይ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ተናግረዋል።
በስፍራው እስካሁን የመጣልን የጸጥታ ሀይል የለም የሚሉት ዋና አስተዳዳሪው በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎችን አስከሬን ማንሳት እንዳልቻሉም ገልጸዋል።
በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች ሞተዋል? በሚል ላነሳንላቸው ጥያቄም "እስካሁን አራት ሰዎች ሞተዋል አራት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፣ የት እንዳሉ እና ይሙቱ ይቁሰሉ ያላወቅናቸው ሰዎች አሉ" ብለዋል።
እነዚህ ታጣቂዎች ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ጥቃት አድርሰውብን ነበር የሚሉት አስተዳዳሪው መንግስት ለቤት መስሪያ በሚል የሰጠንን የቤት መስሪያ ቆርቆሮዎችን እና የቤት እንስሳቶቻችን ሁሉ ዳግም ተዘርፈዋል ብለዋል።
የሞቱ ሰዎችን እንድንቀብር እና ሌላ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ መንግሥት የጸጥታ ሀይል እንዲልክላቸውም አስተዳዳሪው ጠይቀዋል።
የአርሶ አምባ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ማሞ ማስረሻ በበኩላቸው እስካሁን ሰባት ሰዎች ከጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ቀበሌዎች በመጡ ታጣቂዎች መገደላቸውን እና 150 መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን እንዳረጋገጡ፣ የተወሰኑትን ሟቾች ስርዓተ ቀብር እንደፈጸሙ ገልጸው ቀሪዎቹን አስከሬን ማንሳት እንዳልተቻለ ተናግረዋል።
አዳሩን ጦርነቱ ጋብ ቢልም ዛሬ ጠዋት ጀምሮ ብዙ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች ወደ አርሶአምባ ቀበሌ በመኪና እየመጡ መሆኑንም አስተዳዳሪው ገልጸዋል ።
የታጣቂዎቹን ጥቃት አርሶ አደር ሚሊሻዎች ለመመከት እየሞከሩ ቢሆንም የታጣቂዎቹ ቁጥር እና የታጠቁት መሳሪያ የማይመጣጠን ነው፣ ጉዳዩን ለዞን እና ለወረዳ ብናሳውቅም ተጨማሪ የመንግስት ጸጥታ ሀይል አልመጣልንም ሲሉ ነግረውናል።
Via:አዲስ ነጋሪ
🧔♂➤ @Dessieowner
ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity
ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes