ዴንማርክ ለኢትዮጵያ የደን ልማት የ15 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች
*******************
ዴንማርክ በኢትዮጵያ የደን ልማት የተፈጥሮ ደኖችን ለመጠበቅ እና በሀገሪቱ ለሚከናወኑ አዳዲስ የደን ሽፋኖች የሚውል የ15 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች።
በአዘር ባጃን ባኩ እየተካሄደ ካለው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ በርካታ የሁለትዮሽ እንዲሁም የባለብዙ ወገን ውይይቶችን እያደረገች ትገኛለች።
ከዴንማርክ መንግስት ጋር በተደረገው የሁለትዮሽ ውይይትም የኢትዮጵያን የደን ልማት ለመደገፍ ስምምነት ላይ ተድርሷል።
ዴንማርክ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ፖሊሲ አጋር ናት ያሉት የዴንማርክ መንግስት ተወካይ ሳይመን ዋንድል ፒተርሰን፤ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ላይ ለምትሰራው ስራ ዴንማርክ አጋርነቷን ታረጋግጣለች ብለዋል።
የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ስዩም መኮንን በበኩላቸው፤ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ እየሰራች ያለችውን ተጨባጭ ስራ የተቀረው ዓለም ሊገነዘበው ይገባል ያሉ ሲሆን የዴንማርክ መንግስት የወሰነው ውሳኔ የኢትዮጵያን ጥረት የሚደግፍ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በተመስገን ሽፈራው